0 0
Read Time:4 Minute, 57 Second

በዚህ ትንታኔ ለአንባቢን መሰረታዊ ግንዛቤ ያመች ዘንድ ‹ወልቃይት› እያልን የምንጠራው አካባቢ ጠገዴንና ሰቲት ሁመራን ያካትታል፡፡

በዚህ ቀጠና እንደአማራ ቀዳሚ ፍላጎታችን የተነጠቀ ማንነታችንን ማስመለስ ሲሆን፤ አማራ በመሆናቸው ብቻ በትህነግ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጸምባቸው የኖሩ ወገኖቻችን ከቀጥተኛ የህልውና አደጋ ተጋላጭነት ነጻ ማድረግ፣ እንዲጠፋ ሲሰራበት የኖረውን አማራዊ ማንነታቸው ዳግም አብቦ፣ የተጎዳ ስነ-ልቦናቸው ተጠግኖ አማራዊ የአስተዳደር ነጻነታቸው እውን ሁኖ ማየትና ለሠላሳ ዓመታት ለተፈጸመው ግፍና በደል የፍትሕና የካሳ ጥያቄ ያለን መሆኑ እንደተጠበቀ ሁኖ፤ በዚህ ጽሁፍ የአካባቢውን ስትራቴጅካዊ ጠቀሜታ እንመለከታለን፡፡

ጉዳዩ ከርስት በላይ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት የማስጠበቅ ጉዳይ ስለመሆኑ በማስረጃዎች እንፈትሻለን፡፡

ወልቃይት የቀጣናዊ ፖለቲካዊ መስፈንጠሪያ ማዕከል እና የብሔራዊ ደህንነታችን አስኳል ስለመሆኗ በዝርዝር እንመለከታለን፡፡

የተከዜ ዘቦች ነን መልካም ንባብ ይሁንላችሁ!
የወልቃይት ጂኦ-ፖለቲካዊ ጠቀሜታ ኢትዮጵያ በቀጠናው ላይ ለሚኖራት የበላይት እጅግ ወሳኝ ስትራቴጅካዊ አካባቢ ሲሆን፤ ለአማራ ህዝብ ደግሞ ሁለመናው ናት፡፡ ትህነግ ይህን በሚገባ ከተገነዘበ ውሎ አድሯል፡፡ ‹ወልቃይት ለአማራ ህዝብ ሁለመናው ናት› ስንል እንዲሁ ሳይሆን፤ እጅግ ዘርፈ ብዙ አገራዊና ክልላዊ ፋይዳ ያላት ከመሆኑም በላይ ለአማራ ህዝብ የማንነቱ መገለጫውና ኩራቱም በመሆኑ ጭምር ነው፡፡ ስለሆነም ወልቃይትን ከአማራ መንጠቅ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአማራ ህዝብ ጉዳቱ ከፍተኛ ሲሆን፤ ለትህነጋዊያን ደግሞ የደደቢት ቅዠታቸው የሆነውን ‹ታላቋ ትግራይ›ን እንዲመሰርቱ ትልቁን በር ይከፍትላቸዋል፡፡ ለዚህ ነው ትህነጋዊያን ወልቃይትን የሞት ሽረት ጉዳይ አድርገው የሚመለከቱት፡፡

ትህነግወልቃይትና አካባቢውን ዳግም በመቆጣጠር ኢትዮጵያንና አማራን ለማዳከም ሌላ እድል ያገኝበታል!
ትህነግ ወልቃይትን በመቆጣጠር ከሱዳን ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር፤ ያልተገደበና በራሱ የሚመራ የውጭ ግንኙነት በመፍጠር፤ አገር የመሆን ህልሙን እውን ለማድረግ ይጠቀምበታል፡፡ ከሱዳን ወታደራዊ ኃይል ጋር በመሻረክ ከሁመራ እስከ ቤንሻንጉል ያለውን የኢትዮጵያ መሬት የመቀራመት ፍላጎት እንዳለው በሀገር ክህደት ተግባራቱ አሳይቶናል፡፡ በተጨማሪም በአባይ ውሃ ጉዳይ የኢትዮጵያ ባላንጣ የሆነችውን ግብጽን ለሀገራዊ ቀውስና ብጥብጥ እጇን በሰፊው እንድታስገባ እየመራ ለማምጣት፣ በእነርሱ የመሳሪያ ድጋፍ ማዕከላዊ መንግሥቱንና የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትን በመውጋት ኢትዮጵያን ወደፍርስራሽነት በመቀየር ግብጽ በአባይ ፖለቲካ የነበራትን የበላይነት በቋሚነት ለማስቀጠል የባንዳነት ተልዕኮውን ለመወጣት፣ በወኪሎቹ በኩል የካይሮን ደጅ ደጋግሞ ረግጧል፡፡ የትህነግ ጭፍራዎች ከግብጽ ሚዲያዎች እኩል ጸረ-ኢትዮጵያ የሆኑ ፕሮፖጋንዳዎችን ሲነዙ የሚውሉት ኢትዮጵያን ለማፍረስ የጋራ ውል ያላቸው በመሆኑ ነው፡፡

በዚህ ሂደት ትህነጎች ቢሳካላቸው እስከ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ያለውንና በምናብ ካርታቸው ላይ ያሳዩንን መሬት አካተው የ‹‹ታላቋ ትራግይ››ን ምስረታ እውን ሲያደርጉ፤ የሱዳን ወታደራዊ ኃይል ደግሞ ባልተጨበጠ የታሪክ ዳራ እና የሕግ ማዕቀፍ ከኢትዮጵያ ‹‹አለን›› የሚለውን መሬት በቀላሉ ይረከባል፡፡ ምኞታቸው ይህ ነው፡፡ በዚህ ለማሰናከል ፍላጎታቸውንና የእጅ አዙርና ይፋዊ ድጋፋቸውን አሳይተውናል፡፡ አሁን ላይ እነዚህ ጥቂት ግን ደግሞ ተጽዕኖ እንፈጥራለን የሚሉ የውጭ ኃይሎች ትህነግን ለማጠናከር፤ በተለይም የጦር መሳሪያና ሎጅስቲክስ ለማቅረብ ወደ ትግራይ መግቢያ በር ይፈልጋሉ፡፡ ይሄ በር ደግሞ ወልቃይት ነው፡፡

ራያና አካባቢው ለትህነጎች እና ‹አቅመ-ቢስ መንግሥት› (Banana Republic) የመትከል ፍላጎት ላላቸው ለውጭ ኃይሎች የወልይቃትን ያኽል አስፈላጊና ምቹ ስላልሆነ በሁለተኛ ደረጃ ይዘውታል፡፡ በዚህም ምክንያት የግብጽ ደጋፊ ውስን የምዕራቡ ዓለም ሀገራት ከራያ ይልቅ ወልቃይትን የቅድሚያ ቅድሚያ (Prioritize) ሰጥተው እንታመንለታለን የሚሉትን መርህ ለመጣስ ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ይህም (የወልቃይት አማራ) ‹[አንድ ሕዝብ] ራሱን በራሱ እንዲያስተዳደር፤ በአፍ መፍቻ ቋንቋው እንዲማር፣ በቋንቋው ችሎት እንዲሰየምለት፣ የቤተ-እምነት አገልጋሎት እንዲያገኝ› የሚያስችለውን መሰረታዊ መብቶቹ ተጨፍልቀው፤ ለትህነግ ተላልፎ እንዲሰጥ ጸረ-ዴሞክራሲና ጸረ-ሉዓላዊነት ዘመቻዎች ላይ ተጠምደዋል፡፡ ይህ ቢሳካላቸው የጦር መሳሪያዎችንና ሌሎች አስፈላጊ የጦርነት ሎጀስቲክሶችን ወደ ትግራይ በማስገባት፣ የተዳከመች ኢትዮጵያን በመፍጠር ቀጣናዊ የበላይነታቸውን ለማስጠበቅ ይጠቀሙበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ: ሰውየው (ክፍልሁለት) ከይገርማል ታሪኩ
Powered by Inline Related Posts
በጠቅላላ ሂደቱ ‹ለእኛ ታዛዥ አልሆነም› ያሉትን የኢትዮጵያ መንግሥት ከቻሉ በትህነግ በኩል ማስወገድ፤ ካልሆነም አቅመቢስ እንዲሆን ለመድረግ ይሞክራሉ፡፡ ይሄን እኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት ደግሞ ከትህነጎችም በላይ ትህነግ ሆነው ወልቃይት በጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሉ (ትህነግ) እጅ ለማስገባት ወሳኝ ስትራቴጅካዊ አጀንዳቸው አድርገው ወስደውታል፡፡

ከአሁናዊ ፖለቲካችን አንጻር ወልቃይት ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን እንደ አይን ብሌን ሁኖ መታየት ያለበት ቦታ ነው!

ከፍ ሲል ለማንሳት እንደተሞከረው፤ ትህነጋዊያን እና አሻንጉሊት መንግሥት የመፍጠር ፍላጎት ያላቸው የውጭ ኃይሎች ክሳቸው ከታሪክና ከነባራዊ ሁኔታ የሚመነጭ ሳይሆን፤ ከጊዜዊ ጥቅምና ከጂኦ-ፖለቲክሱ ስትራቴጅካዊ ጠቀሜታ አንጻር ነው፡፡ ለዚህም ነው ወልቃይትን እጅግ አስፈላጊ ቦታ አድርገው የወሰዱት፡፡ እነዚህ የውጭ ኃይሎች ወልቃይት የበጌምድር ታሪካዊ አካል የአማራው ግዛት ስለመሆኑ ባይጠፋቸውም፤ እውነታውን ለመሻር ከፍ ሲል በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ፤ ዝቅ ሲል ደግሞ በአማራ ክልል መንግሥትና ህዝብ ላይ የቻሉትን ያኸል ተጽእኖ ለማድረግ እየሞከሩ ነው፡፡ እነዚህ ወገኖች የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎቻቸውን ደግመው እስካልፈተሹና ከነባራዊው ሁኔታ ጋር አጣጥመው ለመጓዝ እስካልፈለጉ ድረስ (ሩቅ ሊያሻግራቸው ባይችልም) ከጊዜዊ ጥቅም አንጻር ሲታዩ ወልቃይት ጸረ-ኢትዮጵያ ለሆነው ኃይል ተላልፎ እንዲሰጥ ጫና መፍጠራቸው በራሳቸው መንገድ ልክ ሊመስል ይችላል፡፡ እነዚህ ኃይሎች ትህነግን መርዳት ሽብርተኝነትን ማበረታታት ስለመሆኑ ሊጠፋቸው ባይችልም አሁናዊ ሚናቸው በውጤቱ ለቀጣናው አውዳሚ ስለመሆኑ ገሃድ ወጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት እና ሕዝብ ደግሞ፤ ወልቃይትን ከእጃቸው እንዳይወጣ፤ ቀጠናውን የመቆጣጠርና በሕግ ለሚገባው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የማፅናት፤ ከማንም በላይ ምክንያትና ጥቅም አላቸው፡፡ ኢትዮጵያን በመካድ በሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ላይ ክህደት ለፈጸመው፤ እንዲሁም ‹‹ታላቋ ትግራይ›› የመመስረት ፍላጎቱን ገሃድ ላወጣው ትህነግ ወልቃይትን ማስረከብ ማለት፤ በኢትዮጵያ የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት ላይ እሳት የመለኮስ ያህል አደጋ አለው፡፡ አልፎም ድርጊቱ ሀገርን ለባዕድ አሳልፎ ከመስጠት አይተናነስም፡፡

በኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች የጋራ ሀብት የተገነባው የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ፍጻሜውን እንዳያገኝ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር የሚሰራው ትህነግ፣ ወደጎረቤት ሀገር በነጻነት የሚንቀሳቀስበት የመልክዓምድር አመችነት አገኘ ማለት ኢትዮጵያን ለመበተን ተጨማሪ ጉልበት፣ ዕድልና ሁኔታዎችን እንደማመቻቸት ይቆጠራል፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት የማይደራደሩት መላ የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች ከአማራ ህዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡ በአሁናዊውና በመጭው ዘመን ፖለቲካችን የወልቃይት ጉዳይ ከኢትዮጵያ የግዛት አንድነት እና ከሀገር ሉአላዊነት ጋር የሚያያዝ በመሆኑ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ አካባቢውን በንቃት ሊጠብቁ፣ የሀገር ውስጥ ባንዳዎችንና የውጭ ጠላቶችን ሊመክቱ ይገባል፡፡

ሌላው የወልቃይትን ጉዳይ እንደ አይን ብሌን የምንመስልበት ጉዳይ፤ ወልቃይት ለኢትዮጵያ ሌላኛው አማራጭ የባህር በር መስመር መሆን የሚያስችል መልክዓምድራዊ ዕድል ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ይኼም ማለት የምጽዋ ወደብ ከሁመራ በ400 ኪ.ሜ የሚገኝ ሲሆን፤ ሰፊ የገበያ ፍላጎትና አቅም ላለው የሰሜን ምዕራብ የኢትዮጵያ ክፍል የወጭ ገቢ ንግድ ፍላጎቱን ያሟላል፡፡ ይህ የወደብ አማራጭ ከኤርትራ ጋር የሚኖረንን ሁለንተናዊ ግንኙነት ያጠናክርልናል፤ የጋራ ሠላምና ደህንነታችን የምናስጠብቅበት ተጨማሪ እድል ይፈጥርልናል፡፡

በሌላ በኩል በትህነግ የአፓርታይድ አገዛዝ ስር የቆየው ወልቃይትና አካባቢው፣ በቀጣይ ወደዚህ አካባቢ ከመላው ኢትዮጵያ ለሚመጡ ወጣቶች ሰፊ የስራ እድል የሚያገኙበት ቦታ ይሆናል፡፡ ላለፉት ሠላሳ ዓመታት እንደነበረው አግላይና ዘረኛ አካሄድ፣ ትግረኛ ቋንቋ መናገር የሀብት ምንጭ መሆኑ አብቅቶለት ኢትዮጵያዊያን በጥረታቸው ልክ ሀብት የሚፈጥሩበት በገበያ ሕግ የሚመራ አካባቢ እንዲሆን የሚያስችል ፖለቲካዊ ሥርዓት ይፈጠራል፡፡ በዚህም ወልቃይትና አካባቢው በወንድማማችነት ስሜት የጋራ ብልጽግናችን ምንጭ በመሆን የኢትዮጵያ ቀጠናዊ የበላይነት ማረጋገጫ የልማት ኮሪደር ይሆናል፡፡

በአካባቢው የሚመረተውን ሰፊ የሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ማሽላ፣ የዱር ሙጫ፣ ወዘተ… ለመሰብሰብ የሚመጡ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ከመላ አገሪቱ የተውጣጡ በመሆናቸው፣ ይህ የሚያመለክተው ወልቃይትና አካባቢው የመላ ኢትዮጵያዊያን እንጅ የአንድ አካባቢ/አማራ ብቻ አለመሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም የወልቃይትን ጉዳይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደአይን ብሌኑ ሊያየው ይገባል፡፡

ትህነግ በየትኛውም አማራጭ ወልቃይትን ዳግም መልሶ ካገኘ ኢትዮጵያን በትኖ ‹‹ታላቋ ትግራይ››ን ለመመስረት መነሳሳቱ አይቀርም፡፡ የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች የጋራ ብሔራዊ ደህንነት አደጋን ለማስተናገድ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ወልቃይት የጋራ ቀይ መስመራቸው ሊሆን ይገባል፡፡

የተከዜ ዘቦች
ወል ቃይት፤ ከተከዜ ፖለቲካ እስከ ቀይ ባህር ጂኦ-ፖለቲካ

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator