Kefale Damtie
፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ሰሞኑን አንድ ስለኩርድ ህዝብ የምታወጋ ሸጋ መፅሐፍ እጄ ገባች። “A people without a state” የምትሰኝ በMichael Eppel የተፃፈች ስትሆን የኩርድን ህዝብ መከራና እንደቡድን ብሎም እንደሃገር ለመሆን ያደረጉት ተጋድሎና የከሸፈባቸው ምክንያቶችንም ለመጠቆም የቻለ ድንቅ ፅሑፍ ነው። ስለኩርድ ህዝብ እንዳነብ ያነሳሳኝ ብዙ ሰዎች የአማራ ህዝብ የኩርድ ህዝብ እጣ ፋንታ እንዳይደርሰው መደራጀትና የተበታተነው የአማራ ህዝብ ወደ አንድ መሰብሰብ አለበት። አሁን ተደራጅቶና ራሱን ካላስከበረና ካላከበረ በኋለኛው ዘመን የአማራ ህዝብ እጣ ኩርዳዊነት ይሆናል ከሚል እሳቤ ከዚያም ከዚህም ሲነሱ ነው። እየሆነም ያለው እየተጓተትን ኩርዳዊነትን እየናፈቅን የምንገኝ ስንቶቻችን ነን? ስንቶቻችንስ ስለአማራ መንግስትነት ስናነሳ ሀሳዊት ኢትዮጵያን እንደመደፍጠጫና እንገት መቅበሪያ አደረግናት?
በአሁኑ ዘመን ከ30 ሚልዮን የሚልቅ የኩርድ ህዝብ ተበታትኖ ይኖራል። በኤፍራጠስና ጤግረስ ወንዞችን ተከትሎ ለመጣው የሞስፐታሚያ ስልጣኔ ፈር ቀዳጅ ህዝቦች ናቸው። በኋላም በፐርሺያውያን ስልጣኔና እድገት ላይ ተፅኦኖ ማሳደር ችለዋል። በኋላ የመጣው የታላቁ የባዛንታይን ግዛት ማስፋፋት ጠቅልሎ ይዞ መፈናፈኛ አሳጥቷቸው ነበረ። ከእስልምና እምነት አብዮት በኋላ የተከሰተው ደግሞ ኩርዶች የእምነቱ ተቀባይ ብቻ ሳይሆን የአረቦች የትሮይ ፈረስ በመሆን የባዛንታይን ንጉሳዊ ግዛት ብትንትኑ እንዲወጣ አድርገዋል። አረቦችን ሲቀበሉ ግን እምነታቸውን ብቻ ሳይሆን ቋንቋቸውንና ባህላቸውን በእምነት ሰበብ አስታቀፏቸው። በኩርድነት ተሰባስበው ሲታገሉ በላያቸው የተጫኗቸው ሼኮች እስልምናን እንደመቃወም እንዲቆጥሩና እንዲሸማቀቁ ያደርጓቸው ነበረ። ከአረቦች ባይሻልም በቱርኮች አገዛዙ አንዴ ለቀቅ አንዴ ጠበቅ ሲል እስከ ፩ኛው የአለም ጦርነት የቱርኮች ምርኮና አገልጋይ ሆኑ። የኩርድ ብሄርተኝነት በጥቂቱም የጀማመረው የአንደኛው የአለም ጦርነትን ተንተርሶ ነው። በዚህ አስከፊ ጦርነት በሚልዮን የሚቆጠር ኩርዲስታን በርሃብና በጦርነት አልቋል። የኦቶማን ቱርኮች ዋነኛ የጦር ሰራዊት የሚገነባው በኩርዶች ነበረ። Michael Eppel በመፅሐፉ እንዳተተው የኩርድ ብሄርተኝነት ከ፩ኛው የአለም ጦርነት በፊት ደካማ ለምን ሆነ? ሲል በምክንያት ያቀረባቸው አምስት ምክንያቶች አሉት።

  1. Primary identity……..ትምህርት ያላገኙና በድህነት የሚማቅቁት ኩርዶች ማንነታቸውን ከኑሯቸው፣ ከጎሳቸውና ከሃይማኖታቸው ጋር በማያያዝ ኩርድነታቸውን ዘንግተውታል። የአማራ ህዝብም ማንነቱን በኢትዮጵያዊነቱ እየለካ አማራነቱን ዘንግቶታል። ጋዜጠኛ የሺሃሳብ አበራ እንዳለው ለአማራ ህዝብ መፍትሄው ከኢትዮጵያዊነት ባዕድ አምልኮ መውጣት ነው።
  2. The personal or tribal interest of the land owners and sufi sheks………የኩርድ የጎሳም ይሁን የሃይማኖት መሪዎች ተገዥነታቸው ለቱርክ ኢመራቶች እንጅ ለህዝባቸው አይደለም። ከቱርኮች የሚቃረን መሪ ከተገኜ በሆዳም ኩርዲስታኖች ይመታል። የአማራን ህዝብ ደግሞ ስናየው ብአዴን የሚባል የወያኔ ፈረስ አለ። ብአዴን የሚያገለግለው ለፈጣሪው ህውሃት እንጅ አንድም ቀን ለአማራ ህዝብ አልሆነም….አይሆንም። ብአዴን የአማራን ህዝብ በማንነቱ እንዲያፍር ባህሉና ወጉ እንዲጠፋ ከአለቃው በሚሰጠው ቀጭን ትዕዛዝ ይፈፅማል። ብአዴን እንደኩርድ የጎሳ መሪዎችና ሼኮች የማዕከላዊ መንግስት ጉዳይ አስፈፃሚ ነው።
  3. The strength of intertribal rivalries……..በኩርዶች ስር ሰዶ የነበረው የእርስ በእርስ ግጭት ሲሆን ይህ እንዲፈፀም የየጎሳ መሪዎችን ቱርኮችና ኢራኖች ይረዷቸው ነበረ። ምንም እንኳ በአማራ ህዝብ የጎሳ ግጭት አለ ባይባልም እንዲፈጠር የሚሰሩ ሃይሎች ነፍ ናቸው። ወሎ፣ ጎጃም፣ጎንደርና ሸዋን እንደጎሳ በመቁጠር እርስ በእርሱ እንዲጠራጠርና እንዲበላላ የሚሹ የትግራይና የኦሮሞ ኤሊቶች እንዲሁም እንከፍ የእኛው ወግኖችም አሉበት። ይሄ እንዲሆን ልንፈቅድላቸው አይገባም። ቅማንት አስብለው ያስነሱት እሳት ያጠፋውን ጥፋት መመልከት በቂ ነው።
  4. The weakness of the Kurdish modern middle class ……..ተምረናልና ዘምነናል የሚሉት የኩርድ ሰዎች ማንነታቸውን ከቱርኩ ማንነት ጋር ማዛመድና ኩርድነታቸውን እያወቁ የቱርክ ካሊፋ ታማኝ አገልጋይ መሆናቸው…..። ይሄን ጉዳይ የአማራ ምሁራንን በደንብ ይገልፃቸዋል። አማራ ነን ማለት ያወረዳቸው እየመሰላቸው የኢትዮጵያዊነት አገልጋይ ነን እያሉ ሲንከባለሉ ይውላሉ።…….የሚገርመው ግን ኢትዮጵያ ኢትዮጵያየን ምን ቢዘምሩ በሌላው ብሄር አማራ ተብለው እንጅ ኢትዮጵያዊ ናቸው የሚል አንድም አታገኙም። አንወርድም ይላሉ……የወረዱ መስሏቸው።…ይልቅስ አማራነት ክፍታ ነው። ቤተሰቦችህ ወገኖችህ በአጠቃላይ የአማራው ማህበረሰብ እድገትና ስልጣኔ እንዲሁም እንደህዝብ ተከብሮ ሲኖር ነው ያንተም የኢትዮጵያ መዝሙር ሊቀጥል የሚችለው። አንተና ቤተሰብህ ላይ ሲደርስ አይደለም አማራ ነኝ …በአማራነቴ ነው የተበደልኩት ማለት ያለብህ…! አንተ ምሁር ነኝ ባይ የጎረቤትህ አማራ ቤት ሲቃጠል ዝም ብለህ ካየኸው ነገ ያንተን ያንቦገቡጉልሃል። ከጎረቤት ካሉ ወገኖችህ ተባበር። መክት! ሲያስፈልግም አንክት። ከኢትዮጵያዊነቴ አልወርድም እያልክ ስትኮፈስ ጅቦ ይዘነጥልሃል። ምሁራን መጀመሪያ ለሚመስልህ ህዝብ ስራ….ተረዳዳ አማራ ነኝ በል። ከራስህ መትረፍ ስትጀምር ሌላውን እርዳ….! አባቶቻችን ሃገር ያቆሙት የሃገር ባለቤት እንድንሆን እንጅ የማንም ወፈፌ መፈንጫ እንድንሆን አይደለም። አንተ የሃገር ባለቤት ለመሆን ምን ያንስሃል? መሬት? ጥበብ? ህዝብ? ምንድን ነው የሚያፍረከርክህ? ኢትዮጵያዊነት የምትለው የአማራው እርስቱ አይደለችም ወይ? አማራ ማለት ኢትዮጵያ ናት እያሉ ሲያላዝኑ የሚውሉ አረመኔ ብሄርተኞችን አትመለከትም። ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነትም በለው የአማራ ብሄርተኝነት ቅድሚያ ለራስህ እወቅበት። ኢትዮጵያ በአማራነትህ የተቀበርክባት የሰማይ ቤትህ አይደለችም። ምሁራን በዚህ በኩል ልለምናችሁ የኩርድን ባርነት ናፍቃችሁ የማንም አገልጋይ ከመሆን ወጥታችሁ ለአማራ ህዝብ አገልግሉ። …………ኩርዶች የተማሩ ቢሆኑም የተማሩት የቱርካዊነት ትርክትን ነው….! የኢራንና የኢራቅነትን ትርክትን ነው። ታዲያ በአሁኑ ዘመን ለመሰብሰብም አስቸጋሪ የሆነባቸውም በጊዜ ነቄ አለማለታቸው ነው።
  5. Absence of a clear nationalist vision……ከኩርዳውያን መካከል ጥቂት ብሄርተኞች ቢኖሩም ጥርት ያለ ግብ የሌላቸው መሆኑና በኢስታንቡል ጭፈራ ቤቶች እያመሹ ተራ አሉባልታ እያወሩ እንደሚውሉ……ኩርድን እንደሃገር ለመገንባት የሚያስቡት ነገር የለም። ለኩርዶች እንዲያውም ከባድ የሆነው ቋንቋቸው መዳከምና ምንም አይነት የግላቸው የፅህፈት ልምድ የሌላቸው መሆን አስቸጋሪ አድርጎባቸዋል። አረበኛ….የቱርክ….የፐርሽያውያንን ቋንቋ ከመናገር በቀር የራሳቸው ቋንቋ ተዳክሟል። አሁንም ቢሆን
    ኩርዶችከአረባዊነት…ከቱርካዊነት…ከኢራናዊነት….ከኢራቃዊነትና ከሶሪያዊነት አስተሳሰብ የወጡ አይመስሉም። ኩርድ ሆኖ የISIS ጦረኛ አለ። ኩርድ ሆኖ የቱርክ ጦር አዛዥ አለ። ኩርድ ሆኖ የራሱን የሶሪያ ኩርዶች ሊወጋ የሚሄድ ኩርድ አለ። በዚህ ድብልቅልቅ ውስጥ የሚገኙት ኩርዶች እጅግ ያሳዝኑኛል። የሚሳካላቸው አይመስለኝም። እድላቸው ያመለጣቸው ከአንደኛውና ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ሀገራት ሲመሰረቱና አንዱ አንዱን እየቆራረሰ ሲወስድ ዝም ብለው እንደተኙ ነበርና። ከጥቂቶች በቀር ጥያቄውም አልነበራቸውም። ኢራንም ሆነ ቱርክ እንዲሁም ሌሎች እንደሃገር ሲቆሙ እነሱ ገና ዱሮ እንደነበሩት የከብት ጭራቸውን እየተከተሉ በኤፍራጠስና ጤግረስ ከብቶቻቸውን ውሃ እያጠጡ ነበረ። በሃይማኖት ሰበብ ቅጥቅጥ አድርገው ገዝተው ..ከትምህርት ከማንኛውም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ውጭ አድርገው ጦረኝነታቸውን ብቻ ተጠቅመው እንደማስቲካ አላምጠው ተፏቸው። የአማራ ህዝብን ውሰዱት …..ትምህርት ገና 30% ሳይደርስ 99 ደርሰናል ብሎ ሪፓርት የሚያደርግ አማራ እያለ……ለ7000 አመታት የተጠቀምንባቸውን የእርሻ መሳሪያዎች እንዳይጥል የተደረገ አማራ እያለ…..የኢትዮጵያዊነት ባዕድ አምልኮ እያለ…..እርስ በእርስ ሲታኮስ የሚያድር አማራ እያለ…..እናቶቻችን በወሊድ እያለቁ ሆዳሙ ነርስ አንድም እናት በወሊድ አትሞትም ብሎ የሚፈክር እያለ…….ኢትዮጵያ እያልን ጦርነት በተነሳ ቁጥር ማረሻውን ቀጥቅጠን ጦር እያደረግን በተዋጋንባት አገር ላይ አማራን ያየህ እየተባለ የሚሳደድባት አገር ላይ እየኖርን….. ግርም የሚለኝ ግብ ሰለሌለን ማንም በወጣ በወረደ ቁጥር ከበሮ ይዘን መደለቃችንን ተያይዘነዋል። የአማራ ህዝብ ግን በዚህ እንቅልፉ ከቀጠለና ጥሩ ቀስቃሽ ከሌለው ገና ገና እንግልቱ ይበረታበታል።
    ይሄ ሁሉ የሚደርሰውም አማራ ላይ ናው! ድርጊቱንም የሚፈፅሙት አማራ ላይ ነው። አማራም ቆሞ መሞትን ተለማመደው። የጠላትን ጉርንቦ ፈጥርቆ የሚጥል አማራ ወገኖቼ በሚላቸው ወገኖቹ የሚደርስበትን ደባ ስናይ የኩርድ እጣ ፋንታ ነው እንላለን። ኩርዶች ምናልባት ታዕምር ካልሆነ በቀር አንድ state ይሆናሉ ብየ አልገምትም። የአማራ ህዝብ ሶስት ምርጫዎች አሉት….
    ፩..ኢትዮጵያዊ ነኝ እያለ ተጨፍጭፎ ማለቅ
    ፪…በኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ ተደራጅቶ መመከትና የስልጣን ባለቤት መሆን
    ፫…ነፃ የአማራ መንግስት መመስረትና የአገር ባለቤት መሆን
    አንደኛው የኩርድ እጣ ወይም ከዚያ በላይ ነገር ይደርሳል።

Via Joshua Ram

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator