መዋቅራዊ ድጋፍ ያለው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና የዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹ
በምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ አማራዎችን በተኩስ እሩምታ ጨፈጨፉ።
በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ አልጌ ቀበሌ መጋቢት 8/2014 ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ በአማራዎች ላይ ማንነት ተኮር ጥቃት እየተፈጸመ ነው።
አንድ ካራንቡላ ቤት ብቻ የነበሩ 7 ወጣቶችን በጥይት ደብድበው ከመግደል አልፈው ቤት ለቤት በመዞር ማንነት ተኮር ግድያ መፈጸማቸው ተገልጧል።
መጋቢት 8/2014 ከምሽቱ 2 ሰዓት የጀመረው ጥቃት ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ እንዳልቆመና የደረሰ አንድም የጸጥታ አካል አለመኖሩን ተደብቀው የተረፉ ነዋሪዎች ለአሚማ ተናግረዋል።
ታቅዶበት ተፈጽሟል በተባለው ጥቃት ለጊዜው የደረሰንን መረጃ ብንመለከት ከተገደሉት 8 ሰዎች መካከል 6 አማራዎች ሲሆኑ 2ቱ የወላይታ ተወላጆች እንደሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
ከ6 በላይ አማራዎች የቆሰሉ ስለመሆኑና ወደ ህክምና ለማድረስ እና የተገደሉትን አስከሬን ለማንሳት ከተደወለላቸው የጸጥታ አካላት መካከል አንዱም እንኳ ለመድረስ አለመቻሉን ለማወቅ ተችሏል።
የፌደራል ፖሊስ የመረጃ ክፍል “ነገ ደውሉ” የሚል አሳዛኝና አሳፋሪ ምላሽ ሰጥተዋል።