ጦማሪ መስከረም አበራ

ለነፍስ የሚናገረው ዘመነ ካሴ !

ዘመነ ሲያወራ በጆሮየ ሳይሆን በነፍሴ እሰማዋለሁ-ዛሬ ታስሮ አይደለም ድሮም …. ዘመነ የሚናገረው ለጆሮ ሳይሆን ለነፍስ ነው፡፡ ንግግሩ ገፈት፣ግሳንግስ የሌለው በደምስር የሚሰርግ ነገር ነው! ዘመነ ካሴ የአማራ ህዝብ ችግር የት ድረስ እንደሚጠልቅ እና የት ድረስ እንደሚዘረጋ እኔ ገባኝ ብየ በማስበው መጠን የገባው ስለሆነ በንግግሩ በደኋላ እየጎተተ አያደክመኝም፤ዘሜ “ይሄ ደግሞ ገና እዚህ ላይ ነው እንዴ?” አስብሎኝ አያውቅመ፤ይልቅስ “የቆሙለትን ህዝብ ጉዳይ እንዲህ አሳጥሮ ግን አስውቦ መናገር ይቻላል ለካ!” ያስብለኛል፤ያስገርመኛል፤ “የህዝብን ህመም መታመምም ለካ እንዲህ አምሮ ይገለፃል” ያሰኘኛል! ስሜትን በቃላት መወከል ለዘመነ ቀላል ነው….

ዘመነ ለነፍስ ይናገራል፤ዘመነ እየፈጩ ጥሬ አይደለም፤ዘመነ የወደቀ ልብን የሚያነሳ፣የዛለ ጉልበትን የሚያበረታ፣በሰው ተስፋ ልትቆርጥ ጫፍ የደረሰች ነፍስን የሚመልስ አንዳች ምትሃት አለው! ዘመነ በትውልድ ተስፋ ላለመቁረጥ ምክንያት የሆነኝ ምልክቴ ነው፤ዘመነ ብአዲናዊነት አፍኖ ለያዘው ትውልድ የቱባው አማራነት ምክልት ነው፡፡ የዘመነ ማስተዋል፣የዘመነ ቀድሞ ስለወደቀ የትግል ጓድ ደም የመሰልሰል ባለማተብነት ብአዲናዊነት ለተገነው የከሃዲነት ጨለማ ላምባዲና ሆኖ ቱባውን የአማራነት እሴት ወለል የሚያደርግ ነው፡፡ ዘመነ ስለወደቁ ጓደኖቹ ነፍሱ ተሸራርፋ የሰለለች በመሆኑ አንድ ወንድሙ ለእሱ ሲል እንዳይወድቅ፣አንድ የቀየው ሰው በእሱ ምክንያት እንዳይታወክ ሲል ደጀን የሆነለትን ህዝብ ርቆ ለመሄድ የወሰነ ፣በዚህም ምክንያት በጀግና መሳይ ቡከኖች እጅ የወደቀ፣ማስተዋሉ አደጋ የሆነበት የትውልድ ራስ ነው!

ዘመነ ውሃ ደፋንበት ሲሉ ይብስ የሚግል ለጊዜው ብአዴናዊነት የሸፈነው ነገ ግንበክብር የሚገለጠው የእውነተኛው የአማራነት ቅሪት ነው! ዘመነ ለህዝቡ ክብር መመለስ ሲል የሚንተከተከውን የራሱን የቁጭት እሳተ ገሞራ በራሱ እጅ እንኳን ለመንካት እንደማይችል እየነገረ የቀዘቀዘውን ልብ ሁሉ የሚያሞቅ ባለ ትኩስ ነፍስ የትውልድ ምልክት ነው !
ምልክት ያለው ትውልድ እድለኛ ነው……. !

https://m.youtube.com/watch?fbclid=IwAR3EL2uru53bI1PkTZydnu6BAatroR08LJsLXN4gAvdhZAmOEETGh1zhDxk&v=PvUwaFyWRqI&feature=youtu.be

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator