0 0
Read Time:4 Minute, 36 Second

ከአማራ ሕዝባዊ ኃይል ( ፋኖ ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ (ጋሻ አማራ) የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

ከፖለቲካውና ከኢኮኖሚው በፍፁም ከማግለል በተጨማሪ በዋናነት በእውቀታቸውና አበርክቶአቸው የታወቁ ስመ ጥር አማራ ምሁሮችን፣ የእምነት አባቶችን፣ የጦር መኮንኖችን፣ ፋኖ አርበኞችና ትውልድ ተረካቢ ተማሪዎችን በመረሸን አስሮ በማንኮላሸትና በማሳደድ የአማራን ትውልድ ቅብብሎሽ ለማቋረጥ በግልፅና በተለያዩ ሴራዎች የታጀቡ አለም አቀፍ ወንጀሎችን በማናለብኝነት በማከናወን እና በትህነግ ወያኔና በኦነግ ተዘጋጅቶ በተግባር ላይ የዋለውን ፀረ አማራ ህገ መንግስት የሚፈፅመውና የሚያስፈፅመው ብአዴን ለተፈጠረለት አማራን የማጥፋት ወንጀል በወያኔ ትህነግና ኦነግ ከተመሰረተበት 1987 ዓ.ም ጀምሮ መሰናክሎች ሲገጥሙት ቆዳውን በመቀያየር አፈር ልሶ በመነሳት ዛሬ ላይ ደርሷል አማራንም ዛሬ ላለበት ሁኔታ አብቅቷል። 

የተከበርኸው የአማራ ሕዝብ ሆይ፣ አያት ቅድመ አያቶችህ አጥንታቸውን ከስክሰው፣ ደማቸውን አፍሠው፣ ላባቸውን እረጭተው በፈጠሯት ኢትዮጵያ መኖር አትችልም ተብለህ በጅምላ እየተጨፈጨፍህ፤ በጅምላ እየተፈናቀልህ እና ብሔራዊ ቀውስ ውስጥ በመውደቅ ተዋክበህ እንድትጠፋ የሚፈፀምብህን ዓለም አቀፍ ዘር ማጥፋት ወንጀል አጥፊዎችህ አደረጃጀቶች ከዛሬ ነገ ልብ ገዝተው ያቆማሉ በማለት ያሳየኸው ከልክ ያለፍ ሆደ ሰፊነትና ቻይነት ለአጥፊ ጠላቶችህ የልብ ልብ እየሰጠ በአደባባይ እየወጡ አማራን ሰብረነዋል፣ አንበርክከነዋል ለማለት መብቃታቸው ዋጋ እያስከፈለህ መሆኑን ቢረፍድም ዛሬ ላይ መረዳትህን ተገንዝበናል። 

አማራንና ኢትዮጵያን ወዳድ ኢትዮጵያውያንን ነጥሎ በመምታት ከተቻለ በማጥፋት ካልተቻለ የተንበረከከ አናሳ በማድረግ ኢትዮጵያን በመብተን በአማራና በሌሎች አፅመ እርስት ላይ ታላቋን ትግርይ እና በገዳ እምነትና ባህል የምትመራ ኢትዮጵያን ካልተቻለ ታላቋን ኦሮሚያን ለማዋለድ ሲፈፀም የኖረው ወንጀል የመጨረሻው ምራፍ ትህነግ አማራን እንዲወር ብአዴንና የኦነጉ ብልፅግና በቀጥታና በተዘዋዋሪ አማራውን በማስመታት ትህነግን ለድል ለማብቃት ላይ መሆናቸን አገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ከሆነ ውሎ አድሯል 

አማራ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ለመድፈር የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ለማወክ በባርነት ለመግዛት በየጊዜው የሚነሱ ኃይሎችን በንግግር የሚያምነውን በንግግር በማሳመን በጦርነት የሚያምነውን በጦርነት በመቅጣት በተግባር የተመሰከረለት የታሪክ ባለቤት መሆኑ አሁን በፀረ አማራዎች ትህነግ፣ ኦነግ፣ ብልፅግናና፣ ብአዴን የተሸረበ ሴራ በተከፈተ የመጀመሪያው ዙር ጦርነት በመሳሪያ አይነትና ክምችት በሰረዊት ብዛትና ስልጠና በተዘረፈ ገንዘብና በውጭ ድጋፍ በእብሪት ሲደነፋ የነበረውን ትህነግን ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አከረካሪውን ሰብሮ መሳለቂያ የተደረገው የውጭ ተላላኪው ፀረ አማራው ትህነግ የአማራን የጦር ባለሟልነት በስልጠና ሳይሆን በደም የወረሰው የአማራ ማንነት መገለጫ መሆኑን ከቀበሮ ጉድጓዱ ሆኖ መመስከሩን ልብ ይሏል። 

ታላቁ የአማራ ሕዝብ ሆይ፣ በደም የምትወርሰው ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ የመጣው ጀግንነትህ በጦር ሜዳ ጠላትን ማንበርከክህ በፖለቲካም ታግዞ ለተቀናጀ ድል ባለመብቃቱ ሳትፈጥረውና ሳትመርጠው በጠላቶችህ ተፈጥሮ በተጫነብህ በብአዴን መመራትህ በቀጥታና በሴራ የትህነግ፣ የኦነግ፣ የኢዜማና መሰል ፀረ አማራዎች እንዲጨፈጭፉህ አባት አያቶችህ በፈጠሯት ኢትዮጵያ እንዳትኖር ተፈርዶብህ የጠላቶችህ መዘባበቻ ተደርገሀል። 

ስለሆነም አንተ የተከበርህ ታላቅ ህዝብ ሆይ፣ በውጭ አገራት የሚኖሩ ከአብራክህ የወጡ አማራዎች ስብስብ የሆነው ጋሻ አማራ የሚከተለውን ራስን የማዳን ጥሪ ሲያስተላልፍ ለዘላቂ ድል ትበቃ ዘንድ ጥሪአችንን ተቀብለህ ለምታደርገው ሁሉን አቀፍ ትግል ወገናችንን በማስተባበር የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ በአማራነታችን እንገደዳለን። 

ስለዚህ በአሁኑ ግዜ ለሶስተኛ ግዜ የትህነግ ወራሪ ቡድን የአማራን ክልል ድንበር ጥሶ እንደ አለፈው አመት የአማራን ህዝብ ለማውረድ፣ ተቃሞቹን ለማውደም፣ እናቶችን ለመግደል፣ ልጆቻቸውን ለመደፍር፣ ከአብይ መከላከያ ጋር በመመሳጠር እንዳለፈው መከላከያው በማፈግፈግ ቦታውን ለትህነግ አሳልፎ በመስጠት ላይ ይገኛል። ስለዚህ አማራውን በጦርነት አንበርክኮ የኦነግና የትህነግ ባሪያ አድርጎ ለመግዛት የሚደረገውን አሻጥር እናወግዛለን። ለዚሁም ተላላኪ ሆኖ የክልሉን ህዝብ እያስገደለና እያስጨፈጨፈ ያለውን ብአዴንን ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ የአማራ ህዝብ በአንድነት ታግሎ እንዲያስወግደው ለፋኖና ለአማራ ልዩ ኃይል እንዲሁም ለአማራ ሚልሺያ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ብአዴን እስካለ ድረስ አማራ ነፃ ሊወጣ እንደማይችል ሁሉ፤ በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ በሚኖርበት አካባቢ ህዝባዊ አመፅ በማካሄድ ብአዲንና ካዴሬዎቹን ከትከሻህ ላይ ነቅለህ መጣል፣ ካልቻልክ መፃኢ እድልህ ለትህነግና ለአቢዩ ኦነግ ባሪያ ሆነህ መገዛት ነው። ስለዚህ ነጻነትህን ለማወጅ ቅን ጨርቄን ሳትል ዛሬ ተነስተህ ፊልሚያውን እንድትጀመር አብክረን እናሳስባለን። 

  1. የተከበርሕው የአማራ ህዝብ ከዛሬ ጀምሮ ብአዴን ትህነግና ኦነግ እኩይ አላማቸውን ለማሳካት ፈጥረው የጫኑብህ አደረጃጀት መሆኑንና አመራሮቹንም ላለፉት 27 አመታት በፊት ትህነግ አሁን ኦነግ እያመጣ የሚጭንብህ መሆኑን በመገንዘብ ለዚህ ያበቃህ ይህ ብአዴን የተባለ አደረጃጀት መሆኑን አስምረህ አቋም ያዝ።  
  2. ከዛሬ ጀምሮ የትህነግ የኦነግ የኢዜማና የማናቸውም ፀረ አማራ ቡድኖች ስብስቦችና ግለሰቦች ዋና መገልገያቸው፣ የጀርባ አከርካሪያቸውና የሕይወት እስትንፋሳቸው ብአዴን መሆኑን አቋም ስትይዝ ትግልህን ከየት መጀመር እንዳለብህ ትረዳለህ። 
  3. አማራ ዛሬ ላይ ለሚፈፀምበት የዘር ማጥፋት ወንጀል የበቃው ብአዴን ከተመሰረተበት 1987 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት ድረስ በያዘው የጸረ አማራነት ፍጥረቱ ነው። ከስር መሰረቱ ካልተወገደ ብአዴን ወደፊትም ንፁህ አማራ ፋኖዎችን፣ አርበኞችን፣ ቆራጥ አመራሮችን፣ ቆራጥ ወጣቶችን እየረሸነ፤ እያሰረና እያሳደደ አማራ መሪ እንዳይወጣለት በማድረግ እና ፋኖ መደምሰስ አለበት ብሎ ህግ በማውጥትና አስፈፃሚ በማዋቀር አማራ በሚኖርብት ሁሉ ጦር አዝምቶ ፋኖዎችንና ቆራጥ ወጣቶችን በመረሸን፣ በማሰር፣ በማሳደድና አጠቃላይ የፋኖን መዋቅር በመበተን አማራን ለማጥፋት የታወጀውን ጦርነት፣ ማፈናቀል፣ ማሰርና ማሳደድ እንዳይመክት በማድረግ አማራን አጥፍቶና አስጠፍቶ ታላቋን ትግራይና የገዳ ኦሮምኛ ኢትዮጵያን በማዋለድ መሆኑን በማወቅ አስፈላጊውን ሁሉ እንድታደርግ። 
  4. በጦር ሜዳ እየተዋደቃችሁ ለምትገኙ ፋኖዎች እና ንፁህ የአማራ ኃይሎች ሆይ፣ በአማራ ልዩ ኃይል በመከላከያ ሰራዊትና በፌደራል ፖሊስ የድንብ ልብሶችን በመልበስ ከሚፈፀም አታሎ መምታት ሴራ እራሳችሁን እንድትጠብቁ እያስጠነቀቅን የአማራ ልዩ ኃይል አማራዎች ተባረውና ታስረው በፀረ አማራ ተላላኪዎች እንደሚመራ፤ መከላከያና ፌደራል ፖሊስ ሙሉ በሙሉ በኦነግ እንድሚመራና አላማውም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አማራን እየጨፈጨፈ፣ እያስጨፈጨፈ ፋኖንና ቆራጥ አማራ የሆኑ የአማራ ልዩ ኃይል አባላትን በአጣዬና በተለያዩ ቦታዎች ጭምር ፋኖን እስከአሁንም እያሳደደ መሆኑ እንዳይዘነጋ እናስጠነቅቃለን። 
  5. የተከበርከው የአማራ ህዝብ ሆይ አማራን አጥፍቶ ኢትዮጵያን ለመበተን እንዲቻል በአማራ ላይ ጦርነት በማወጅና በተለያየ ሰበብ የሚደረገው የዘር ማጥፋት በዘላቂነት የሚቆመው የሞራል ውሳኔ በመወሰን የብአዴንን አመረሮችና የኮር አባሎች ከቀበሌ ጀምሮ መንቀልን ወደ ወረዳዎች በማሳደግ ከፌደራል ወደ ከልል፣ ከክልል ወደ ዞን፣ ከዞን ወደ ወረዳና ቀበሌ የሚወረደውን አማራን የማጥፋት ትዛዝን እና አማራን ሰልሎ ወደላይ የሚተላለፈውን መረጃ በመበጣጠስ የጎበዝ አለቃን በጥንቃቄ በመሾም፣ ወደ ፊት የመገስገስ አስፈላጊነት የህልውና ትግልህ መርህ ታደርግ ዘንድ ስናሳውቅ ብቸኛ የድል መንገዱም ይህ መሆኑን አስምረን ነው። 
  6. የተከበርከው የአማራ ሕዝብ ሆይ፣ ህልውናህን በማስከበር ለድል የሚያበቃህን የትግል መስመር የሆነውን ብአዴንን ከቀበሌ ጀምሮ እየነቀልህ የጎበዝ አለቃህን ለማስቀመጥ ጦርነት ማወጅ አያስፈልግህም። የሚያስፈልገው አማራ በሚኖርበት ሁሉ በህዝባዊ እምቢተኝነት ፆታንና እድሜን ሳይመርጥ በግልና በቡድን ማናቸውም አይነት ስልቶችና መንገዶች በመጠቀም በቀብሌው ተፅኖ ፈጣሪ አመራሮችን የሹም ጆሮ ተላላኪና አጨብጫቢዎችን ኢላማ በማድረግ አማራን ከሚያሰቃዩበት ሥልጣን እየነቀሉ ወደ ፊት መገስገስ ነው። 

በመጨረሻም የአያቶችህን ብሂል እያስታወስን ለጋራ የህልውና ትግልና ለጋራ ድል፤ መላው አማራ በያለበት የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ እንዲነሳ ጥሪ እናስተላልፋለን!!!  

ወገን ተጨፍጭፎ ሆነን አዘን ላይ፤ 

ቀያችን ተቃጥሎ ቆመን አመድ ላይ፤ 

ጦር ተዘምቶብን ሆነን ውጊያ ላይ፤ 

 ለዚህ ካበቁን ጋር አንድ ይኮናል ወይ። 

መስከረም 6 ቀን 2015 ዓ/ም 

ጋሻ አማራ

PDF VIEW

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator