ከጋሻ አማራ – የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
የተከበርክ ውድ ታላቁ የአማራ ሕዝብ ሆይ፦
ጸረ አማራ፣ ጸረ ኦርቶዶክስና ጸረ ኢትዮጵያ የሆነው ኦነጋዊው የኦህዴድ ብልጽግና መራሹ ቡድን ታማኝ አገልጋይ የሆነውንና በጫንቃህ ላይ ተጣብቆ ያለው የአማራ ብልጽግና/ብዓዴን የአባርክህ ክፋይ የሆነውን አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴንና ባልደረቦቹን ባህርዳር በ08 ቀበሌ በ2ኛ ጣቢያ ማሰሩን ለማወቅ ችለናል።
እስሩን ተከትሎ በአማራ ክልል ፖሊስ ኮማንደር ክንዱ በኩል አርበኛው ተያዘ ተብሎ የተገለጸበት አገላለጽ ፍጹም ቅጥፈትና ሀሰት መሆኑን ለሕዝባችን እያስታወቅን የፖሊስ ኮማንደሩን እና አጠቃላይ የአማራን ክልል ብልጽግናን ጸረ ፋኖ እና ጸረ አማራ ዘመቻን በጽኑ እናወግዛለን!
እንደ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮማንደር ክንዱ መግለጫ አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ በባህርዳር ከተማ ውስጥ በሕዝብ ጥቆማ ተያዘ ብሎ የገለጸ ሲሆን፤ ሲያዝ በእጁ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ መያዙን እና አርበኛው ህገ ወጥ ቡድን አቋቁሞ የሚንቀሳቀስ ነበር ብሎ የገለጸብርትን ውንጀላ ጋሻ አማራ በጽኑ ያወግዛል።
አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ መላው የአማራ ሕዝብ በጠላት ተወርሮ ህልውናው አደጋ ላይ በወደቀበት ወቅት የክልሉ መንግስት ነኝ የሚለው የአማራ ብልጽግና / ብአዴን ስድስት ጊዜ የክተት ጥሪ ባወጀበት ወቅት ከአቻዎቹ ፋኖዎች የመ/አ ማስረሻ ሰጤና የሸዋ ፋኖ አሰግድ ጋር በመሆን የመላው አማራ ፋኖ አደረጃጀትን በአንድ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል-ፋኖ ስር ለማስተባበር የአማራን ፋኖ ያደራጀ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው እንጂ ዛሬ የድል አጥቢያ አርበኛ ነኝ ባዩ ኮማንደር ክንዱ እንደገለጸው ዘመነ ያደራጀው ህግ ወጥ ቡድን አይደለም።
ስለዚህም የአማራን ፋኖ ሕገ ወጥ ቡድን ብሎ የገለጸውን የአማራ ፖሊስ ኮማንደር ክንዱን ጋሻ አማራ በጽኑ እያወገዘ መላው የአማራ ሕዝብም ፋኖህን ህገ ወጥ ቡድን ያለውን ተቋምና አመራር እንድታወግዝ ጥሪ እናቀርባለን።
የእስር እርምጃው ሂደት ላይ ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ እኔ በወንድሞቼ ላይ ጥይት አልተኩስም ብሎ ከወሰነና እራሱን ካቀረበ በኋላ የተፈጸመ ክህደታዊና ይሁዳዊ በሆነ እርምጃ ሊታሰር የቻለ መሆኑን ያወቅን ሲሆን በዚህም ጉዳይ ላይ ተሳታፊ የሆኑትን – ማለትም አርበኛ ዘመነ ካሴን አስሮ ለኦሮሙማ ለመስጠት ሴራ ላይ የተሳተፉትን ሁሉ በጽኑ እናወግዛለን – አጋልጠንም እንታገላቸዋለን።
ኦነጋዊው የኦህዴድ ጸረ አማራ ቡድን በተለያየ ጊዜ ጫካ በመዋጋት ላይ ካሉ የኦነግ ሸኔ አመራሮች ጋር ተነጋግሬ አመጣኋቸው ያላቸውን በርካታ ነፍሰገዳይና ጨፍጫፊዎችን እጁን ዘርግቶ በፍቅር እየተቀበለ ባስተናገደበት ሁኔታ በህዝባችን ጫንቃ ላይ ተፈናጦ አማራን እመራለሁ የሚለን የጃንደረባዎች ስብስብ የሆነው የአማራ ብልጽግና/ብአዴን ግን፣ አንተ ስትወረርና በጠላት ስትጨፈጨፍ እምቢ ለሕዝቤ ብሎ በመነሳት ታግሎ በመታገል ህልውናውን የሰጠልህን ፋኖ እና የፋኖ አመራሮችን እንደ ወንጀለኛ በማሰር የኦነጋዊውን የኦህዴድን ትእዛዝ የሚፈጽም ነው የሆነው።
- አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ ለምንድነው የሚታሰረው?
- ከ15ሺህ በላይ የአማራ ፋኖ ለምንድነው በብአዴን ታፍኖ በእስር እየማቀቀ ያለው?
- የምስራቅ አማራ ፋኖ – አመራር የሆኑት እነ ምሬ ወዳጆና ፋኖ እስራኤል ለምንድነው የግድያ እርምጃ ተከፍቶባቸው በተዓምር ለመትረፍ የቻሉት?
- የአማራ ልዩ ኋይል ዋና አዛዥ ብ/ጄ ተፈራ ማሞና ባልደረቦቹ ስድስት የጦር አዛዥ መኮንኖች ለምንድነው ከአመራርነታቸው እንዲባረሩ የተደረገው? ለምንድነው እንዲታሰሩ የተደረገው?
በአጠቃላይ የአማራ ፋኖ ለምንድነው በዚህ በጸረ አማራ በሆነው ጃንደረባው ብአዴን የተጠላውና ጦርነት ሊከፈትበት የቻለው ብለህ እራስህን እንድትጠይቅ እንጥይቅሃለን።
ውድ ታላቁ የአማራ ሕዝብ ሆይ፦
ትናንት በሰኔ 2019 ላይ ውድ የሆኑትን መሪዎችህን እነ ብ/ጄ አሳምነው ጽጌና መሰል ለአማራ የሚቆረቆሩ እውነተኛ አማራሮች – እንደ ፋኖ ሻለቃ አስቻለው ደሴና መስል በጸረ አማራው ብልጽግና ቡድን በግፍ መገደላቸው የትናት ማታ የእግር ውስጥ እሳት ትዝታ ነው።
መሪዎችህን በጸረ አማራው ኦህዴድ/ብአዴን በሴራ ከተነጥቅህ በኋላ በነበሩት ሶስት ዓመታት ውስጥ በኦህዴድና በብአዴን የሚዘወረው የብልጽግና መንግስት በአንተ በአማራው ላይ በከፈተው በማንነትህ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ በመጨፍጨፍ የዚህን መንግስት ተብዬን ቡድን ማንነት ቁልጭ አድርገህ አይተሃል አውቀሃልም።
አሁን ባለንበት ሁኔታ የንጹሃንን ደም በማፍሰስና የአማራን አደረጃጀት በማውደም የማይረካውና የማይጠረቃው ደም መጣጩ የኦህዴድ/ብአዴን የብልጽግና ቡድን የአብራክህ ክፋይ፣ የክፉ ቀን ደራሽ በሆኑት ልጆችህ ፋኖዎች ላይ የዘመተበት ምክንያት በአንተው በአማራ ሕዝብ ምክንያት መሆኑን ይጠፋሃል ብለን አንገምትም።
ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴና መላው የአማራ ፋኖ በብአዴን ጥርስ ውስጥ ገብቶ መጠነ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ የተከፈተበት ምክንያት አንተን ሰፊውንና ታላቁን የአማራ ሕዝብ መሪና ተከላካይ ኃይል አልባ በማድረግ፤ አንተን በባርነት ቀፍድዶ ለመግዛት ባለመው የኦነጋዊው/ኦሮሙማ ዓላማ ምክንያት ታማኝ አገልጋዩ በሆነው ጃንደረባው ብአዴን በኩል ሊከፈት የቻለ ዘመቻ ነው እንጂ ፋኖዎቻችን በግልም ሆነ በተናጠል ለእስርና ለእንግልት የሚያበቃ አንዳችም የሆነ ጥፋት ፈጽመው አይደለም።
ውድ ታላቁ የአማራ ሕዝብ ሆይ፦
ታግለው የሚያታግሉ መሪዎቻችንን በማሰር፣ ለነገደ አማራ ህልውና መጠበቅና መከበር ምትክ የለሽ ህይወታቸውን ለመሳዋት የተነሱትን ፋኖዎቻችንን በማሰር በማሳደድና ብሎም እንደ ወንጀለኛ በማውገዝ የአማራን ትግል ማክሸፍም ሆነ ማስቆም አይቻልም፤ ብለህ ትግልህን አጠናክረህ የምታቀጣጥልበት ጊዜው አሁን ሆናል።
አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴንና ባልደረቦቹን – ከወንድሞቻችን ጋር አንታኮስም ብለው እራሳቸውን ሲያቀርቡ በባሕርዳር የተሰገሰገው የጸረ አማራው ኦነጋዊው ኦህዴድና ትህነግ ፍጹም አገልጋይ በሆነው ብአዴን እንዲታሰሩ ከመደረጉም በላይ ልጆችህን ለጠላት ወገን አሳልፎ በመስጠት ወደ አዲስ አበባና ወደ ኦሮሚያ የማሰቃያ እስርቤቶች ለመውሰድ ጃንደረባው ብአዴን ወስኗል።
ይህንን የጸረ አማራ ሃይሎችን ሴራና ውሳኔ የምታከሽፈው ደግሞ አንተው ታላቁ የአማራ ሕዝብ በመሆንህ መላው የአማራ ሕዝብ በሙሉ – በተለይም የአማራ ወጣት በሙሉ ፋኖዎቻችንን ከባሕርዳር አውጥቶ ወደ ኦሮሚያና ወደ አዲስ አበባ የመውሰድን እርምጃ በንቃት ተከታትላችሁ የማክሸፍና ፋኖዎቻችንን የመጠበቅ ታላቅ ኃላፊነት ተጥሎባችኋል።
- ጋሻ አማራ – ዓለም አቀፉ የአማራ ሕዝባዊ ኋይል-ፋኖ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በአርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴና ባልደረቦቹ ላይ የተፈጸመውን የብአዴንን ክህደታዊ የእስር እርምጃን በጽኑ እያወገዘና እየኮነነ መላው የአማራ ሕዝብ ፋኖዎቹን ነጻ የማውጣትና ብሎም ነጻነቱን ማረጋገጫ ሁሉን አቀፍ ትግል አጠንክሮ እንዲያቀጣጥል ጥሪውን እያቀረበ – በዚህ ጉዳይ ላይ በምንሰጠው ተከታታይ የትግል አቅጣጫ መጠቆሚያ መግለጫዎቻችን ሕዝባችን ቀድሞ እንዲረዳ ከወዲሁ ልንገልጽ እንወዳለን።
- ጋሻ አማራ – ለመላው የአማራ ሕዝብ ታጣቂ ኋይሎች – ማለትም ለአማራ ልዩ ኋይል፣ ለአማራ ሚሊሺያ፣ ለአማራ ፖሊስና ለአማራ ተወላጅ ለሆናችሁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ አፈሙዛችሁን በጸረ አማራና በጸረ ኢትዮጲያ በሆነው ኦህዴድ/ብአዴን መራሹ የብልጽግና ደም አፍሳሽ ቡድን ላይ በማድረግ ሕዝባችሁን ከጥፋት እንድትታደጉ – ወንድሞቻችሁ የሆኑትን ፋኖዎችን ከጠላት ጥቃት እንድትጠብቁ አበክረን ጥሪ እናቀርባለን።
- ጋሻ አማራ – በዳያስፖራ ላለው መላው የአማራ ተወላጅ ዘርፈ ብዙ ማህበራት፣ ድርጅቶች፣ አንቂዎችና ጋዜጠኞች የምናስተላልፈው ጥብቅ ጥሪ ሕዝባችን ጠላትነቱ በለየለት የብአዴን ቡድን መጠን ሰፊ ጥቃት የተከፈተበት ሕዝብ ነው። ይህንን ጠላታችንን መላው የአማራ ሕዝብ በሀገር ውስጥና በውጪም ሀገር ያለው በአንድነት የአማራ ብልጽግና/ ብአዴን ሊለወጥና ሊሻሻል የማይችል የነገደ አማራ ቁጥር አንድ ጠላት መሆኑን አውቀን እና ጠላትነቱን በግልጽ አውጀን በጋራ እንድንታገለው ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የአማራን ፋኖ በማሰር፣ የአማራን ታጋይ አመራር በማሰር የአማራን ትግል ማስቆም አይቻልም።
አማራው ባሉት ቆራጥ ተተኪ ልጆቹ እየተመራና እየታገለ የነጻነት ትግሉን እስከድል ድረስ በጽናት አጠናክሮ በመንቀሳቀስ ፍጹማዊ ነጻነቱን ይጎናጸፋል።
- ጋሻ አማራ – መላው የአማራ ሕዝብ በእነ አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴ መታሰር ጉዳይ ላይ በሀሳብና በአቋም መለያየት እንደሌለበትና በአንጻሩም ፋኖዎቻችን በአሁኑ ሰዓት በባሕርዳር 08 ቀበሌ በሚገኘው 2ኛ ጣቢያ የታሰሩ መሆናቸውንና ያሰራቸውም የአማራ ክልል ብልጽግና / ብአዴን መሆኑን በመገንዘብ በቀጥታ የትግላችንን አትኩሮት በመላው የብአዴን መዋቅር ላይ ያነጣጠረና ጀግኖቻችንን እሳቤ ውስጥ ያስገባን ትግል በጋራና በአንድነት ልናቀጣጥለው እንደሚገባን በአንክሮ እንግልጻለን።
በተባበረ የአማራ ክንድ ጸረ አማራ የሆነውን ብአዴንን ታግለን እናስወግዳለን!!!
መስከረም 11 ቀን 2015 ዓ/ም
ጋሻ አማራ