ከአውሮጳ የዐማራ ማኅበራት ፌዴሬሽን የተሰጠ የአቋም መግለጫ
መፍትሔው መደራጀትና መታገል ብቻ ነው!!
አማራ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለእናት አገሩ ደሙን ያፈሰሰና አጥንቱን የከሰከሰ ማኅበረሰብ ነው። በአማራነቱ የበላይነትም ሆነ የበታችኝነት ስሜት የሌለው እና ሰውን በስብዕናው እንጂ በዘሩ የማይለካ በመሆኑ ከሁሉም ጋር ተዋልዶና ተቀላቅሎ አገሬ ባላት የኢትዮጵያ ክፍል ሁሉ ተሰባጥሮ ይኖራል። የአማራ ሕዝብ ለዘመናት በሚኖርባቸው አካባቢዎች ሁሉ ማህበረሰቡን መስሎ ባህልና ወጋቸውን አክብሮና ተጋርቶ የሚኖር እንጂ የዘር ፍጅት የከፈቱበት ጠላቶቹ እንደሚያስወሩት የራሱን ባህልና ቋንቋ አስገድዶ የጫነ ማህበረስብ አይደለም። ሀቁ ይህ ሆኖ እያለ የኦሮሞና የትግሬ ጽንፈኞች አማራው ያልፈጸመውንና የማይመለከተውን የሀሰት ትርክት እየፈጠሩ የጥላቻ ጡጦ እያጠቡ ባሳደጓቸው መንጋዎች የዘር ማጽዳትና ማጥፋት ወንጀል እየፈጸሙበት ይገኛሉ። ዐማራዉን እና የኢትዮጵያ መሰረት የሆኑትን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እና ነባር የእስልምና ሃይማኖቶቹን በማጥፋት ትንንሽ አገራትን ለመመስረት የሚፈልጉት እነዚህ ፅንፈኛ ቡድኖች ዐማራዉን በመግደልና በማፈናቀል እንዲሁም የተለያዩ ዉስጣዊ አጀንዳዎችን በመፍጠር ዐማራዉን እረፍት አልባ ለማድረግ ተናበው በመተግበር ላይ ናቸው። በተለይም የኦሮሙማዉ ፋሽስት አገዛዝ ኦሮሚያ ከሚባለዉ ክልላቸው የሚያካሂዱትን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ተግባር አልበቃ ብሏቸው በኦሮሙማዉ ፋሽስት አብይ አህመድ ትዕዛዝ የኦነግን ልዩ ኃይል የአገር መከላከያ ሰራዊትን ዩኒፎርም አልብሰው በማዝመት ዐማራውን ከቀየው የማጥፋት ተግባራቸዉን በማስፋት ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም የኦሮሞ እና የትግሬ ጽንፈኛ ስብስቦች የአገሪቱን የስልጣን መሪነት ከመጨበጣቸዉ በፊትም ሆነ ከጨበጡ በኋላ በስዉርና በግልፅ እያካሄዱት ባለዉ ዐማራን የማዳከምና የማጥፋት ተግባር ከግማሽ በላይ ግባቸዉን እያሳኩት ይገኛሉ።
ይህ ሁሉ ተግባር እየተፈፀመ በዐይኑ እያዬ ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ እኔ ኢትዮጵያዊ እንጂ ዐማራ አይደለሁም እና ሌሎችን ምክንያቶችን የሚደረድር ዐማራ አውቆም ይሁን ሳያውቅ ለአጥፊዎቹ አጋዥ ኃይል እንደሆነ ሊያዉቀዉ ይገባል። ስለሆነም ማንኛውም የዐማራ ተወላጅ ከዶሮና ከዕንቁላል ማን ይቀድማል ከሚል የጅል ክርክር እና ንትርክ ተላቆ በዐማራነቱ የተከፈተበትን የህልውና አደጋ ለመመከት ቆርጦ መነሳት ይኖርበታል። የዘገየም ቢሆን ዐማራውም አሁን የተደቀነበትን የህልዉና አደጋ ሸሽቶ ማምለጫ መንገድ እንደለሌው በመረዳት የሞት ሽረት ትግሉን ጀምሮታል።
በዓለም ላይ የምንገኝ የዐማራ ተወላጆችም በምንኖርበት ሀገር ያቋቋምናቸውን የዐማራ ማኅበራት አንድ ላይ በማምጣት በአገር፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ ወጥ የሆነ አደረጃጀት እንዲኖረን እየሰራን እንገኛለን። በመሆኑም በአውሮጳ የምንገኝ የዐማራ ማኅበራት በተናጠል ስናደርግ የነበረውን ድጋፍ አቀናጅተን ችግሩን በሚመጥን ደረጃ ተደራሽ እንዲሆን ስንመክር እና ቅድመ ዝግጅት ስናደርግ ቆይተን እነሆ ዘሬ 10 የዐማራ ማኅበራት የተሳተፉበት መስራች ጉባዔ አካሂደን የመተዳደሪያ ደንቡን በማጽደቅ በአውሮጳ የዐማራ ማኅበራት ፌዴሬሽን መስርተናል።
በመጨረሻም በአውሮጳ የዐማራ ማኅበራት ፌዴሬሽን የመስራች ጉባዔውን ምክንያት በማድረግ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የሚከተሉትን ጥሪዎች ያቀርባል።

  1. በዘር ፍጅቱ ሰለባ ለሆነውና ህልውና ትግሉን በማካሄድ ላይ ለሚገኘው የዐማራ ሕዝብ
    ሀ) ለወዳጅህ አልጋ ለጠላት ቀጋ የሆንከው ጀግናው የዐማራ ሕዝብ በፋሺስቱ የአብይ አህመድ ኦነግ መራሹ አገዛዝ የታወጀብህን ሁሉን አቀፍ የዘር ማጥፋት የህልወና ጦርነት ከአያት ቅድመ አያቶችህ በወረስከው ወኔ እና ጀግንነት ለአይበገሬዎቹ አርበኛ ልጆችህ ምሽግ፣ ስንቅና ትጥቅ በመሆን የምትከፍለውን መስዋዕትነት እያደነቅን እኛም ልጆችህ ሁሉን አቀፍ ድጋፋችንን ለማድረግ ዝግጁ መሆናችንን ለማብሰር እንወዳለን።

ለ) የንቀታቸው ንቀት የጀመርከውን የአልሞት ባይ የህልውና ተጋድሎ ማንነትህን በውል ያልተረዱ በጉልበት ትጥቅ ብቻ ሳይሆን ሱሪህን ጭምር ለማስፈታት ፎክረው የዘመቱብህን የባንዳ ስብስብ የውስጥ ሱሪውን ሳይቀር በማስወለቅህ ኮርተንብኃል፤ የግል አገልጋያቸውን (ግርማ የሺጥላን) ጭምር ራሳቸዉ በመግደል በሴራ እርስ በርስ ሊያፋጁህ ሞከሩ የሞኝ ለቅሶ አደረክባቸው፤ ፋሺስቱ የአብይ አህመድ አገዛዝ በሽምግልና፣ በውይይትና በእርቅ ስም የነጻነት ትግልህን ለማሰናከል የሚያቀርበውን ማጭበርበሪያ ካለፈው በመማር አለመቀበላችሁን እናደንቃለን፤
ሐ) ደካማ ጎንህን እናውቃለን ባይ ጠላቶችህ ኢትዮጵያ ተደፈረች፣ ወደብ እናስመልሳለን እና የሽግግር መንግሥት ያስፈልጋል የሚሉ የማታለያ የጅል ለቅሶ ጀምረዋልና ከድል በመለስ በላቸዉ፤
መ) ከተጨባጭ ሁኔታዎች ውስብስብነት የተነሳ ትግሉን ሙሉ በሙሉ በአንድ እዝና ማዕከል መምራቱ አስቸጋሪ ቢሆንም የአካባቢውን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገ እና የተናበበ ተጋድሎ ለማንም የውጭ ወዳጅም ሆነ ጠላት ጣልቃ ገብነት እድል ሳትሰጡ ተጋድሏችሁን በጀመራችሁት ትብብር እንድትቀጥሉ አደራ እንላለን፤
ሠ) ፋሺስቱ የአብይ አህመድ አገዛዝ ወቅት እየጠበቀ እንዳታርስ፣ ምርት እንዳትሰበስብ እና ማዳበሪያ ጭምር በመከልከል እንድትራብ፣ አቅመቢስ ደካማ አድርጎህ አጽመ እርስትህን ነጥቆ የለለ ሀገር ለመመስረት የሚያደርገውን ወረራ ሚስማር ሲመቱት ያጠነክራል እንዲሉ ልጆችህን ላለማስነካት ቀፎው እንደተነካ ንብ የምታደርገው ጠንካራ ተጋድሎ አማራጭ የለሽ የአልሞት ባይ ተጋዳይነት የአባቶችህ ልጅ መሆንክን ያስመሰከርክበት በመሆኑ ኮርተንብሀል፤

  1. በርህ እስከሚንኳኳ ለምትጠብቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ
    የኦሮሞና የትግራይ ጽንፈኛ ስብስቦች ሕዝባዊም ሆነ ኢትዮጵያዊ ዓላማና ግብ የላቸውም። ጸረ ኢትዮጵያ በመሆናቸው ታሪኳንና ቅርሶቿን በማውደም ላይ ይገኛሉ። ጸረ ሕዝብ በመሆናቸው ደግሞ የሕዝቡን አንድነት፣ ባህል፣ እምነት እና ትውፊት ያጠፋሉ። ዓላማና ግባቸው ታሪካዊት ኢትዮጵያን ከዓለም ካርታ ፍቀው ኦሮሚያና ትግራይ የሚባሉ ታሪክ አልባ ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች የጸዱ አገራትን መፍጠር ነው። ለተግባራዊነቱ የኦሮሚያ ክልልን እና አዲስ አበባን ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች በማጽዳት ላይ ሲሆኑ የመሬት ወረራው ያልነካው አንድም ክልል የለም። ስለሆነም ተራ በተራ ከምታልቅ ከአማራ ወገንህ ጎን ተሰልፈህ ለመታገል ቆርጥህ ተነሳ፤ ከታሪክ እንደምንማራው ፋሺስቶች ካልተወገዱ ፋሺዝም ስለማይቆም እነኚህን ጥቁር ፋሺስቶች ለአንዴና ለመጨራሻ ጊዜ ለማስወገድ መፍትሔው መደራጀት እና መታገል በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከዐማራ ወገኑ ጎን በመሰለፍ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪያችንን እናቀርባለን፤
  2. ለኦሮሞ እና ለትግራይ ሕዝብ
    የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ፦ ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ ነውና ከአብራክህ የወጡ ልጆችህ በስምህ እየማሉና እየተገዘቱ ከኢትዮጵያዊ ወገንህ ደም እያቃቡህ መሆኑን ተገንዝበህ ዝምታህን በመስበር በገሀድ ወጥተህ በቃ ልትል ይገባል። ልጆችህ የሚገሉት በጎሳ ቅልቅል ከሆንክ፣ በእምነት ከእነርሱ ከተለየህ እና ቋንቋውን ካልቻልክ ኦሮሞም ብትሆን አይምሩህምና በቃ በስሜ አትነግዱ ልትል እና ልትታገላቸው ይገባል።
    የትግራይ ሕዝብ ሆይ፦ ብልህ ከሰው ስህተት ይማራል ጅል ግን ከራሱም ስህተት አይማር እንዲሉ በትግሉ ወቅት በስምህ በሺዎች የሚቆጠሩ ልጆችህን አስፈጅተው የሚፈልጉትን ስልጣን ካገኙ በኋላም ለ27 ዓመታት የኢትዮጵያን ሕዝብ በስምህ ረግጠው ገዙት፤ ከሥልጣን ሲገፉ ዳግም ልጆችህን አስፈጁ አሁን ደግሞ የተረፉትን ለማስፈጀት የጦርነት ነጋሪት እይጎሰሙ ይገኛሉ። ታሪክ ተረካቢ ትውልድ እንዳይኖር አድረግው ወደ መቃብር ሊወርዱ ሲዘጋጁ እያየህ ዝምታህ ድጋፍ ካልሆነ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልምና ምርጫህን ማስተካከሉ ቢያንስ ከታሪክ ተጠያቂነት ያድንኃልና እንድታስብበት ጥሪ እናቀርባለን።
  1. ከሀገር ውጭ ለሚኖረዉ የዐማራ ተወላጅ
    በአሁኑ ሰዓት ዐማራዉ ወገንህ ህልውናውን ለመታደግ ክቡር ህይወቱን እየገበረ ባለበት ወቅትና ለወሳኙ ድል ለመብቃት ወገንህ እየተዋደቀበት ባለበት ሁኔታ ለቅሶና ዋይታ ስለማይጠቅም በዓለም ዙሪያ የምትኖሩ ዐማራዎች በየአካባቢያችሁ በተቋቋሙ የፌደሬሽኑ የዐማራ ማኅበራት ስር በአባልነት በመታቀፍ ለህልዉናዉ ትግል የበኩላችሁን አስተዋፆ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
  2. ለአገር መከላከያ ሰራዊት
    ለአገራቺሁ ሉዐላዊነት እና ለሕዝባችሁ ደህንነት መከበር ህይወታችሁን ሳይቀር አሳልፎ ለመስጠት ቃለ መሀላ በመስጠት የተቀበላችሁትን አደራ እንዳትወጡ ለማድረግ ፋሺስቱ አብይ አህመድ በዐማራው ወገናችሁ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንድትፈጽሙ እና በህግም ሆነ በታሪክ ተጠያቂ እንድትሆኑ እያደረገ መሆኑን ተገንዝባችሁ አሰላለፋችሁን ከዐማራው ወገናችሁ ጋር በማድረግ ዘረኛው የኦሮሙማ ፋሽስት አገዛዝ ሀገርና ሕዝብን ከማፈራረሱ በፊት እንዲወገድ በሚደረገው ተጋድሎ የድርሻችሁን እንድትወጡ ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን።
  3. ለብአዴን (የዐማራ ብልጽግና) ሹማምንት
    የዐማራ ሕዝብ ከወገንህ ጎን እንድትቆም ከበቂ በላይ ጊዜ ስጥቶሀል፣ ታግሶሀል፣ መክሮሀል ዘክሮሀልም ነገር ግን አሻፈረኝ በማለትህ መከራ ሊመክርህ ከበርህ ቆሟል። መቼም ሳታጎነብስ ጫንቃህ ላይ ወጥቶ የሚፈናጠጥ ደፋር አይኖርምና ሚናህን እንድትለይ የመጨረሻ ዕድል ተሰጥቶኃልና አጋጣሚውን እንድትጠቀም ይሁን። የኦሮሙማዉ ፋሽስት አገዛዝ ተጠቅሞ እንደሚወረውርህ ከአቶ ግርማ የሺጥላ ልትማር ይገባል። በአሁኑ ሰዓት በፈቃዳችሁ ስልጣን የመልቀቅ እርምጃ እየወሰዳችሁ የምትገኙ አመራሮች ቢያንስ የበደላችሁትን ሕዝብ ለመካስ እድል እንዲሰጣችሁ ትግሉን በመቀላቀል የበኩላችሁን አስተዋፆ እንድትወጡ እንጠይቃለን።የብልጽግና ካድሬ ያልሆናችሁ ምሁራን ይህ የህልውና ትግል የሁሉንም ተሳትፎ ስለሚጠይቅ አንዱ ሞቶ ሌላው አጥር ተንጠልጥሎ ጠብቆ ስልጣን የሚይዝበት ወቅት ባለመሆኑ ሁሉም የአቅሙን ሊያበረክት ይገባል።
    በተባበረ ክንዳችን ፀረ-ዐማራ ዘረኞችን እና ዘረኝነትን እናጠፋለን!!
    ኅልዉናችን በትግላችን!!
    በአውሮጳ የዐማራ ማኅበራት ፌዴሬሽን

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator