0 0
Read Time:54 Second

የአማራው የዘር ፍጅት እንዲቆም በሚጠይቀው፣ 13ተኛ ቀኑን በያዘው የለንደኑ የርሃብ አድማ ያየሽይራድ ገሠሠ ከርሃቡ ጋር በተያያዘ ጉዳት የደረሰባት መሆኑን ተከትሎ አስቸኳይ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ነው።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሀምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

የአማራው የዘር ፍጅት እንዲቆም በሚጠይቀው፣ 13ተኛ ቀኑን በያዘው የለንደኑ የርሃብ አድማ ያየሽይራድ ገሠሠ ከርሃቡ ጋር በተያያዘ ጉዳት የደረሰባት መሆኑን ተከትሎ አስቸኳይ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት መሆኑን ካጋሩት ላይቭ የቪዲዮ መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

ሰውነቷ ዝሎ አቅም ሲያንሳትና ስትዝለፈለፍ ታይቷል፤ አምቡላንስ ይዘው በመጡ የጤና ባለሙያዎች የድንገተኛ ህክምና ትብብር ሲደረግላትም ተስተውሏል።

በሲዊትዘርላንድ የስቶፕ አማራ ጄኖሳይድ ዳይሬክተር የሆነችው ዮዲት ጌዲዮን በ12ኛ ቀኗ በደምሽ ያለው የስኳር መጠን በአደገኛ ሁኔታ ቀንሷል በሚል የጤና ባለሙያዎች በሰጧት ምክረ ሀሳብና ትዕዛዝ የርሃብ አድማውን በማቆም በአደባባይ ድምፅ ወደመሆን እንቅስቃሴ መሸጋገሯ ይታወቃል።

እነዚህ ብርቱ ሴት ታጋዮች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በኢትዮጵያ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የዘር ፍጅት እንዲቆም በማውገዝና በማጋለጥ የሚታወቁ ናቸው።

በዚህ የርሃብ አድማም በለንደን ከሚገኙ አማራዎችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመሆን ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ከማሰማታቸው በተጨማሪ በዩኬ ቤተ መንግስት ግቢ ፊት ለፊት ለ13 ቀናት የዘለቀ፣ ብዙዎችን ያነጋገረ እና ታጋዮችን ያስመሰገነ የርሃብ አድማ በማድረግ ከተገፉ ወገኖች ጎን መሰለፋቸውን አሳይተዋል።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator