በጠላት የተከበበው የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልዉና አደጋ ለመመከት ወደ ትግል የገባው ፋኖ አረጋ ዘውዱ በሚታገልለትና ወገኔ በሚለው የመካነሰላም ፖሊስ በተኮሰበት ጥይት ህይወቱ አልፏል፡፡

አዎ መካነሰላም እና አጠቃላይ ቦረና የምስራቅ አማራ ፋኖ ዉለታ አለበት።

ያኔ የመንግስት አመራርና አጠቃላይ የጸጥታ መዋቅሯ በሜሴጅ መልዕክት እየተለዋወጠ ሁሉም ለጠላት አሳልፎ ጥሏት የሄደችው መካነሰላም ከተማ በምስራቅ አማራ ፋኖ ጀግና ልጆች በጠላት እንዳትያዝ ሆናለች፡፡

ስለሆነም የአካባቢው ማህበረሰብ ዉለታችሁን መክፈል አለባችሁና ጀግናችሁን በሰላምና በጀግና ሽኝት ስርአተ ቀብሩን እንድትፈጽሙ ስንል በምስራቅ አማራ ፋኖ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ የሚመለከተው የመንግስት አካል ጉዳዩን በጥልቀት እንዲመለከተዉና ወንጀለኛዉን በፍጥነት ለህግ እንዲያቀርብ እንፈልጋለን፡፡

አስር አለቃ አረጋ ዘውዱ የመካነሰላም ልጅ እና የምስራቅ አማራ ፋኖ ዲሽቃ ተኩሽ በዞብል ግንባር በነበረው ተጋድሎም ብዙ ጀብዶችን መፈጸሙ ይታወሳል፡፡

መጋቢት 01/2014 ዓ.ም ቤተሰብ ለመጠየቅ ፈቃድ ተሰጥቶት ወደ መካነሰላም ከመሄዱ በትውልድ ቦታው ሲደርስ በመካነሰላም ፖሊስ በጥይት ተመትቶ ሆስፒታል ገብቶ እንደነበር ተገልጧል፡፡

ስለሆነም የዚህ ድርጊት መጨረሻው ለትግሉም ለአማራ ህዝብም የማይበጅ ተግባር በመሆኑ የሚመለከተው የመንግስት አካል ቢያስብበት መልካም ነው።
” ፋኖነት ለኢትዮጵያዊነት ህያው ምስክር ነው፡፡”

መረጃው የራያ ጢነኛ ነው።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator