በደቡብ ወሎ ዞን በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን 103 ጤና ጣብያዎች እና 9 ሆስፒታሎች ላይ ውድመትና ዘረፋ መፈጸሙን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታውቋል።

የትግራይ ወራሪና አሸባሪ ቡድን በአማራ ክልል ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች በተቋማት ላይ ከፍተኛ የሆነ ዘረፋና ወድመት አድርሷል።

ዘረፋና ውድመት ካደረሰባቸው ተቋማት መካከል የጤና ተቋማትና የትምህርት ተቋማት ከግንባር ቀደሞቹ ይጠቀሳሉ። የሽብር ቡድኑ ወረራ በፈፀመባቸው የደቡብ ወሎ አካባቢዎች የጤና ተቋማትን አውድሟል።

የወገን ጦር በሚያደርስበት ከባድ ምት አባላቱ እንደ ቅጠል እየረገፈ የሚሸሸው ጠላት ተቋማትን እያወደመ ነው የሚሸሸው። ከሰሞኑ በገነቴ ከተማ ተመትቶ የወጣው የሽብር ቡድኑ የገነቴ ጤና ጣብያን ሙሉ በሙሉ አውድሞት ነው የሸሸው።

የገነቴ ጤና ጣብያ ኃላፊ አረቡ መሐመድ ሠፊ ለሆነ ማኅበረሰብ የጤና አገልግሎት የሚሰጠው ተቋም ሙሉ ለሙሉ ወድሟል ብለዋል።

በጤና ጣብያው ለአገልግሎት መስጫ የሚሆኑ መሳሪያዎች ኹሉ ውድመትና ዘረፋ ደርሶባቸዋል ነው ያሉት።

አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ሕዝብን በብዙ መንገድ ሊጎዳ እንደመጣ አንዱ ማመላከቸው በጤና ተቋሙ ላይ ያደረሰው ጉዳት መሆኑንም አንስተዋል። የገነቴ ጤና ጣብያ ከ25 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የጤና አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበርም ኃላፊው አንስተዋል።

በአሁኑ ወቅት በገነቴ ጤና ጣብያ የጤና አገልግሎት ይሰጡ የነበሩ ዜጎችም ከጤና አገልግሎት ውጭ እንዲሆኑ መገደዳቸውን ነው የተናገሩት።

አውዳሚና ዘራፊው ቡድን በጤና ጣብያው የህክምና መስጫ መድኃኒትና መሳሪያ መዝረፉንና የተቀረውን ደግሞ አውድሞ መሸሹንም አስታውቀዋል።

የአሚኮ የጋዜጠኞች ቡድን በሥፍራው ተገኝቶ እንደተመለከተው ጤና ጣብያው ከፍተኛ ውድመትና ዘረፋ ደርሶበታል። ተከታታይ ሕክምና የሚወስዱ ዜጎች አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደወደቁም ኃላፊው ገልጸዋል።

የጤና ተቋሙን ወደ ቀደመ አገልግሎቱ ለመመለስ ሥራዎች መጀመራቸውንም አንስተዋል። ተቋሙ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ እንዲመለስና የዜጎች የጤና ችግር ያሳስበኛል የሚል ሕዝብ ወዳድ ኹሉ ድጋፍ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አንተነህ ደመላሽ አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን የአማራ እናቶች እና ሕፃናት ታክመው እንዳይድኑ ዓላማ ሰንቆ በግልፅ እየሠራ እንደሚገኝ ነው የገለፁት።

በዞኑ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩ 133 ጤና ጣብያዎች መካከል 103 የሚሆኑት በወራሪውና አሸባሪው ቡድን ውድመትና ዘረፋ ደርሶባቸዋል ብለዋል። በዞኑ አገልግሎት ከሚሰጡ 13 ሆስፒታሎች መካከል ደግሞ ዘጠኙ ውድመትና ዘረፋ ደርሶባቸዋል ነው ያሉት።

የደሴ ሪፈራል ሆስፒታልን ጨምሮ የኮምቦልቻ፣ የቦሩና የአቀስታ አጠቃላይ ሆስፒታሎችም ከተጎዱ ሆስፒታሎች መካከል ይገኙበታል። በዞኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጤና ኬላዎችም ውድመት እንደደረሰባቸው ነው መምሪያ ኃላፊው ያስታወቁት።

አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን መውሰድ የሚችለውን የሕክምና መስጫ መሳሪያዎችን ሲወስድ መውሰድ የማይችለውን ደግሞ ሕዝብ እንዳይጠቀምበት ከጥቅም ውጭ አድርጎ ነው የሸሸው።

ጠላት በገባበት ኹሉ በጤና ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት እንደሚያደርስ የተናገሩት ኃላፊው የደቡብ ወሎ ሕዝብ የጤና አገልግሎት እንዳያገኝ የሚያደርግ ጉዳት ማድረሱንም ገልጸዋል።

ነጻ በወጡ አካባቢዎች የጤና ተቋማትን ጉዳት የሚለይ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል። በዞኑ የወሊድ አገልግሎት፣ የድንገተኛ ሕክምና እና ተከታታይ መድኃኒት ተጠቃሚ የኾኑ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አገልግሎት በአፋጣኝ እንዲጀመር እየሠሩ መሆናቸውን ነው የተናገሩት። አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ የክልሉ ዜጎች ከጤና አገልግሎት ውጭ ሆነዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator