ራሱን የአማራ ክልል ፀጥታ ምክር ቤት ብሎ የሚጠራው እና በየትኛውም የክልሉ እና የፌደራል ህግጋት የማይታወቀው ህገ-ወጥ ቡድን በዘመነ ካሴ ላይ ያሰማራው እና ዘመነን መያዝ ያልቻለዉ ሰራዊት የእናቱን ቤት በጥይት ደብድቧል። መፅሀፍትን ጨምሮ ያግፕኘውን ቁሳቁስ ተሸክሞ ወስዷል።
በንፁሁ ልጃቸው ላይ እሩምታ ተኩስ ሲከፈት በአይናቸው ያዩት እናት ንቦቻቸውን አስማርተው አፋኙን አዋክበውታል።
ከተኩስ ልውውጡ በኋላ አፋኙ እንደ ምርኮኛ የያዛቸው የዘሜ ወላጅ እናት የሆኑት የ80 ዓመት መነኩሴ እማሆይ የኔአለሽ ሙጨ ለማዳበሪያ መግዣ ያጠራቀሙትን ብር 6000.00 ከመቀነታቸው በሰራዊቱ አባላት።
በየ ቦታው ተመሳሳይ ድርጊቶች እንደሚኖሩ ይገመታል። በርግጥ የብአዴን ሰወች ድሮዉንም ኃላፊነት አይሰማቸውም፥ ከሰሞኑ ግን ለይቶላቸው ያበዱ ይመስላሉ። ከሁሉም የሚገርመኝ ግን ለስንት ብሔራዊ ጉዳይ “የምንተማመንባቸው” ጀነራሎች የዚህ አሳፋሪ ታሪክ አካል መሆናቸው ነው።
የተጀመረው የእብደት አካሄድ ቆሞ ህዝቡ ሰላሙን ያገኝ ዘንድ ሁሉም በየፊናው የሚችለውን ይወጣ!!!
ሕዝብን ማሸነፍ አይቻልም!!
Via አስረስ ማረ ዳምጤ
“ቤት ንብረታችንን አውድመው የ85 ዓመት እናታችንን አንገላተዋል” የዘመነ ካሴ ወንድም ፋኖ ንብረት ካሴ!!
የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) ሰብሳቢ የሆነውን አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን ለማጥቃት ከሰሞኑ ወደ ምዕራብ ጎጃም፤ ሰሜን ሜጫ ወረዳ፤ መርዓዊና በአካባቢ ባሉ ጫካዎች የተሰማራው የአገዛዙ ሰራዊት በዘመነ ካሴ ቤተሰቦች ብሎም በመርዓዊ ንፁሃን ኗሪዎች ላይ በርካታ ግፎችን እንደተፈፀመ ተዘገበ።
የአርበኛ ዘመነ ወንድም ፋኖ ንብረቱ ካሴ ለኢትዮ 360 ሚዲያ እንዳረጋገጠው፣ በዚሁ ጥቃት ከሕዝብ ወገን 4 ሰዎች በጥይት ተመተዋል። ከእነዚህ መካከል 3ቱ ተሰውተዋል፤ አንዱ በከፍተኛ ደረጃ ቆስሎ በሕክምና ላይ ናቸዉ። ወታደሮቹ ስናይፐር፣ ብሬን እና መትረየስ የታጠቁ ናቸው።
“የዘመነ ካሴ የ85 ዓመት እናት ቤት በከባድ መሳሪያ ተደብድቦ፣ ከመቀነቷ የቋጠሩትን ገንዘብ ወስደውባቸዋል” ብሏል ፋኖ ንብረቱ።
የአካቢቢው ኗሪ በየቤቱ ፋኖዎችን አሳልፎ ላለመስጠት አፋኙን ቡድን ተዋግቷል። በተለይም ከአጎራባቹ ይልማና ዴንሳ ወረዳ በፍጥነት የደረሱ ፋኖዎችና ሌሎች ኗሪዎች በርካቶች እንዲነሱ ምክንያት ሆነዋል።