በአብይ አህመድ ብልፅግናና በትህነጎች መካከል ሲደረግ የነበረው ፕሮፓጋንዳ በፀረ አማራነት እንደሚደመደም ቀድመን ለማስታወስ ወትውቼ ነበር።ከእንደገና ይነበብ!!!

ጦርነት እና ሰላም

የሰለም መኖር በጦርነት ይታወቃል።የጦርነትም መኖር በሰላም ይታወቃል።የብርሃን መኖር በጨለማ መኖር እንደሚታወቀው ሁሉ ማለት ነው።የሰው ልጆች ከስጋት ነፃ ሆነው መኖርን ስለሚመርጡ የሚመጣባቸውን ጠላት በጦርነት ድል የማድረግ ግዴታ አለባቸው።

ከሰሞኑ የጦርነት ፕሮፓጋንዳ በማዕከላዊ መንግስት ሰዎች እና በትህነግ ሰዎች ሲነገር እየሰማሁኝ ነው።ትግሬ ክልል ራስ ገዝ በመሆን የሀገረ መንግስት ምሥረታ ልምምድ ላይ ነኝ በማለት በአደባባይ እየተናገረች ነው። የማዕከላዊ መንግስት ባለስልጣናት ደግሞ የሀገር ሉአላዊነት እና አንድነትን ማስከበር በሚል የትህነግ ሰዎች በትግሬ ክልል እያደረጉ ያሉትን የራስ ገዝ ልምምድ ለማስቆም እየተናገሩ ነው።በእርግጥ በሁለቱም በኩል ፕሮፓጋንዳው መነዛት ከጀመረ ሁለት ዓመት ሞልቶታል። በዚህ ፕሮፓጋንዳ ምክኒያት ማዕከላዊ መንግስቱ ትግሬ ጠል በአንፃሩ የሌዎቹ ብሔሮች ከለላ ተደርጎ እንዲሳል እየተደረገ ነው።እውነታው ግን ሌላ ነው።በትህነግ ጊዜ የነበረውም አሁንም ያለው ማዕከላዊ መንግስት ህዝብ ጠል መሆኑ ነው። በተለይም በአማራ ጠልነት ሁለቱም ተመሳሳይ ይዘትና አመለካከት እንዳላቸው መገንዘብ ያሻል።

የአማራ ህዝብ ለጦርነት እና በጦርነት ድል በማድረግ አዲስ አይደለም።ሀገር ተወረረች ድንብር ተደፈረ በተባለ ቁጥር ፈጥኖ በመድረስ በነፍጠኝነት ጥበቡ ሀገር ያስከበረ የድል ታሪክ ባለቤት ነው። አሁን ነገሮች ተቀይረዋል።ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ለአማራው ከፈረሰች ሦስት አስርት ዓመታት ተቆጥረዋል። አሁን በምንገኝባት ኢትዮጵያ ሀገር ተወረረች ድንበር ተደፈረ ጥሪ አማራው ቀድሞ አቤት ማለት አይችልም መሆንም የለበትም።

የአማራ ህዝብ የሚሰለፈው ብቸኛ ጦርነት ለራሱ እኩልነት ፍትህ ነፃነት መከበር ብሎም ባለሀገርና ባለመንግስት ለመሆን ብቻ ነው።አማራው መሰለፍ ያለበት ጦርነት ራሱ የሚመራው መሆን አለበት። የጦርነቱን ሜዳ፡የጦርነቱን ሰዓት ብሎም ከየትኛው ጠላት መቼና የት የሚለውን መምረጥና ጦርነቱን የሚጀምረው ራሱ አማራው ለራሱ ዓላማዎች ይሆናል።ከዚያ ውጭ በሌላ ጄኔራል እና ለሌላ ዓላማ በሚደረግ ጦርነት የዳግማዊ ባድመ አይነት ትርኢት የሚኖር ከሆነ ትርኢቱን ያይ እንደሆን እንጂ ተዋናይ መሆን አይችልም።

ጦርነትን በሚመለከት አማራው በተለየ ሁኔታ ተጎጂ እንደሚሆን አድርገን በመሳል ቀድመን የምንጮኸው ጉዳይም ትክክል አይመስለኝም።መሆን ያለበት እንደ አፄ ምኒልክ ሁሉ ሊመጣ ያለውን በማሰብ በቂ ዝግጅት እያደረጉ መቆየት ነው።በጦርነት ማሸነፍ የሚቻለው ከዝግጅት እስከ የጦር ሜዳ ውጊያ ያሉ ታሳቢ አስፈላጊዎችን ሁሉ ማሟላት ሲቻል ነው።

አሸንፎ የገባ ያሸንፋል!!!

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator