የአማራ ተማሪዎችን የ12ኛ ክፍል ውጤት መበላሸት ተከትሎ ተማሪዎቹ ፍትህ የሚያገኙበትን መንገድ በማፈላለግ የአማራ ተማሪዎች ማህበር (አተማ) ግንባር ቀደም ሚና ሲጫወት ሰንብቷል። ከነዚህ ስራዎቹ አንዱ በዛሬው እለት በአማራ ክልል መዲና ባህርዳር የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ማዘጋጀትና ማስተባበር ነው።
የማህበሩ ሰብሳቢ ተማሪ እሸቱ ሲደክምበት የሰነበተውን ሰልፍ ለመታደም ትናንት ቅዳሜ ባህርዳር ከተማ ለመግባት ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ባህርዳር ኤርፖርት ሲደርስ የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች ሁለት እጆቹን ጠፍረው ባህርዳር አባይ ማዶ ወደ ሚገኘው ፖሊስ ጣቢያው ወሰዱት። በታሰረበት የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በአካል ተገኝተው “አሁን ወደ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን( አሚኮ) ሄደህ ሰልፉ እንደቀረ ተናገር ካልሆነ ወደ እስር አቤት ትገባታለህ” እያሉ ማስፈራራት ጀመሩ።
እነ ይልቃል አማራውን ከማፈን የሚቀድም ስራ ስለሌላቸው ነው የልጅ ልጃቸው የሚሆነውን ትንሽ ልጅ ለማስፈራራት የተጣደፉ የመጡት።ይሄኔ አማራ ሞተ ተፈናቀለ ቢባል እየተጣደፉ ሊመጡ ቀርቶ “ፅንፍ አትያዙ” የሚል ምክር ነገር ወርውረው ወደ ወንበራቸው ነበር!
ሆኖም ተማሪ እሸቱ “የፈለጋችሁትን አድርጉኝ እንጅ ይሄን አላደርግም” ሲል በድፍረት ይሞግታል። “ዝነኛው” ተናጋሪ ዶ/ር ይልቃል “እኔኮ ታላቅህ ነኝ፣የምልህን ልትሰማኝ ይገባል” ሲሉ በቀደም በፖርላማው የተናገሩትን አይነት ጨዋታ አመጡ። “ታላቅነትዎትን ብቻ ሳይሆን ወንበርዎትንም አከብራለሁ፣የሚሉኝ ነገር ግን የመከባበር ሳይሆን የህይወት ጉዳይ ነውና ላደርገው አልችልም፣እርስዎ የሚያደርጉትን ለመቀበል ግን ዝግጁ ነኝ” ሲል የልበ ሙሉ ሰው መልስ ሰጥቷል።
ባለስልጣኑም ማድረግ የሚችሉት ማሰር፣ማፈን፣መርገጥ ነውና ተማሪ እሸቱ ከታች በምታዩት መንገድ እስር ቤት ወርውረውታል። ተማሪው ይፈታ ዘንድ ድምፅ ልንሆነው ይገባል! ካልሆነ ፍትህ ለጎደለበት የሚሟገት ማጣት ይመጣል…..
መረጃውን የሰጡኝ ዛሬ እሸቱ የታሰረበት ድረስ ሄደው ጠይቀውት ነገሩን ከራሱ አፍ የሰሙ ጓደኞቹ ናቸው።