አምሐራ ሳይንት የአማራ ህዝብ መነሻ እና የአማርኛ ቋንቋ መነሻ የሆነ የብዙ ድንቅ ነገር መገኛ ታሪካዊ ባህላዊ የእምነት የጀግና የቁንጅና መነሻ ቦታ ነው አምሐራ ሳይንት ቃላዊ ትርጉም
አምሐራ የሚለው ስያሜ ከጥንት ጀምሮ የነበረ ሲሆን ‹‹ አም›› ማለት ህዝብ ሲሆን ‹‹ ሐራ›› ማለት ደግሞ ነጻ፣ ከፍታ / ተራራ ማለት ነው፡፡

‹‹ ዐምሐራ ›› ማለት በግዕዝም በሂብሩም ቋንቋ ትርጉሙ ይህ ነው፡፡

በጥብቅ ነጻ የወጣ ህዝብ ወደ ከፍታ የወጣ ህዝብ እንደ ማለት ነው፡፡ አለቃ ታየ ‹‹ አማሀራ / አማራ/ ›› የሚለውን አራሽ የሚል ትርጉም ሰጥተውታል፡፡

ዶ/ ር ሀብተ ማርያ አሰፋ ‹‹ ዐምሐራ ›› ን በተለያየ ትርጉም ተርጉመውታል ዛሬም ከቀበሌ እስከ ወረዳ ከወረዳ እስከ ዞን ከዞን ክልል እስከ አገር አቀፍ ደረጃ የክልላችን መገናኛ ብዙሀን ጨምሮ በአማርኛ ‹‹ አማራ ›› በእንግሊዘኛ ‹‹ ዐምሐራ ፣AMHARA: በማለት ይጽፋሉ ይናገራሉ፡፡

ይህን ስም ሳያጠፉ ዐምሐራ ›› ሳይንት ብለው የሚጠሩትና የሚጸፍ ትንሽ ሰዎች ናቸው ትክክለኛ መጠሪያውም ይሄው አምሐራ የሚለው ነው ፡፡

‹‹ ዐምሐራ – ስመ ነገድ ፣ ጨዋ ወታደር
ዐም-ወገን ፣ነገድ፣ህዝብ ሐራ-ጨዋ ፣ወታር ›› ማለት ነው ብለው ሊቀ ህሩያን በላይ መኮነን በህያው ልሳን ግዕዝ አማርኛ መዝገበ ቃላት ሶስተኛ እትም ላይ ተርጉመውታል፡፡

ሳይንት / ሳይንት ማለት በእንግሊዘኛ ቅዱስ፣ ጻድቅ ፣ የተባረከ ሰው፣ትዕግዝተኛና ራስ ወዳድ ያልሆነ ሰው ማለት ሲሆን ለቦታ ደግሞ የቅዱሳን ቦታ የቅዱሳን ሀገር ማለትነው፡፡/ ኦክስፎርድ ዲሽክረኒ፣/፡፡

ሳይንት የሚለውን ስም ያወጡት አቡነ ተክለሀይማኖት ናቸው ፡፡ በማለት መሪጌታ መሰረት ለማ ይናገራሉ፡፡ ሳይንት ማለት በአረበኛ የእህል ማከማቻ ጎተራ ማለት ነው ፡፡

አንዳንድ ሰዎች አረቦች በአካባቢው እንደነበሩ ይናገራሉ፡፡ በጥቅሉ አምሐራ ሳይንት ማለት ነጻ የወጣ ቅዱስ ህዝብ ማለት ነው።

አምሐራ-ሳይንት በደቡብ ወሎ ከደሴ ከተማ 200 ኪ.ሜ ርቀት ያላት እምቅ የታሪክ የፓለቲካ የተፈጥሮ ሀብት ያለው ሚስጥራዊ ቦታ ነው።

ከሰሜን ደቡብ ጎንደር/በሽሎ\ከደቡብ መካነ ሰላም ወረዳ ከምስራቅ ተንታ አጅባር ወረዳ ከምእራብ ጎጃም/አባይ\ የሚያዋስኗት በዉስጧ ሁለት ሰፋፊ ወረዳወችን የያዘ ነው።

በወረዳው በርካታ ቅርስ የሚገኝ ሲሆን ዋነኛው
ታሪካዊዋ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም ከአራቱ መናብርት ጽዮን ማለትም ከአክሱም ጽዮን ንቡረ ዕድ፣ከመርጡለ ማርያም ርዕሰ ርዑሳን፣ከጣና ቂርቆስ ሊቀ ካህናት መካከል አንዷ የፓትርያርክ መቀመጫ ነበረች።

ጥንታዊት ርእሰ አድባራት ወገዳማት ተደባበ ማርያም በ982 ዓ.ዓ የተመሰረተች ሲሆን መስራቹ ደግሞ የቤተልሔም ተወላጅ የአሚናዳብ ዘር የሆነው ሳቤቅ ይባላል
በተድበማርያም ውድ ቅርሶች ያሉ ሲሆን ከነዚህ መካከል፦

1.ዐፄ ካሌብ ወደ ደቡብ አረቢያ የናግራንን (የመን) ክርስቲያኖች ለመርዳት ይዘውት የዘመቱት ጋሻ፣

2.የእብራይጥ ሲኖዶስና የአረማይክ ቅዳሴ እግዚእ፣

3.በአረማክ ቋንቋ የተጻፉ የስሌዳ መጻህፍት፣

4.በአረበኛና በግእዝ የተጻፉ መጻህፍት ወንጌል ዘወርቅ፣

5.የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ጳጳስ የቀደሰበት የእጅ መስቀል፣

6.የዕጨጊ ዮሐንስ በትረ ሆሳዕና፣የአቡነ አኖሪዎስ እና የአቡነ ቄርሎስ የእጅ መስቀል፣

7.የዐፄ ገላውዴዎስ መካነ መቃብር፣

8.የአጼ ዳዊት ዙፋን፣

16 የቅዱስ የሬድ ድጓ እና ጊዩርጊስ ወልደ አሚድ፣ ገድለ አዳም እንዲሁም ከ1,000 የሚበልጡ ጥንታዊ የብራና መጻህፍት፣ስእልና ስነ ጥበባዊ ቅርሶች፣ በርካታ ጥንታዊ የእጅና የመጾር መስቀል፣ንዋየ ቅድሳት፣ስዕሎች፣የነገስታት ዘውዶች፣ወንበርና አልባሳት ይገኛሉ።

በኋላም የሁለተኛው ሰሎሞናዊ ሰርዎ መንግሥት ነገሥታቶች አፄ ገላውደወስን ጨምሮ አፄ ዘርአያእቆብ፣ አፄ በዕደማርያም፣ አፄ እስክንድርና ሌሎች ነገስታት ልብሰ መንግስታቸውን ለተድባበ ማርያም አበርክተዋል።

ምንጭ_ወሎ ቤተ አምሐራ – Wello Bete Amhara የልማት እና የበጎ አድራጎት ድርጅት

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator