0 0
Read Time:1 Minute, 51 Second

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ማኅበር መንግሥት ለመገናኛ ብዙኀን ችግሮች መፍትሄ እየሰጠ እንዳልሆነ ገልጧል።

የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች ከቤታቸውና ከሥራ ገበታቸው በጸጥታ ኃይሎች መታፈናቸው እንዳሳሰበው የገለጸው ማኅበሩ መንግሥት ጋዜጠኞችን በሕግ አግባብ ብቻ እንዲጠይቅ እና ጋዜጠኞችን ያፈኑ አካላትም ለሕግ እንዲቀርቡ ጠይቋል።

የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በነጻነት ስራቸውን እንዲሰሩ እንደሚያደርጉ እና በጋዜጠኞች ላይ ምንም አይነት እንግልት እንደማይደርስ ቃል ገብተው ነበር ሲል ጠ/ሚ አብይን የወቀሰው ማኅበሩ ስለሚደርሱ በደሎች ጩኸታችን ሰሚ አግኝቶ መሻሻል ከማሳየት ይልቅ ከድጡ ወደማጡ እየተቀየሩ ስለመምጣታቸው ገልጧል።

ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ሕግ ባለበት ሀገር በጠራራ ጸሐይ ከሚሰሩበት ቦታ ወይም ከሚኖሩበት ቤት ያለሕግ አግባብ ታፍነው የተወሰዱ፣ በማይታወቅ ቦታ ታግተው የቆዩ እና ተሰውረው ከቆዩበት ቦታ በአፋኞቻቸው በድንገት የተለቀቁ ጋዜጠኞች በርካታ ናቸው ብሏል፡፡

ከማሕበራችን በተጨማሪ ይህ ጉዳይ ያሳሰባቸው በኢፌዴሪ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ መግለጫዎችን አውጥተው ነበር ሲል አክሏል፡፡

በተጨማሪም የጋዜጠኞቹ ታፍኖ መወሰድ እና ደብዛ መጥፋት ጉዳይ በማሕበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በከፍተኛ ደረጃ የብዙ ዜጎች መነጋገሪያ መሆኑም ጸሐይ የሞቀው እውነት
ነበር ሲል ገልጧል፡፡

በተጨማሪም በቅርቡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ራሱ ያወጣውን የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ 1238/2013 ራሱ በመሻር መጋቢት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የቦርድ አባላትን ሹመት ያጸደቀበትን መንገድ ድግሞ ማሕበራችን የፕሬስ ነጻነቱን ይበልጥ የሚያሸመደምድ ሆኖ አግኝቶታል፡፡

በምክር ቤቱ ከተጣሱ የአዋጁ
ክፍሎች መካከል፡-

  1. የቦርድ አባላት እጩዎችን የመመልመልና የማፅደቁ ሂደት ለሕዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ አለመከናወኑ፣
  2. ሕዝብ እጩ ግለሰቦችን ሳይጠቁመና በእጩዎችም ላይ አስተያየት ሳይሰጥ የተካሄደ ምርጫ መሆኑ፣
  3. የእጩዎች አመራረጥ ሂደትና የተመረጡ እጩዎች ዝርዝር በመገናኛ ብዙኃን ወይም በሌሎች ኤሌክትሮኒክ
    ማሰራጫዎች በይፋ አለመገለጹ፣
  4. ከቦርዱ አባላት መካከል ሁለቱ ከመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ወይም ከሲቪል ማኅበረሰብ እንደሚሾሙ አዋጁ ቢገልጽም አንድም የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች አባል በዚሁ ሹመት አለመካተቱ ይጠቀሳሉ፡፡

ማሕበራችን ይህ ሕግን የጣሰ አካሄድ ‹‹የቦርዱ አባላት ሥራቸውን ሲያከናውኑ ከፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጣልቃ ገብነት ወይም ተፅዕኖ ገለልተኛና ነፃ መሆን አለባቸው›› (ክፍል 2፣ ቁጥር 6) የሚለውን ድንጋጌ የሚፃረር ሆኖ አግኝቶታል፡፡

በዚህም ምክንያት ማሕበራችን ይህን ሹመት እንደማይቀበለው ገልጾ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩን ዳግም እንዲያጤነውና ስህተቱን እንዲያርም በግልጽ ጠይቆ የነበረ ቢሆንም እስካዛሬ ድረስ መፍትሔ ባለማግኘቱ የሕግ አውጭው፣ ሕግ ተርጓሚውና ሕግ አስፈጻሚው የመንግስት አካላት ተባብረው ለመገናኛ ብዙኃን የሰጡትን ነጻነት እየነጠቁት እንደሆነ ተረድተናል፡፡

በመሆኑም የሚመሩት ገዢ ፓርቲ፣ የመሠረቱት መንግስትና የሚመሯቸው የፍትሕ ተቋማት የተገለጸውን ወንጀል በመንግስት ስም የፈጸሙ ግለሰቦችን እና ሕቡዕ ቡድኖች ያለምንም ማደባበስ በቁጥጥር ስር በማዋል ለፍትሕ እንዲያቀርቡ እና ጉዳዩንም ለሕዝብ በይፋ እንዲገለጹ ማሕበራችን በይፋ ይጠይቃል ብሏል ለጠ/ሚኒስትር አብይ በጻፈው ደብዳቤ።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator