የአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ “የተደረገብንን አንረሳም!” በሚል መሪ ቃል በመጪው ሰኞ ሰኔ 19/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት(3) ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የትምህርትና የስራ ማቆም አድማ በመላው አማራ ክልል ጠርቷል ።

በዚህም የትምህርትና የስራ ማቆም አድማ (ጥሞና) በኦሮሙማ ፋሽስት አገዛዝ በግፍ ለተረሸኑ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን እና የኦርቶዶክስ መነኮሳት ፣መናንያን ፣ቀሳውስት እና አማኞች በህሊና ፀሎት ታስበው ይውላሉ ።ከሰኔ 19/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀናት የህሊና ፀሎትና የሻማ ማብራት መርሃ ግብር በእዬ ቤታችን ይካሄዳል ።በአገዛዙ በአራቱም ማዕዘን በግፍ ለተጨፈጨፉ አማራ ወገኖቻችን የህሊና ፀሎት ይደረጋል ።

ባለፉት ሁለት ወራት “ህልውናችን በክንዳችን!” በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የቆየው በሁለት ምዕራፍ የተካሄደው የሰፊው የአማራ ህዝባዊ እምቢተኝነት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል ። በእነዚህ ሁለት ምዕራፎች ህዝባዊ እንቅስቃሴው አድጓል ወደ ተሻለ ደረጃ ደርሷል ።

በመጪው ሰኞ የተጠራው የአማራ ህዝባዊ እምቢተኝነት ሶስተኛው ምዕራፍ ነው ።በዚ አድማ ያነሳናቸው ሕዝባዊ ጥያቄዎች ከአገዛዙ ምላሽ ካላገኙ በቅርብ ጊዚያት ውስጥ ወሳኝ የሆነውንና ምን አልባትም የመጨረሻውንና ህልውናችን የምናስከብርበትን አራተኛውን የትግል ምዕራፍ ስለምንጀምር ሁሉም የስነ ልቦናና የአካል ዝግጅት እንዲያደርግ እግረ መንገዳችን እናሳስባለን!!፣

የአማራ ህዝባዊ እምቢተኝነት ጥያቄዎች ፦

1).በመከላከያ ሰራዊት ስም የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ የሚገኘው ወራሪው የኦሮሙማ ኦነግ ስራዊት በአስቸኳይ ክልሉን ለቆ እንዲወጣ

2).አማራ በመሆናቸው ብቻ በአገዛዙ በግፍ እሰር ላይ የሚገኙ የአማራ መሪዎች ፣ምሁራን ፣ጋዜጠኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ

3)በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረገው ሁሉን አቀፍ የዘር ፍጅት ይቁም

4).የአማራ ህዝብ በነፃነት የመዘዋወር መብቱ ይከበር ።በሚሊዮን ወገኖቻችን ላይ በአዲስ አበባ ፣በኦሮሚያ የሚደረገው ቤት ፈረሳ እና ማፈናቀል ይቁም

5).የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ በአስቸኳይ መፍትሄ ይሰጠው

6).ሸገር ከተማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚደረገው የመስጊድ ፈረሳ እና ከዚህም ጋር ተያይዞ የሙስሊም ወገኖቻችን ላይ የሚደረገው ወከባ ፣እስራት እና ግድያ በአስቸኳይ ይቁም

7).ደብረ ኤልስ ገዳም ጨምሮ በሌሎች የኦሮቶዶክስ እምነት ተቋማት ፣ምዕመናን ፣ቀሳውስት ፣ገዳማውያን ፣መነኮሳት እና አማኞች ላይ የሚደረገው ማውደምና ጭፍጨፋ ይቁም

😎.የአማራ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ የማግኘት መብታቸው እንዲረጋገጥ

9).በቀጣይ አመት ጀመሮ አዲስ ቅጥር አልፈፅምም ያለው መንግስት የተመራቂ ተማሪዎችን ጉዳይ አንደገና እንዲያየው

10).በመላው የንግድ ማህበረሱ ላይ በተለይም የአማራ የንግድ ማህበረሰብ ላይ ሆን ተብሎ ያለ አግባብ ግብር መጨመር እና በህዝቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ውድነትን በአገዛዙ እንዲኖር መደረጉን በመቃወም

11).ከኢትዮጵያ ህዝብ እውቅና ውጭ ንብረትነታቸው የህዝብ የሆኑ የንግድ መርከቦች ሽያጭ እንዲሁም አርቆ አሳቢ ብርቱ ቀደምት አባቶቻችን ያቋቋሙት አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ለመሸጥ የሚደረግ ድርድርን እንዲቆም

12).ከኢትዮጵያ ህዝብ ወግና ባህል ባፈነገጠ መልኩ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ፣አሽከርካሪዎች ላይ እና አገር አማን ብለው ከቦታ ቦታ በሚንቀሳቀሱ የአማራ ወገኖቻችን ላይ የሚፈፀመውን መንግስታዊና ስርዓታዊ ድጋፍ ፣እውቅና ያለው አፈና እና ደብዛ ማጥፋት እንዲሁም የማስለቀቂያ ገንዘብ መጠየቅ አስነዋሪ ተግባርን እንዲቆም

ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግስታዊ እና ስርዓታዊ በሆነ ሁኔታ ፀረ አማራነቱን በይፋ ያወጀው የብልፅግና መንግስት የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች አልቀበልም በማለት የአማራ ህዝብ መሪዎችን ፣ጋዜጠኞችን እና ምሁራን አስሯል ፤ጀግናው የአማራ ልዩ ሀይልን በትኗል ፤በመከላከያ ፣በፌደራል ፓሊስና በአዲስ አበባ ፓሊስ ውስጥ የሚገኙ የአማራ ተወላጅ አባላትን ወከባ እና እስራት ፈፅሟል ፤በአማራ የቁርጥ ቀን ደጀን በሆነው እና በአማራዊ እሴት በታነፀው ፋኖ ላይ ዘመቻ አውጇል ፣የስርዓቱ ታዛዥ የሆኑ ሰራዊት አዝምቶ በከባድ መሳሪያ ፣በድሮን እና በጀት ጥቃት እየፈፀመ ይገኛል ፤ቤተክርትያናት ፣ገዳማትን እና መስኪዶችን በከባድ መሳሪያ ደብድቧል ፣በዶዘር አፍርሷል ።በአጠቃላይ ክልላችን አገዛዙ የጦር ቀጠና አድርጎታል ።

በመሆኑም እነዚህን ድርጊቶች የምንቃወማቸው እና የምንታገላቸው በመሆኑ መላው የአማራ ህዝብ ከመጪው ሰኞ ሰኔ 19/2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉ ሶስት (3) ተከታታይ ቀናት

1ኛ.በሁሉም የግል ፣የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ ከአንደኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ያሉ የትምህርት ተቋማት የትምህርት ማቆም አድማ ያደርጋሉ

2ኛ.ሁሉም የግልና የመንግስት ተቋማት የስራ ማቆም አድማ ያደርጋሉ

3ኛ.የትራንስፖርት አገልግሎት ይቆማል

4ኛ.መላው የአማራ ህዝብ በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ያደርጋል

5ኛ.የህክምና ተቋማት ለድንገተኛ እና ለተመላላሽ ታካሚዎች ብቻ ክፍት ይሆናሉ

ስለሆነም መላው ህዝባችን ይህንን አድማ ለመፈፀም እና ለማስፈፀም እንዲዘጋጅ የአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ ጥሪውን ያስተላልፋል ።ከላይ የተጠቀሱትን እገዳዎች ወይም ክልከላዎች ተላልፎ የሚገኝ ለሚደርስበት ሁሉ ሃላፊነቱን እራሱ ይወሰዳል ።

የተደረገብንን አንረሳም‼️

የአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ

ሰኔ 17/2015 ዓ.ም

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator