የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ላይ የሚፈጽመው ግፍ ለከት እና ሀይባይ አጥቷል።

የጅምላ ግድያው፣ እገታ፣ ዝርፊያና ማፈናቀሉ ተጠናክሮ ከቀጠለባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ የምስራቅ ወለጋ ዞን ነው።

በመኪና፣ በእርሻ ማሳና በቤታቸው ጭምር የሚገኙ አማራዎችን በቀጥታ ከመግደሉ ባሻገር አግቶ ወደ ጫካ በመውሰድ በጭንቀት ላይ ካለ የታጋች ቤተሰብ በመቶ ሽህ የሚቆጠር ገንዘብ ከተቀበለ በኋላ መግደሉና አድራሻ ማጥፋቱ እየተለመደ መጥቷል።

እንደአብነት በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ መንደር 4 አካባቢ
ኦነግ ሸኔ የትሕነግ ካድሪዎችን በማስታጠቅ በመረጃ ልውውጡ፣ በግድያ፣በእገታና በማፈናቀሉ ረገድ አብረው እየሰሩ መሆኑ ይነገራል።

ህዳር 13 ቀን 2014 በጊዳ አያና መንደር 4 ፊትበቆ አካባቢ ጠብቀው አዝመራውን እንዳይሰበስብ ኦነግ ሸኔ እና ለጥፋት ያደራጃቸው አካላት እየሰሩ ነው ተብሏል፤ ከዛም አልፈው የአማራው አርሶ አደር ዓመቱን ሁሉ የደከመበትን አዝመራ እየጫኑ በመዝረፍ ላይ ናቸው።

የአንገር ጉትን ከተማ አስተዳደር “መከላከያ ከከተማ አይወጣም አቅም ካላችሁ አዝመራችሁን መሰብሰብ ትችላላችሁ” ማለታቸውን ተከትሎ
የተወሰኑ ገበሬዎች ወደ ፊትበቆ ሲሄዱ ተኩስ እንደተከፈተባቸው ተሰምቷል፤
አንድ ሰውም አግተው ወስደዋል።

በትንሹ በ8 ሄ/ር መሬት ላይ ያለን በቆሎ ባለቤቱ የአማራ መሆኑን በማረጋገጥ በመኪና ተጭኖ ወደ ፊትበቆ እየተወሰደ መሆኑ ተገልጧል።

የግፍ ግፍ ከተሰራባቸው ባለሃብቶች መካከል አንድ በሊሙ ወረዳ መንደር 6 የሚገኙ ባለሃብት ይጠቀሳሉ።

ህዳር መጀመሪያ አካባቢ 2014 ጽንፈኛ እና የተደራጁ ኦነጋዊያን መንደር 6 መግባታቸውን ተከትሎ ሸሽተው ከጥቃት ያመለጡ ከፍተኛ የእርሻ ልማት ያላቸውን አማራዎች አስር አስር ሽህ እየከፈላችሁ ግቡ ማለቱን እውነት ነው ብሎ በማመን አስር ሽህ ብር ከፍለው የገቡት ባለሃብት በጨካኙ ቡድን ታግተው ተወስደዋል።

የታጋች ቤተሰብም 100 ሽህ ብር እንዲከፍሉ ተጠይቋል፤ የተባሉትን ከመክፈላቸው ደግሞ 300 ሽህ ብር እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል፤ የተባሉትን ከፍለው እስካሁን የባለሃብቱን አድራሻ እንኳ አልተቻለም ተብሏል።

የሽብር ቡድኑ ጭካኔ የከፋ መሆኑን የገለጹት ምንጮች 410 ሽህ ብር ተቀብሎ እንኳ ያገተውን ሰው ለመልቀቅ አልቻለም ሲሉ ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል እየተፈጸመ ያለው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ፣ እገታ፣ማፈናቀልና ዝርፊያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እንጅ እየቀነሰ ሲመጣ አይስተዋልም።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator