Community News

ሰፊ ክፍተት ስለአማራ ህዝብ

አያሌው መንበር

አሁን እያየውት ያለው ሰፊ ክፍተት ስለአማራ ህዝብ ጉዳይ በቂ መረጃ ከሌላቸው ሰዎች ውስጥ የሚዲያ ሰዎች ጭምር ናቸው።

ይህንን የምለው የማልጠብቃቸው ሰዎች ሁሉ ብዙ ስህተት ሲሰሩ ስለምመለለት ነው።

ለምሳሌ ሰሞኑን ስሜነህ የሚባለው ጋዜጠኛ ከዮሐንስ ቧያለው ጋር ሲወያይ የጠየቀው ጥያቄ በእጅጉ አስደንግጦኛል።

“የአማራ ህዝብ ቁጥር ምናምን የምትሉት እኮ ዝም ብላችሁ ተከታይ ለማፍራት እንጅ ትክክለኛ መረጃ መሆኑን የሚያሳይ የለም” ሲል ነው የጠየቀው።እውነት በጣም ደንግጫለው።

አቶ ዮሐንስም ጋዜጠኛውን መልሶ ጠይቆ አሸማቆት ነው ያለፈው።” ቢያንስ 2.4 ሚሊዮን ህዝብ በቅርቡ መንግስት አምኖ እንደተጨመረ አታውቅም ወይ?” ሲል ነው የመለሰለት።

በነገራችን ላይ የብአዴን ሰዎች ትንሽ ቆይተው መልካቸው እንደ እስስት ካልተቀያየረ ዮሐንስ ቧያለው ጥሩ አቋም ያለው ሰው ሁኖ አግኝቸዋለው።

ምናልባት ለመረጃ ሩቅ የሆናችሁ እና ግራ የምትጋቡ ጋዜጠኞች ካላችሁ ከብሄርተኞች ገፅ የኋላ ታሪክ እና የእለት ተዕለት ዘገባ ብትገቡ በቀላሉ ትረዱታላችሁ።ለእናንተም Mini research ነው።ሳትለፉ መረጃ ታገኙበታላችሁ።

በዚህ በስሜነህ ተገርሜ ሳላበቃ ዛሬ ደግሞ ፕሬስ ድርጅት ዘገባው ላይ በአንድ ግዙፍ ስብሰባ ተገኝቶ ነገር ግን ሌላ አስቂኝ የዜና ሊድ ይዞ ወጥቷል።
ይህ የሚያሳየው ጋዜጠኞቻችን የመረጃ ክፍተት እንዳለባቸው ነው።በግሌ ከተንኮል የመነጨ አድርጌ የምወስድባቸው አንዳንድ ጋዜጠኞች ቢኖሩም ብዙሃኑ ስለአማራ ህዝብ የተዛባ ወይም ቁንፅል ብቻ መረጃ ያለው ግን ከመረጃ ክፍተት ይመስለኛል።

እናም እዚህ ላይ ስራ መስራት ሳይኖርብን አይቀርም።
በነገራችን ላይ የዛሬ አራት አመት ስለአማራ ስፅፍ ቀድሞ በስድብ ያጥረገረገኝ የአማራ ጋዜጠኛ ነበር።
ሰውየው ዛሬም ሸለመጥማጥ ሁኖ ይሹለከለካል።ለውጥ የሚባለውም ያስተማረው አይመስለኝም።እነዚህን እየተውን ወጣቶችና ሌሎች ላይ ግን ከቀናነት ስራ መስራት ይጠይቃል።

እድለቢሶች ስለሆን እንጅ ለማወቅ ብንሻ እኮ በጣም ቀላል ነበር።ብዙ ስለአማራ የሚፅፉ ጋዜጠኛ ጓደኞች እያሏቸው መረጃ የሌላቸው ሰዎች ግን ይገርሙኛል።

የሆነው ሁኖ የጋዜጠኞች የብሄርተኝነት አብዮት መሰራት አለበት።እነ የሺሀሳብ አበራ ንጋቱ አስረስ Tesfaye Woldesilassie Yalelet Wondye እና ሌሎችን ብቻ በመከተል ስለአማራ ህዝብ ጉዳይ በቂ ትንተና ማግኘት ይቻላል።
ሳይቸግረን መረጃ አጠር አንሁን ለማለት ነው።

ይህ ትችት የማውቃችሁን እና ሁኔታው የማይፈቅድላችሁም አይመለከትም።

Translator