0 0
Read Time:42 Second

የአማራ ሰማዕታት
ይሰራላቸው ሐውልት

ይጠራ ስማቸው የሁሉም ከነአባት
ወልቃይት ፤ጠገዴ እንዲሁም በጠለምት
በግፍ ለተፈጁት በትነግ ሰራዊት።

ይጠራ ዘር ስማቸው የሁሉም ከነአባት
ወተር ፤ጉራፈርዳ አንዲሁም በአሰቦት
በግፍ ለተፈጁት በኦነግ ሠራዊት።

ይጠራ ስማቸው የሁሉም ከነአባት
ጎደር አደባባይ ወልደያ ለሞቱት
በድፍረት በወኔ በክብር የወደቁት።

ይጠራ ስማቸው የሁሉም ከነአባት
በአጋዚ ስናይፐሮች ባሕርዳር ላለቁት
በጠላቶች ሴራ በግፍ የተቀጩት።

ይጠራ ስማቸው የሁሉም ከነአባት
በአጣየ በደራ ፤በመንዝና ተጉለት
ለማንነት ሲሉ ተዋድቀው የቀሩት።

ይጠራ ስማቸው የሁሉም ከነአባት
“በቤንሻንጉል ጉምዝ” በዛ መርዛማ ቀስት
በአማራነታቸ ብቻ በስቅይ ያለፉት።

ይጠራ ስማቸው የሁሉም ከነአባት
በመርዝና ጥይት በግፍ የተፈጁት
እንደ በግ በካራ በግፍ የታረዱት።

ይጠራ ስማቸው የሁሉም ከነአባት
በማእከላዊና በቅሊንጦ እሥርቤት
በአርመኔ ድርጊት በግፍ ግፍ የሞቱት።

ይዘር ዘር ስማቸው የሁሉም ከነአባት
በምድረ ኢትዮጵያ የሆኑት መስዋእት
በአማራነታቸው ብቻ በግፍ የተፈጁት።

ይጠራ ስማቸው የሁሉም ከነአባት
በአውሮጳ አሜሪካ በሁሉም አለማት
ወገን! ወገን ሲሉ ዘላለም ያረፉት።

እውነተኛ ዳኞች እስቲ ተሰየሙ
አኖሌን መርምሩ አማራንም ስሙ
ታሪክ ለፍርድ ይቅረብ ክርክሩን ስሙ።

መረጃ፤ ማስረጃ ይቅረብ ከያለበት
ይሰማ ድምጻቸው አሁን ያሉ ህይውት
ስንት ንጹህ አልቋል ለአማራ ማንነት።

በሉ እናስባቸው ሀሉንም በየአመት
መስዋዕት ሆነዋል ለአማራ ማነት
ትውልድ እንዳይረሳም ይሰራላቸው ሐውልት።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator