0 0
Read Time:1 Minute, 11 Second


****ወንድወሰን ተክሉ****

“ኢዜማ ማህበረሰቡን በጊዜያዊ ስሜት እያነሳሳ በውስጥ ያለውን ቅራኔ እያባባሰ በዚያ በሚገኝ ዝና ስልጣን ላይ የመውጣት ፍላጎት የለውም”
ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ
በማለት በይፋ ተናግረዋል::

የኢዜማው መሪ ይህን ሲሉን ምን ለማለት እንደፈለጉ አውቃችኃል?? እያስተላለፉት ያለውን መልእክት እንመልከትላቸው እስቲ ……..

ይህ ማለት …
? እንደ ኢዜማ አባባል opportunist አይደለሁም – በአንፃሩም የተረጋጋና ለሀገር የሚጠቅምን እስትራቴጂና ፖለቲካዊ አቋምን መርህ ያደረገ አካሄድ የምከተል ድርጅት ነኝ እያለን ነው::


? ሁለተኛው ምን ማለት ነው”ኢዜማ በህዝቦች ውስጥ ያለን ቅራኔ እያፋፋመ ማህበረሰቡን በጊዜያዊ ስሜት በማነሳሳት ስልጣን ላይ መውጣት ፍላጎት የለውም” ብሎ ማለት???

?1ኛ- ኢዜማ ቀደም ብሎ ለስልጣን ሳይሆን ስልጣን ላይ ያለውን የአቢይ መንግስትን ደጋፊ አማካሪና የሚረዳ መሆኑን ያሳወቀና ሌት ተቀን እየሰራ ያለ ድርጅት ነኝ ማለቱ ነው

?2ኛ- በዚህ በአቢይ መንግስት ደጋፊነቴ መር አካሄዴ ዜጎች ሲበደሉ ሲፈናቀሉ ቤታቸው በላያቸው ላይ ያላግባብ ሲፈርስ የአዲስ አበባን ህልውና የሚንድ መንግስታዊ ተግባር ሲፈፀም እንደ እውነተኞቹ የህዝብ ተቆርቋሪዎች የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አብን እና አዴፓ መንግስትን ተቃውሜና ህዝብን ደግፌ ድምፄን የማሰማ አይደለሁም እያለን ነው


?3ኛ- እታች In the ground በህዝቡ ውስጥ እየደረሰ ያለውን ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ችግሮችን መግለፅ ማለት ፀረ አቢይ መራሹ የብልፅግና መንግስት እርምጃ መውሰድ ማለት ነውና የፈለገውን ያህል ህዝባዊ በደልና የህግ መጣስ ቢፈፀም ሞኝ ሆኜ የምቃወም አይደለሁም እያለን ነው


? ሲጠቃለል ኢዜማ opportunist አይደለሁም ቢለንም ተግባሩና አካሄዶቹ በአጠቃላይ ከኦፖርቹኒስትነት በላይ ገዝፎ ፀረ ህዝብነትና ባንዳነትን የተላበሰ አካሄድ እየሄደ እንደሆነ ሰፊው ህዝብ አውቆታል::


? እውነተኛ የህዝብ ድምፆች የሆኑት ከላይ የተጠቀሱት ድርጅቶች በእያንዷንዷ ጉዳይ ድምፃቸውን እያሰሙ የኢዜማን የብልፅግናን ተላላኪነትና ጉዳይ አስፈፃሚነትን ተግባር እጋልጠዋልና አጅሬ ብሬ የፈለገውን ቢወሻክት አንደበቱን ሳይሆን ተግባሩን ነው የምናምነውና ከንቱ ጩህትን አስምቷል ብዬ ነው እምረዳው

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator