በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከማሼ ዞን ሚዥጋ ወረዳ አንገር ሜጢ ቀበሌ ዓመቱን ሁሉ የደከሙበትን አዝመራ ምርት በመሰብሰብ ላይ የነበሩ 26 አማራዎች ተገድለዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመው በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ታህሳስ 13 ቀን 2014 ሲሆን ስርዓተ ቀብራቸው በአካባቢው ባሉ ጉምዞች መፈጸሙ ተገልጧል።
የአካባቢው ምንጮች ለአሚማ እንደገለጹት ከተገደሉት ሰዎች መካከል:_
1)ቢሻው ይርሳው፣
2) ምትኩ ቢሻው፣
3) በልስቲ ይርሳው፣
4) ተዋቸው አስማረ፣
5) ሸጋው ጫኔ፣
6) ፈንታሁን ቢሻው፣
7) አስቴር፣
8/ ትብለጥ እና
9) ዘመን ገደፋዬ የተባሉ አማራዎች ይገኙበታል።
በተመሳሳይ 3 ሴቶች በሽብር ቡድኑ ታግተው መወሰዳቸው ተገልጧል፤ አንድ ሰው ደግሞ አምልጦ ወደ ነቀምት ማለፉ ተሰምቷል።
በተመሳሳይ በወሪንቃ ቀበሌ ታህሳስ 15 ቀን 2014 አቶ ጌታቸው ሀሰን የተባሉ ርሃብ የጠናባቸው ተፈናቃይ አባት ወደ አዝመራቸው ሲሄዱ ታርደዋል ተብሏል።
አስከሬን ፍለጋ ታህሳስ 17 ቀን 2014 ፍለጋ ሲሄዱ ደግሞ አቶ ሸጋ ሀሰን የተባለ ሰው ደግሞ በወሪንቃ ቀበሌ ዳልቻ አካባቢ ሲደርስ መቁሰሉ ተሰምቷል።
ይህ ሁሉ ሲሆን ወረዳ ላይ ያለው መከላከያና ልዩ ኃይል፣ አዋሳኝ በሆነው ሳሲጋ ወረዳ በሬዳ ዙሪያ ያለው የመከላከያ ኃይል እነዚህን ኃይሎች ለማጥፋት አለመንቀሳቀሱ ብዙዎችን ያሳዘነ መሆኑ ምንጮች ለአሚማ ተናግረዋል።