ብልፅግና የመራጭ ድምፆችን መለመኛና መስረቂያ ፕሮጄክቶች ሲመፃደቅ ለሀገር ወሳኝ የሆነው ጣና ኃይቅ ህልውና እደጋ ላይ እንደወደቀ ነው

ወንድወሰን ተክሉ

? ከአባይ ግድብና ከአዲስ አበባው መኪና ማቆሚያ ፕሮጄክት የትኛው ነው ለሀገርና ለህዝብ የሚጠቅመው??

?ከቤተመንግስቱ አንድነት ፓርክና ከአባይ ግድብ የትኛው ነው ለሀገርና ለህዝብ የሚጠቅመው?

?የህዳሴውን ግድብ ግንባታን አጠናቅቄ ለመፈፀም የውሃ መሙላት ስራን እጀምራለሁ የሚል መንግስት የግድቡን የውሃ ምንጭ ከሆነው አንዱን የጣናን ሃይቅ ህልውናን ዘወር ብሎ ባለማየት ይቻለዋልን???

የሀገራችን ወቅታዊ ፖለቲካ የቱን ያህል እጅና እግሩን ያጣ – የጊዜያዊ በላተኞች መነኻሪያ : የስልጣኖች ሁሉን ስልጣን ማሳደጃ መሆኑን እምናውቀው የኢኮኖሚውንና የልማቱን ዘርፍ ስንመለከት ነው::

አቢይ መራሹ መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣበት ማግስት አንስቶ በቢሊዮን ዶላር ወጪ ከሶስት ደርዘን በላይ ፕሮጄክቶችን ገንብታል እያስገነባም ነው::: በአብዛኞቹ ማለት ይቻላል እጅግ አጭር ፖለቲካዊ ትርፍ ማጋበሻነት ታስበው የተሰሩ የታይታይ ፕሮጄክቶች ሲሆኑ እጅግ ወሳኝና ጠቃሚ የሆነ ስራን – እንደ የጣንን ኃይቅ ከእምባጭ ወረራ ለመታደግ ድንቡሎ ወጪ አድርጎ መስራት የተሳነው ስርአት መሆኑን በተጨባጭ ተግባሩ በገሀድ እያሳየን ነው::

በአዲስ አበባ ብቻ ድምፅ መስረቂያነት ታቅደው ለታይታይ የተገነቡና እየተገነቡ ያሉ ፕሮጄክቶችን ወጪ ስንመለከት በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠር እንደሆነ ዳታዎች ያሳያሉ:::

ነጥባችን ለምን ግንባታዎች ይካሄዳሉ: ለምን ልማት ይፈፀማል ሳይሆን ልማቱና ግንባታው እውነተኛ ለሀገርና ለህዝብ በሚጠቅም መልኩና ቅድሚያና የቅድሚያዎች ሁሉ ቅድሚያ first priority የሚያስፈልጋቸውን እንደነ የጣናን ኃይቅ የመታደግን ስራ ለምን አይሰሩም የሚል ነው::

ይህ ስልጣን ላይ ያለው ስብስብ ከሶስት አመት በፊት ጣናን ኬኛ በሚል መፈክር ሁለት መቶ ወጣቶችን በመላክ ጣናን እንታደግ ሲል በወቅቱ ለስልጣን የሚያበቃውን የኦሮማራን ህብረት ለመፍጠር ሲል ፖለትካዊ ተግባር ፈፀመ ተብሎ ሳይሆን የታየው ተቆርቋሪነቱን ገለፀ በማለት ያዩትና ያሰቡት በርካቶች ናቸው::

ያኔ መንግስት አልነበረምና ማድርግ የቻለውን ወጣቶችን የመላክን ተግባር የፈፀመ ዛሬ ስልጣን ላይ ተቆናጦ መንግስት በሆነበትና ቢሊዮን ዶላሮችን እየመዠረጠ ከሶስት ደረዝን በላይ ፕሮጄክቶችን ሲያስገነባ ምነው 2%ያህሉን ወጪ መድቦ ጣናን ለመታደግ አልሞከረም ብለን ስንጠይቅ ፍትሃዊ ጥያቄ ስለመሆኑ አንፋሽና አጎንባሽ ያልሆኑት ሀቀኛ ዜጎች በሙሉ የሚያውቁትና የሚስማሙበት ሀቅ መሆኑን እናውቃለን:

በብልጭልጩ አትታላሉ ይላል ጠቢቡ – እናም ይህ የስልጣን ጥመኛ ስብስብ የድምፅ መለመኛና መስረቂያ ፕሮጄክቶቹን ገታ አድርጎ ቅድሚያ መሰጠት ለሚገባው ለእንደ ጣና አይነቱ ችግር ቅድሚያ እንዲሰጥ መስሚያ ጆሮ ካለው ጥሪያችንን እናሰማለን!!!!

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator