ከባቦ ገምቤል ወረዳ ቦኒ ቀበሌ 8 የሰፈራ ጣቢያዎች ላይ በ1977 ዓ/ም ጫካ መንጥረው እንዲገቡና አካባቢውን እንዲያለሙ የተደረጉ ናቸው።

በጥቂቱ ላለፉት 38 ዓመታት ሀገሬ ብለው የኖሩበት፣ጫካ መንጥረው ሀብትና ንብረት ካፈሩበት፣ ከተዳሩበትና ከተኳሉበት ቀያቸው በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ የተፈናቀሉ ወገኖች ጥያቄ አልተመለሰም።

እነዚህ ወገኖች አሸባሪውና ወራሪው ኦነግ ሸኔ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ካሉ ተባባሪዎቻቸው ጋር በመተባበር መጋቢት 20 እና 21/2013 ዓ/ም በፈጸሙባቸው ጭፍጨፋ የ43 አማራዎችን አስከሬን አግኝተው ስርዓተ ቀብር መፈጸማቸው ይታወሳል።

ከ20 በላይ ቁስለኞች አሉ። የበለጠ እና የተደራጀ ምርመራ ግን የሚያደርግ አካል አልተገኘም።

ህዳር 8፣9 እስከ 12/2014 ደግሞ በተፈጸመው ዳግማዊ እና የመጨረሻው የዘመቻ ጥቃት ተፈጽሟል።

በምዕራብ ወለጋ ዞን ከባቦ ገምቤል ወረዳ ቦኒ ቀበሌ ከ8ቱ ሰፈራ ጣቢያዎች (ከ3 ልዩ የሰፈራ ጣቢያ ቀበሌዎች) ማለትም:_

1) ቦኒ ቀበሌ፣
2) ሙሚ ድልቢ እና
3) ሲርባ ኢጉ ባሉ አማራዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል።

በወረዳው ካሉት 21 ቀበሌዎች መካከል 3ቱ ልዩ የሰፈራ ጣቢያዎች ናቸው።

የ77ቱን ድርቅ ተከትሎ በደርግ ዘመን በመንግስት እንዲሰፍሩ የተደረጉ ናቸው። አብዛኛው ከወሎ አካባቢ የመጡ አማራዎች ናቸው። ጥቂት ቢሆኑም የትግራይ ተወላጆችም አሉበት።

ከህዳር 12/2014 ጀምሮ
በአሶሳ ዞን ባምባሲ ወረዳ 02 ቀበሌ ወርደ ቪዥን ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይገኛሉ።

ከጥር 5/2014 በኋላ በየወሩ በነፍስ ወከፍ ይሰጥ የነበረው 15 ኪሎ ስንዴ ለ3 ወራት ያክል ተቋርጦብናል ብለዋል።

የምግብ ዋስትናዎች ሲጠየቁ በመንገድ ላይ ሽፍቶች እየዘረፉን ስለሆነ ነው በሚል አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት እየደረሱልን አይደለም ሲሉ አማረዋል።

በአስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ እንዲደርሳቸው እየተማጸኑ ይገኛሉ።

በተመሳሳይ ከምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ተፈናቅለው ምንጃር አረርቲ ያሉ ተፈናቃዮችም ለ2 ወር ያህል እርዳታ ተቋርጦባቸዋል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator