0 0
Read Time:1 Minute, 18 Second

ዛሬ በዋለው ችሎት በጋዜጠኛ መስከረም አበራ ላይ የ14 ቀን የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ ፖሊስ ከጠየቀባቸው ምክንያቶች ውስጥ ” መኖሪያ ቤቷን በምፈትሽበት ወቅት የውጪ ሃገር ገንዘብ አግኝተናል ፤ ገንዘቡ በብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የተገኘ መሆኑን እያጣራን እንገኛለን ” ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠን ፤ …
ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ ፦ ” የተከበረዉ ፍርድ ቤት ፖሊስ እንደ ዋና ምክንያት በማጋነን ያቀረበው ተገኘ የተባለው 2 ባለ 50 የኬንያ ሽልንግ ነው ፤ እሱን ባለቤቷ ኬንያ በሄዱበት ወቅት ይዘውት የመጡት ነው ። … ክብር ፍ/ቤት 2 ባለ 50 የኬንያ ሽልንግ እንደ ትልቅ ነገር እዚህ ይዞ መምጣት የዚህን ችሎት ክብር የሚመጥን አይደለም ። ….. ፖሊስ ብርበራ ያካሄደው ግንቦት 21 ቀን ነው ፣ 2 ባለ 50 የኬንያ ሽልንግ የተገኘው በዚሁ ቀን ነው የዚህ ውጤት ለማግኘት ያባለፈው ቀናት አልበቃ ብሎ እንዴት 14 ቀን ይጠየቃል ?! ” በማለት ጠበቃ ሰለሞን ለፖሊስ ምላሽ ሰጥቷል ።

 ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ "የተከበረዉ ፍርድ ቤት ፤ ጋዜጠኛ መስከረም ፖሊስ ጠርጥረን የያዝናት በሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት ነው ብሏል ።... ሆኖም ግን ፖሊስ ደንበኛዬን በእስር ቤት እያስጠራ

በተደጋጋሚ የሚጠቃቸውና የሚመረምረው ፍጽም ያልተገባ ነገር ነው። …. “የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ፊልድ ማርሻል ጀነራል ብርሃኑ ጁላ እና ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር አበባው ታደሰ ፣ በምትጽፊው ጽሁፍ ከፍተኛ የጦር ጄነራሎችንም አሳቅቀሻል የሚል ጥያቄ ነበር ሲቀርብላት የነበረው” ….

  ፖሊስ ይህን የመጠየቅ እና የመመርመር በሕግ የተሰጠው ስልጣን የለውም ፤ ጋዜጠኛ መስከረም አበራ በፃፈችው ጹሁፍ የተሳቀቀ አካል ካለ እራሱ አቤቱታ ያቀርባል እንጂ ፖሊስ አይመለከተውም ።... በእሷ ጽሁፍ "ተሳቀቅኩ” የሚል ሰው በሌለበት በዚህ ልትጠየቅ አይገባም ። ....
 በመስከረም ጽሁፍ እስካሁን ተሳቀቅን በማለት ክስም ሆነ አቤቱታ የቀረበ የለም ፤ ይህ በሆነበት ሁኔታ ፤ ፖሊስ በእስር ቤት ደንበኞዬን አስሮ ለማቆት ከመፈለግ ውጪ ጠረጠርኩ ለሚለው ወንጀል ምንም አይነት የምርመራ ሥራ እየሰራ አይደለም ...፤ 

ይህም በመሆኑ የተከበረዉ ፍርድ ቤት መስከረም በእስር የሚያስቆያት ምንም ነገር ስለሌለ የዋስትና መብቷ ይፈቅዳላት ” በማለት ፤ ጠበቃ ሔኖክ ለፍርድ ቤቱ አቤት ብሏል።

ዘገባው የይድነቃቸው ከበደ ነው

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator