““““““““““““““““““““““““““““`
ከአማራ ሕዝባዊ ኃይል(ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
የዜጎችን ሰላም ደህንነት የመጠበቅ ግዴታዉን መወጣት የተሳነው መንግስት ያደረገውን ሀገር የማዳን ጥሪ እና በህዝባችን ላይ የተደቀነውን የህልውና አደጋ ተከትሎ በአዲስ መልኩ የተጠናከረው የፋኖ አደረጃጀት ሀገር እና ህዝብን በመጠበቅ ከባድ መስዋዕትነት የከፈለ እና በመክፈል ላይ ያለ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁን እንጅ ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በተለይም መንግስት ከህወሃት ጋር ያለዉን ጦርነት አጠናቅቄያለሁ ካለ ማግስት ጀምሮ ጠላቶቻችን በብርቱ መታገል ተስኗቸው ያሉ የመንግስት የፀጥታ አመራሮች በበርካታ የክልሉ አካባቢወች የፋኖን ስልጠና የማስጓጎል፣ ፋኖወችን የማሳደድ፣ የማሰር እና የተለያዩ ትንኮሳወችን የመፈፀም እኩይ ተግባራት ሲፈፅሙ ቆይተዋል።

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ቀደም ሲል ፀረ-ፋኖ መንግስታዊ እንቅስቃሴ በተከሰተባቸው ሰሜን ሸዋ፣ ሁሉም የጎጃም ዞኖች እና ደቡብ ጎንደር አካባቢ ያሉ ፋኖወች ችግሮችን በትዕግስት እና በጥበብ እንዲያልፉ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከጧቱ 2:00 አካባቢ ከቤተ ክርስቲያን እየተመለሰ የነበረዉን ፋኖ ደርሳችሁ አትንኩትን የፀጥታ ኃይሎች ያልተመዘገ መሳሪያ አለህ በማለት ያለ መያዣ ትዕዛዝ በከባባ ይዘው ማሰራቸውን እና ያለ ምንም ህጋዊ ምክንያት የፋኖ መዝገቡን ቤት መክበባቸውን ተከትሎ በሰላማዊ መንገድ ሊያናግሯቸው ከቀረቧቸው የአካባቢው ፋኖወች ጋር “ጀግና ከሆናችሁ ግጠሙን” በሚል ዛቻ በማቅረብ ጉዳዩ ወደ ግጭት እንዲያመራ አድርገዋል። በዚህ ግጭት ምክንያት በአቀስታ ግምባር የፋኖ ብርጌድ መርቶ ለድል ያበቃው ፋኖ መዝገቡን ጨምሮ የሰወች ሕይወት አልፏል።

መንግስት ባደረገው ጥሪ መሰረት በክልሉ ውስጥ ያልተመዘገበ መሳሪያ መያዝ የተለመደ ሆኖ ባለበት በአሁኑ ወቅት ይህንን ምክንያት በማድረግ ግምባር ላይ ሲፋለሙ የነበሩ ፋኖወችን ማሰር በፋኖ ላይ የተቃጣ ጥቃት መሆኑን እንገነዘባለን።

እስካሁን ድረስ ከፋኖ ጋር ግጭት በተከሰተባቸው አብዛኞቹ አካባቢወች በፋኖ አማካኝነት የተፈፀመ ግልፅ የወንጀል ተግባር በሌለበት ከፀጥታ ኃይሉ ጋር ግጭት መፈጠሩ እና በዚህም ምክንያት ደም መፍሰሱ በእጅጉ አሳዝኖናል። በተለይም ህወሃት ለዳግም ወረራ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ባለበት በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ ሆነን ፋኖን ካለጠፋሁ የሚል የፀጥታ እና የፖለቲካ አመራር መኖሩ ህዝቡን በከፍተኛ ደረጃ አስቆጥቷል።
በመሆኑም:-
1/ የመንግስት አመራሮች በተለይም በፀጥታ መዋቅሩ አመራርነት ላይ ያላችሁ ወንድሞቻችን የፋኖ መሰልጠን፣ መደራጀት እና መታጠቅ እናንተን ጭምር ከውርደት የሚታደግ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከፋኖው ጋር በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ እና የጋራ የህልውና ጠላቶቻችን ላይ ያነጣጠረ ቀና መንገድን እንድትከተሉ፣ ከዚህ በኋላ ሊከሰቱ ከሚችሉ ግጭት ቀስቃሽ ተግባራት እንድትቆጠቡ እና ጥቃቅን ችግሮችን በውይይት እንጅ በአፈሙዝ ለመፍታት እንዳትሞክሩ ጥሪ እናቀርባለን።

2/ መላው የአማራ ሕዝብ በፋኖወች ላይ የሚደርሰውን የተቀነባበረ ዘመቻ ለማስቆም በመንግስት ላይ አስፈላጊዉን ጫና በማድረግ የአማራ ህዝብ እንደ መርገምት የተጫኑትን ውጫዊ ጠላቶቹን የሚመክትበት እድል እንዳይመክን ተገቢዉን ትግል እንዲያደርግ እንጠይቃለን።

3/ በሁሉም አካባቢ በማናቸውም አይነት የፋኖ አደረጃጀት ዉስጥ ያላችሁ ጓዶቻችን እና መላው የአማራ ወጣቶች ያለንበትን ወሳኝ የታሪክ መታጠፊያ እንድትገነዘቡ እና የሚደርሱ ትንኮሳወችን እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ በጥበብ እና በብስለት በማለፍ የትግላችን መዳረሻ ግብ ላይ ሳንደደርስ በአጭሩ ለመቅጨት የቋመጡ የውስጥ ቅርብ አዳሪወችን እና ስውር እጃቸውን የሰደዱ ውጫዊ ኃይሎችን የሚያሳፍር የተግባር እና አመለካከት ባለቤቶች መሆን እንዳለብን ለአፍታም እንዳንዘናጋ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

4/ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የፋኖ መደራጀት የአማራ ህዝብ ጥንካሬ፣ የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ደግሞ የኢትዮጵያ ጥንካሬ መሆኑን ያለፈው ታሪካችን እና ካልተቋጨው የጦርነት ሂደት መገንዘብ የሚቻል በመሆኑ መንግስት እየሄደበት ካለው የጥፋት መንገድ እንዲታቀብ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ እንድትመክሩ እና የተለመደው ድጋፋችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እናቀርባለን።

5/ በመጨረሻም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰላም እና ደህንነት እንዲሁም ለህልዉና ትግላችን ስኬታማነት ሲባል ለፋኖ መዝገቡ እና ለሌሎች ህልፈት ምክንያት የሆኑ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ እና መንግስት ከግጭት ቀስቃሽ ድርጊቶች እንዲቆጠብ በድጋሚ እያሳሰብን ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ለአማራ ህዝብ ህልዉና ሲባል በቀጣይ መረር ያለ የትግል ጥሪ ለማድረግ የምንገደድ መሆኑን እናሳውቃለን።

በዚህ አጋጣሚ የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በሞጣ ከተማ ፋኖ ላይ የተፈፀምመዉን አፈና ለመስበር ባደረገው ተጋድሎ የተሰዋዉን ወንድማችን ፋኖ 10 አለቃ መዝገቡ ዋለልኝ ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቹ እና የትግል አጋሮቹ መፅናናትን እንመኛለን።
የአማራ ልዩ ኃይል የማህበረሰቡን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ ላሳየው ህዝባዊ ወገንተኝነት ላቅ ያለ ክብር ያለን መሆኑን እንገልፃለን። ከሐቅ እና ከፋኖ ጎን የተሰለፈውን የሞጣ ከተማ እና አካባቢዉን ህዝብም በእጅጉ እናመሰግናለን።

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ)
ባሕርዳር- ኢትዮጵያ

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator

Hi, How can I help you? 

02:22
Log In / Sign Up