ከአማራ ሕዝባዊ ግንባር የተሰጠ መግለጫ
መነሻችን የአማራ ህልውና፣ መዳረሻችን የኢትዮጵያ አንድነት!
(ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ/ም)

በአማራው ሕዝብ ሕልውና እና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የተደቀነው አደጋ ወደ ከባድ ምዕራፍ ተሸጋግሯል። በሀሰት ትርክትና በጭፍን ጥላቻ የሚነዳው ጽንፈኛው የኦሮሙማ ፖለቲካ ታላቋን ኦሮሚያ ለመፍጠር ስትራቴጂካዊ ግብ አስቀምጦ ተግባራዊ እንቅስቃሴ
በማድረግ ላይ ይገኛል።

ብልፅግና ፓርቲን የተቆጣጠሩት እና በዐብይ አህመድ የሚመሩት አክራሪ የኦሮሞ ብሄርተኞች “ታላቋ” የሚሏትን ኦሮሚያ ለመፍጠር በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጽሙትን የዘር ፍጅት (ጄኖሳይድ) በማስፋፋት እና አዋሳኝ የሆኑ ክልሎችን ወርረው መሬት ለመቀማት እየተንቀሳቀሱ ነው። በዚህ ሂደት ሰለባ እንዲሆኑ ካሰቧቸው መካከል ከአማራ ክልል በተጨማሪ ሲዳማ፣ አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤንሻንጎል፣ ጌዴዮ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ፣ ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ ይገኙበታል። “አገረ ኦሮሚያ የባህር በር ያስፈልጋታል” ብለው ስላመኑም፣ የሶማሌ ክልልን ለሁለት ቆርጠው ወደ ቀይ ባህር ለመዝለቅ ዕቅድ አዘጋጅተዋል። አዲሲቷ ኦሮሚያ ከሌላ ብሔሮች የጸዳች ብቻ ሳትሆን፣ ከኦርቶዶክስ እምነትና ከነባሩ እስልምና የጸዳችም
እንድትሆን አልመው በመስራት ላይ መሆናቸው ፀሐይ የሞቀው ሃቅ ነው።

ባለፉት አምስት ዓመታት በተበታተነ መልኩም ቢሆንም ውጥናቸውን ተግባራዊ ለማድረግ በተደረገ እንቅስቃሴ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አማራዎች በኦሮሚያ ክልል የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ የመፈናቀል እና የጅምላ ግድያ ሰለባ ሆነዋል። በሀገራችን ላይ ያንዣበበው አደጋ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እነዚህ ተጨባጭ ማስረጃዎች ናቸው። ሁኔታዎች በዚሁ ከቀጠሉም የወደፊት እጣ ፈንታችን ከሩዋንዳ የዘር እልቂት የከፋ እንደሚሆን
በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል።

ይህንን በመላው ኢትዮጵያ፣ በተለይም የውጥኑ ዋና እንቅፋት ይሆናል ተብሎ በተሰጋውና የዘር-ፍጅት (ጄኖሳይድ) በታወጀበት የአማራ ሕዝብ ላይ የተነሳውን ከባድ አደጋ ለመቀልበስ የሚያስችል ሀገራዊ እና ሕዝባዊ ትግል የመጀመሪያ ምዕራፍ የሚያቀናጅ የአማራ ሕዝባዊ
ግንባር (Amhara Popular Front) ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

የግንባሩ ዓላማ:-

  1. የአማራ ሕዝብ ራሱን ከጅምላ ፍጅት (ጄኖሳይድ) ለመከላከል የሚያደርገውን የህልውና ትግል ቀዳሚ መነሻ ማድረግ፤
  2. የአማራ ሕዝብ የህልውና ማስጠበቅ ትግል መዳረሻው የኢትዮጵያን እንደሃገር ለሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለፍ፣
  3. ለአማራ ሕዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ የህልውና ስጋት የሆነውን ህገ-መንግስት ለኢትዮጵያ ሕዝብ አብሮነት ዋስትና በሚሰጥ መንገድ እንዲሻሻል ማድረግ፤
  4. በሕዝባዊ ትግል ነፃ በሚወጡና የብልፅግና ፓርቲ አስተዳደር በሚፈረሰባቸው ቦታዎች ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከፋኖ እና የሕዝቡን ትግል ከተቀላቀሉ የመንግሥት ሹማምንት በተውጣጡ አካላት የአካባቢ አሥተዳደሮችን መመሥረት፤
  5. በሚቋቋሙት የአካባቢ አሥተዳደሮች አማካኝነት የሕዝብን ሠላም፣ ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ፀጥታ ማስጠበቅ፤
  6. በአማራ ሕዝብ ላይ ያንዣበበውን የጅምላ የዘር ፍጅት (ጄኖሳይድ) እና የሀገር ብተናን አደጋ ለመግታት ከሚንቀሳቀሱ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ኃይሎች ጋር ተባብሮ መስራት ናቸው።

በአብይ አህመድ የሚመራው የብልፅግና ፓርቲ ብቃት እና ሕዝባዊ መሠረት የሌለው፣ ከእውቀት የፀዳ፣ በጥላቻ የተመረዘ፣ ለሰው ልጅ ክብር የሌለው እና ሙሰኛ ድርጅት ነው። ህወሓት-መራሽ በሆነው የኢህአዴግ ዘመን የነበረውን ሥርዓት በከፋ ሁኔታ አጠናክሮ አስቀጠለው እንጂ አለወጠውም።

በኢህአዴግ ዘመን የነበረው የኦህዴድ አገዛዝ ለ27 ዓመታት ለኦሮሞ ሕዝብ ጠንቅ ሆኖኖሯል። የአሁኑ የኦህዴድ ብልፅግና ፓርቲ ደግሞ ይህንን የክህደት ታሪኩን ለማስረሳት እና ሕዝብን ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመቸው ሥርዓቱን የኦሮሞ ሕዝብ ሥርዓት በማስመሰል የኦሮሞን ሕዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በሐሰት ትርክት እያጋጨ፣ በስጋትና በጥርጣሬ እንዲታይ እያደረገው ይገኛል። የኦሮሞ ሕዝብ ከዚህ ውጥንቅጥ እንደማያተርፍ
ካለፈው የህወሓት ኢህአዴግ ሥርዓት ውድቀት ተምሮ አሰላለፉን ከሌላው ኢትዮጰያዊ ወገኑ ጋር ማድረግ ይገባዋል።

ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ሠላምና አንድነት ተጠቃሚው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው። የብልፅግና ፓርቲ ዘረኛና ኋላቀር አገዛዝ ሀገርን ከማፍረሱ በፊት መላው ኢትዮጵያዊ በጋራ በመቆም ሀገር የመታደግ ታሪካዊና ሕዝባዊ አደራን መወጣት ይኖርበታል። ይህን አደራ ለመወጣት
የአማራ ሕዝብ ግንባር በበኩሉ በሙሉ ኃይሉ ይንቀሳቀሳል።

በመጨረሻም፣ የምስረታውን ዜና በሚያበስርበት በዚች ዕለት፣ የአማራ ሕዝባዊ ግንባር የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል፡ –

  1. የአማራ ሕዝብ ሆይ! ከተከፈተብህ የጅምላ የዘር ፍጅት (ጄኖሳይድ) ራስህን ለመከላከል ከሕዝባዊው ፋኖ እና ሌሎች መሰል አደረጃጀቶች ጎን እንድትቆም፣ ቀሪው የኢትዮጰያ ሕዝብም ለዚህ የፍትህ ትግል በሙሉ ኃይልህ እንድትተባበር፤
  2. የመከላከያ፣ የአማራ ክልል ልዩ ሃይልና ሚሊሺያ፣ የፖሊስ እና የአድማ ብተና አባላት ሆይ! በራሳቸሁ ሕዝብ ላይ እንድትተኩሱ የሚሰጠውን ትዕዛዝ እንዳትቀበሉ፣ በማንነትም ሆነ በሐይማኖት እንዳትከፋፈሉ፤
  3. የሐይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ሆይ! ከአብራኩ ከወጣችሁት ሕዝብ ትግል ጎን እንድትቆሙ፤
  4. የፖለቲካ ድርጅቶች ሆይ! የቆማችሁለትን ዓላማ በተለያዩ ሰበብ አስባቦች ከመክዳት ተቆጥባችሁ፣ የሕዝቡን ትግል በአግባቡ እንድትመሩ፤
  5. የሲቪክ ተቋማት፣ የሙያና የሠራተኛ ማህበራት ሆይ! ራሳችሁን ከገዢው ፓርቲ ተፅዕኖ ነፃ በማውጣት ከትግሉ ጎን እንድትቆሙ፤
  6. በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጰያዊያን ወይም ዲያስፖራ ሆይ! በሀገር ቤት ውስጥ ለፍትህ እና ለዘላቂ ሰላም የሚደረጉትን ትግሎች በሙሉ ኃይላችሁ እንድትደግፉ፣
  7. የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጰያ ለተፈፀሙት እና በመፈጸም ላይ ላሉት የጅምላ የዘር ጭፍጨፋዎች በገለልተኛ አካል እና በሐቀኝነት አጣርቶ ፈጻሚዎቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን!

የአማራ ሕዝባዊ ግንባር

ሙሉ መግለጫው

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator