0 0
Read Time:2 Minute, 20 Second
አቶ የሱፍ ኢብራሂም

አቶ የሱፍ ኢብራሂም በወቅታዊ ጉዳይ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል:_

በማህበራዊ ድረገፆች፣ በስልክና በፅሁፍ መልእክት መልካም የዒድ በዓል ለተመኛችሁልኝ ወንድምና እህቶቼ በሙሉ የከበረ ምስጋናየን ለማቅረብ እወዳለሁ።

በተቻለ መጠን ሰሞኑን በተፈጠሩት ችግሮች ዙሪያ ከዒድ በፊት ተጨማሪ ከመናገርና ከመፃፍ ይልቅ ጥናት በማድረግ የተደራጀ ሀሳብ ለማቅረብ ነበር የፈለግኩት።

ሆኖም የህዝባችንን እሴቶች ለማጉደፍ ዙሪያ ገባውን የሚደረገው ጥድፈትና ወከባ እጅግ ይዘገንናል።

ማንም እየተነሳ ማንነት ሊሰጠንና ሊነፍገን ሲፈልግ ተመለከትን።

የማንነት ጉዳይ በባለቤቱ እንጂ በጉጅሌ ጉባኤ የሚበየን አይደለም! ብይኑ የራሳችንና የራሳችን ብቻ ነው! የውጫዊና የጠላት ሙከራስ ይሁን፣ የለመደ ነው።

ሌላውንና በመካከላችን የታየውን ገመና ሌላ ጊዜ በዝርዝር እንመለስበታለን።

የሌላውን ወገን እምነት መጥላት፣ ምእመኑን ማዋከብና ማጥቃት እንዲሁም ተቋማቱን የማውደም ዝንባሌና እንቅስቃሴ በየትኛውም የኃይማኖት አስተምህሮ ተቀባይነት የሌለውና የተወገዘ ነው።

ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶችና ጊዜያት ፅንፍ የወጡ እንቅስቃሴዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ። የጥላቻ ብሄርተኝነትን ለማሸነፍ ስንታገል በኃይማኖት ጀርባ በሚፈፀሙ ሴራዎችና የፅንፈኛ ስምሪቶች ልንሸነፍ አይገባም።

በአሁኑ ጊዜ ድርሻቸው ቢለያይም የጥላቻ ብሄርተኞች፣ ሰርጎ ገቦች፣ ራስ-ጠልና ሆድ አደር ባንዳዎችና እውቀት አልቦ ፅንፈኞች የሰቆቃና ምስቅልቅል ምንጭ መሆናቸው አይካድም።

በሌላ በኩል ሰሞኑን በርካታ የአማራ ልጆች የመፍትሄ አካል ከመሆን ይልቅ የጠላት ቀጠና ውስጥ ዘው ብለው ሲገቡ አስተውለናል፣ ይህ ትክክል አይደለም!

በተለይ በየዕለቱ ቀጠና እያፈራረቁ እርስበርስ መነታረክ፣ የሆነን ክስተት ተከትሎ መንጎድ፣ ደመንፍሳዊ የሆነ ብሽሽቅ ውስጥ መግባት ከንቱነት ነው።

በነገራችን ላይ በመካከላችን ያሉት ፅንፈኞች አዲስ የተፈጠሩ አይደሉም። ቤተእምነቶችን እናፈርሳለን፣ ሽብር እንፈፅማለን እያሉ በቪዲዬና በኦዲዬ ሲገዘቱ ካልሰማን አናምንም ማለት ነው?

ጥፋተኞችን ማውገዝ፣ ማጋለጥና መቅጣት ይገባል። ፍትህ ወሳኝ ጉዳይ ነው፣ የግፍ ጥቃቶች ሰላባ ለሆኑት ሁሉ ተገቢ ፍትህና ካሳ መስጠት ይገባል። በዚህ ረገድ አንዳችንን የሚጎዳ ነገር የሁላችንንም ትኩረትና ትብብር ይጠይቃል።

ፅንፈኝነት የድንቁርና ውጤት እንጂ የማንም ኃይማኖት ወይም ማህበረሰብ ሞኖፖል ሊሆን አይችልም። በፅንፈኞች ምክንያት የሚኮነን ማህበረሰብም ይሁን ኃይማኖት አይኖርም!

በነገራችን ላይ የክርስትናና እስልምና ኃይማኖቶች ዘመናትን እና ዓለማትን የተሻገሩ ኃይማኖቶች ናቸው። በታሪክ የግዙፍ ጉልበትና የሰፋፊ ግዛት ባለቤቶች በነበሩ ኃይሎች ፉከራና ውርወራ ሳይሸነፉ እዚህ መድረሳቸውን መዘንጋት አይገባም።

አማኝነት የህዝባችን እሴት ነው። አማኝነት መልካም ነገር ነው። ምእመኑና ተቋማቱን መጠበቅ ይገባናል። በተለይ በተለይ አንዳችን የሌላችንን!

ባለፈው እኔ ሻሸመኔና አርሲ አካባቢ የነበረውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ “በአማራና በኦርቶዶክስ ላይ የተፈፀመ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው” የሚል ግልፅ አቋም ይዥ ከማናቸውም ፖለቲከኛም ይሁን ከቤተክርስቲያኗ አመራር በፊት ቀድሜ በየሚዲያው የሞገትኩበት ምክንያት—ክርስቲያን ስለሆንኩ አይደለም።

የሰብዓዊነት ስሜትና ያደኩበት በጎ ባህል ተፅእኖ ሊጠቀስ ቢችልም ዋናው ምክንያትም እሱ አይደለም። ዋናው ምክንያት በተለያዩ ሰበቦች ጀርባ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ሁሉ የጋራ መቋጠሪያ በህዝባችን ላይ የተያዘው ጥልቅ ጥላቻ መሆኑን ጠንቅቄ ስለምገነዘብ ነው።

ነገር ግን… “ለምን የአማራ ጉዳይ ሲሆን ይሄን ያክል ይጋነናል?” ማለት አንድ ነገር ሆኖ በተደጋጋሚ የታዘብነውን እውነታ በአዲስ መልክ ማመንዥክ መፍትሄ አያመጣም። በቃ ይታወቃል፣ 360 ድግሪ ተመልካችና ታዛቢ ያለበት ነው።

ችግሮች በሚፈጠሩበት ወቅት የኛን ትክክለኛ ሚና መለየትና መወጣት ያስፈልጋል።

የጠላት ጥንካሬ የኛ ድክመት ውጤት ብቻ ነው!

ግን ግን … የአማራ ህዝብ ያሳለፈውንና ያለበትን የማህበረ-ፖለቲካ ሁኔታ በትንሹም ቢሆን የሚገነዘብ የአማራ ተወላጅ ወገኑን ለማጥቃት በፍፁም እጁን እንደዋዛ ሊሰነዝር አይችልም!

በተለይ በዚህ ወቅት የኃይማኖት ፅንፈኝነት ውስጥ የሚገባ አማራ በራሱ ላይ የሚተኩስ ” ተላላ” ሰው ብቻ ነው።

ስለሆነም በወገኖቹ ላይ በጥፋት የሚሰማራ “የአማራ ተወላጅ” ከህዝባችን ስትራቴጂክ ጠላቶች ተርታ የሚመደብ ነው።

በመጨረሻ ማንም እየተነሳ ስለማንነታችን እንዲፈተፍት በር መክፈትም ይሁን መፍቀድ የለብንም!

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator