ከወልዲያ ወደ ቆቦ የሚወስደው የአልወሃ ድልድይ በአሸባሪው ህወሃት ፈርሷል።
አሸባሪው ህወሓት በገባባቸው አካባቢዎች ሁሉ መሰረተ ልማቶችንና የህዝብ መገልገያዎችን መዝረፍና ማውደም ዋነኛ ዓላማው አድርጎ ተንቀሳቅሷል።
የሽብር ቡድኑ አሁን ላይ በፀጥታ ሃይሎች የጋራ ክንድ እየደረሰበት ያለውን ከፍተኛ ምት መቋቋም ባለመቻሉ በሽሽትም ላይ ሆኖ መሰረተ ልማቶችን እያወደመ ይገኛል።
ከትናንት በፊት በሀይቅና ውጫሌ ከተሞች መካከል ያለውን ድልድይ አፍርሶ ከፈረጠጠ በኋላ ዛሬ ሌሊት ደግሞ በጣሊያን ጊዜ የተሰራውን ጥንታዊውን የአልዉሃ ድልድይ አፍርሶ መሸሹን ኢዜአ ዘግቧል።
የሽብር ቡድኑ ይሄንን ውድመት ያደረሰው የመሰረተ ልማት አውታሮችና ተቋማትን የማፍረስ እኩይ ዓላማውን ለማሳካት እንዲሁም ከጸጥታ ሃይሉ የፈጣን እንቅስቃሴ ጥቃት ለመትረፍ በማሰብ መሆኑ ታውቋል።