0 0
Read Time:5 Minute, 51 Second

እ.ኤ.አ. በ1861 ዓ.ም. በአሜሪካን አገር የተቀሰቀሰው የርስ በርስ ጦርነት መንስዔ የባርነት ሥርዓትን ለመልቀቅና የባሪያን ነጻነት ለመስጠት ባለመፈለግ በየአቅጣጫው ተቃውሞ በመነሳቱ ነበር። ጦርነቱ በዋናነት የተካሄደው በሰሜን የአሜሪካ የአንድነት ኃይልና በደቡብ የአሜሪካ ተገንጣይ የኮንፈደራል ኃይል መካከል ሲሆን የርስ በርስ ጦርነቱ ባርነት እንዲወገድ በሚፈልጉ ሰሜንና ባርነት ሥርዓታዊ እንዲሆን በሚሹ ደቡብ አሜሪካኖች መካከል የተካሄደ ነበር። የባርያ ነጻነትን የማይፈቅዱት የደቡብ የአሜሪካ ክፍል ባሪያ አሳዳሪዎች የባርያ ሥርዓትን የሚቃወመው አብርሐም ሊንከን ፕሬዝደንት ሆኖ ሲመረጥ በአላባማ ግዛት ሞንገመሪ ከተማ ላይ ታላቅ ስብሰባ አድርገው ጀፈረሰን ዴቪስ የሚባለውን ባርያ አሳዳሪ ፕሬዝደንት አድርገው በመምረጥ የባርያ ሥርዓታቸውን ተገንጥለው ለማስቀጠል “ኮንፌደረት እስቴት ኦፍ አሜሪካ” ብለው የራሳቸውን አገር በመሰየም መደቡ ቀይ የሆነ ባንዲራ አዘጋጅተው ራሳቸውን ማስተዳደር ጀመሩ። የአብርሐም ሊንከንን ውሳኔም በመቃወም እ.ኤ.አ. በሚያዚያ 12 ቀን 1861 ዓ.ም. የርስ በርስ ጦርነቱን ጀመሩ።

የተገንጣዩ የደቡብ “ኮንፌደረት እስቴት ኦፍ አሜሪካ” ፕረዝደንት ሆኖ የተመረጠው የጀፈርሰን ደቪስ አዝማች ጀኔራል ሮበርት ኢ.ሊ. ነበር። በጣም ታዋቂ የሆኑት ሁለቱ የሰሜኑ ክፍል አዝማቾች ደግሞ ጀኔራል ዩልየስ ግራንት እና ጀኔራል ሸርማን ነበሩ። ለሁለት ዓመታት የተካሄደው የርስ በርስ ጦርነት የተጠናቀቀው በፔንሲልቫኒያ ጌትስበርግ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 3 ቀን 1863 ዓ.ም. በተደረገው ጦርነት የደቡቡ ኮንፈደሬት ጦር ሠራዊት አዛዥ ሮበርት ኢ.ሊ. የሚመራው ጦር በድል ከተመታና ወደ ትውልድ ቦታው የኮንፌደሬቱ ዋና ከተማ ወደነበረችው ወደ ቨርጂኒያ ሪችመንድ ከሸሸ በኋላ በጦርነቱ መቀጠሉ ጥቅም የሌለው መሆኑን ተገንዝቦ ለባሮች ነጻነትና እኩልነት ይታገል ለነበረው ለአሸናፊው የሰሜን የአንድነት ኃይል እጁን ሲሰጥ ነው።

የቨርጂኒያ ክፍለ ሀገር አስተዳዳሪው ዲሞክራቱ ራልፍ ኖርትሃም ከሰሞኑ በአሜሪካ ግዛቶች የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት በማድረግ የባሮችን እኩልነት ባለመቀበል አሳፋሪውን የባርነት ሥርዓት ለማስቀጠም የኮንፈደሬት ጦር ሠራዊትን እየመራ ለሁለት ዓመታት ለባሮች ነጻነትና አኩልነት ይታገሉ የነበሩ የሰሜን አሜሪካ የአንድነት ኃይሎችን የወጋውን የባሪያ አሳዳሪውን የጀኔራል ሮበርት ኢ.ሊ.ን ሐውልት እንዲወገድ መወሰኑን ተከትሎ ገዳ የሚባለው የባሪያ አሳዳሪዎች ሥርዓት አቀንቃኞቹ ኦነጋውያን “የጀኔራል ሮበርት ኢ.ሊ. ሐውልት ከተነሳ የምኒልክ ሐውልትም መነሳት አለበት” የሚል አዲስ ዘመቻ ጀምረዋል።

ኦነጋውያን በዳግማዊ ምኒልክ ጥላቻ ጥንቢራቸው የዞረና የማይድን የዝቅተኛነት በሽታ ተጠቂ የሆኑ ግብዞች ስለሆኑ ባሪያ አሳዳሪው ጀኔራል ሮበርት ኢ.ሊ. እና በዋናነት በኦሮሞ የአካባቢ ገዢዎች ይካሄድ የነበረው የባሪያ ንግድ እንዲጠፋ አዋጅ የደነገጉት ባሪያ ነጻ አውጭው ዳግማዊ ምኒልክ ተቃራኒ ሰዎች እንደሆኑ እንኳ የማያውቁ የማንነት ቀውስ ያደደባቸው የእውቀት ጾመኞች ናቸው።

ባሪያ አሳዳሪውና የባሪያን እኩልነት የማይቀበለው አሜሪካዊው ጀኔራል ሮበርት ኢ.ሊ. ኢትዮጵያ ውስጥ ወደረኛ ይፈለግለት ከተባለ የሚቀርበው በምስራቅ አፍሪካ ወደር የማይገኝለት ባሪያ ነጋዴ የነበረው የጅማው ንጉሥ አባ ጅፋር እንጂ “ይድረስ ካባ ጅፋር ከጃንጃሮ ወዳንተ አገር የመጣውን ጋላ እንግዲህ ከእጄ ከገባልኝ ብለህ ጭቡ አድርገህ ባርያዬ ነህና አንተንም ልበድልህ፣ ልጅህንም አምጣና እንደከብት ልሽጠው ፣ ልለውጠው አትበል። ይህን ያህል ዘመን አባቶቻቸው ከአባቶችህ፣ ልጆቹ ካንተ ጋር አብረው ኑረው ባሪያ ሊባሉ አይገባም። ባደባባይም ባርያዬ ነው እያልክ አትሟገት። የሰው ባርያ የለውም። ሁላችንም የእግዚአብሔር ባርያዎች ነን።” የሚል የእኩልነት መልዕክት ያዘለ አዋጅ ከአዲስ አበባ በባሪያ ንግድ ክብረ ወሰን ወደተቀዳጀው ወደ አባ ጅፋር የላኩት አጼ ምኒልክ አይደሉም።

ስለዚህ የባሪያ አሳዳሪው ጀኔራል ሮበርት ኢ.ሊ. ሐውልት ስለፈረሰ ኢትዮጵያ ውስጥም ሐውልት ይፍረስ ከተባለ መፍረስ ያለበት እንደ አብርሐም ሊንከን ባሪያን በአዋጅ ነጻ ያወጡት የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ሐውልት ሳይሆን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ባሮች የተፈነገሉበትና በምስራቅ አፍሪካ ወደር የማይገኝለቱ የባሪያ ነጋዴ የሆነው የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ነው።

አባ ጅፋርን በ1904 ዓ.ም. በሚኖርበት ጅማ ሄዶ የጎበኘው ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም አባ ጅፋር «ከአንድ ሚሊዮን በላይ የአካባቢውን ሕዝብ በባርነት ሽጦ እንደጨረሰ» ‘ኦቶባዮግራፊ [የሕይወቴ ታሪክ]’ በሚል ባዘጋጀው የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ አስፍሯል።

ሌላም ማስራጃ አለን። በ1916 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት [League of Nations] አባል ለመሆን ባመለከተችበት ወቅት በእንግሊዝ መንግሥት ከፍተኛ ተቃውሞ ቀርቦባት ነበር። የኢትዮጵያን መንግሥት የአባልነት ማመልከቻ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት [League of Nations] ለማስገባት ወደ ጀኔቫ የተላከው ቡድን መሪ የነበሩት ራስ ናደው አባ ወሎ በፈረስ ስማቸው «አባ መብረቅ» እንግሊዝ ኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ማኅበር አባል እንዳትሆን የተቃወመችበትን ምክንያት ለንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ በላኩት የቴሌግራም መልዕክት፤

«እንግሊዝ ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሐን የዘገቡትንና በሱዳን፣ በኬንያ፣ በኤደንና በግብጽ ባሉት የቅኝ ግዛት መንግሥቱ በኩል የሰበሰበውን ማስረጃ በማያያዝ በደቡብ ኢትዮጵያ እየተካሄደ ስለነበረው የባርያ ንግድ ሁኔታ፤ በተለይም የጂማው አባጅፋር በከፋ፣ በማጂ፣ በጊሚራና በጉራፈርዳ ሕዝብ ላይ እየካሄዱት ያለው መጠነ ሰፊ የባሪያ ንግድ ለማኅበሩ የፖለቲካ ኮሚሲዮንና ለጠቅላላ ጉባኤ በማቅረብ አባል እንዳንሆን ከፍተኛ ተቃውሞ አቅርቦብናል» ሲሉ አስረድተዋል።

ለዚህ የራስ ናደው አባ ወሎ ቴሌግራም የአልጋ ወራሽ ተፈሪ መኮንን መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ ሰጠ። ኢትዮጵያ ውስጥ በአባ ጅፋር አማካኝነት የሚካሄደው የባርያ ንግድ ባጭር ጊዜ ውስጥ ጨርሶ እንዲታገድና የሰው ልጅ መብት በመላው የአገሪቱ ግዛት እንዲከበር የአልጋወራሽ ተፈሪ መንግሥት ለመንግሥታቱ ማኅበር ቃል በመግባት ኢትዮጵያ ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ከመስከረም 17 ቀን 1916 ዓ.ም. ጀምሮ ኢትዮጵያ የመንግሥታቱ ማኅበር 57ኛ አባል ሆና መመዝገቧ በይፋ ታወጀላት።

አባ ጅፋር ጅማን ያስፋፉው በአካባቢው የነበሩ እንደ የም እና ጌራ አይነት ነገዶችን በመውረርና በማጥፋት የተረፈውን ሕዝብ ደግሞ ባሪያ አድርጎ በመሸጥ ነበር። አባ ጅፋር ባሪያ አድርጎ የሸጠው ኦሮሞን ጭምር ነበር። ለዚህ ማስረጃ ይሆን ዘንድ ከታች የታተመውን የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ደብዳቤ መመልከት ይቻላል። ዳግማዊ አጼ ምኒልክ አባ ጅፋር ሰውን ባሪያ እያሉ እንዳይጠቱ በተደጋጋሚ ትዕዛዝና ማስጠንቀቂያ ከዚያም እስከ እስር ድረስ ደርሰው ነበር።

ከአንድ ሚሊዮን በላይ የጅማን አካባቢ ሕዝብ ባሪያ አድርገው የሸጡትና የምስራቅ አፍሪካው ታላቁ የባሪያ ነጋዴ አባ ጅፋር ልጆች ነን የሚሉን ኦነጋውያን ናቸው እንግዲህ የባርያ ሥርዓትን ለመልቀቅና የባሪያን ነጻነት ለመስጠት ባለመፈለግ ጦርነት የከፈተው የጀኔራል ሮበርት ኢ.ሊ ሐውልት ሲፈርስ ስላዩ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያዊ በባርነት የሸጠው የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ተቀምጦ አባ ጅፋር የባሪያ ንግዱን እንዲያቆም፤ ፈንግሎ በባርነት ሰንሰለት ያሰራቸውን የልዩ ልዩ ነገዶች ባሮች እንዲለቅና ባሮች ነጻ እንዲወጡ አዋጅ ያወጡት የዳግማዊ አጼ ምኒልክ ሐውልት ይፍረስ የሚሉን!

በገዳ ወታደራዊ ዘመቻ ባሪያ የተደረገው ሕዝብ ተቆጥሮ አያልቅም። የኦሮሞ የገዢ መደብ ኢትዮጵያን ሲወር ጭሰኛ ተደርገው፤ ከመሬታቸው ተነቅለው ገርባ የተደረጉት ነባር የኢትዮጵያ የኦሮሞ ባሮች ነበሩ። ገርባዎች የኦሮሞ ባሮች ናቸው። ገርባ የሚለው የኦሮምኛ ቃል የአማርኛ ፍቺው ባርያ ወይንም አገልጋይ ማለት ነው። ጰለታ ማለት ኦሮሞ ገርባ ያደረገው ወይንም በሞጋሳና ሜዴቻ ማንነቱን ወደ ኦሮሞ የቀየረው ሰው ልጅ ማለት ነው። ኦሮሞ ያስገበራቸውን ነባር የኢትዮጵያ ነገዶች ገርባ እያለ እንደሚጠራቸውና ጭሰኛ አድርጓቸው እንደኖረ ማወቅ የሚሻ ቢኖር በኦሮሞ ታሪክ ጥናት ጥርሱን የነቀለው አሌክሳንድሮ ትሪውልዚ “Boorana and Gabaro among the Macha Oromo in Western Ethiopia” በሚል ያሳተመውን ድንቅ ምርምር ያንብብ። ልብ በሉ! ገርባው፣ ጰለታውና ዳለቻው ሁሉ ከኦሮሞ የገዢ መደብ ባርነት የተላቀቀው በዳግማዊ አጼ ምኒልክ አዋጅ ነው።

ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ነጻ ያወጡት ሕዝብ አገር ቤት በኦሮሞ ፊውዳሎች በባርነት የተያዘውን ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ውጭ የሸጡትን ጭምር ነው። ሳንድራ ሼል የሚባሉ ተመራማሪ «From slavery to freedom : the Oromo slave children of Lovedale, prosopography and profiles» በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ. በ2013 ዓ.ም. ያሳተሙት መጽሐፍ የኦሮሞ ባላባቶች ባሪያ አድርገው የሸጧቸውን የምዕራብ ኢትዮጵያ ነገዶች አባላት ዝርዝርና ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ደቡብ አፍሪካ ድረስ በመላላክ ገንዘብ ጭምር እየከፈሉ ነጻ እንዲወጡና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ስላደረጓቸው ገርባዎች፣ ጰለታዎችና ባሮች ይናገራል። ጥናቱ የኦሮሞ ባላባቶች ከደቡብና ምዕራብ ኢትዮጵያ ባሪያ አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሸጧቸውን ሰዎችና ዳግማዊ ምኒልክ ገንዘብ እየከፈሉ ያስለቀቋቸውን ባሮች ትውልዶች ጭምር አካቷል። በኦሮሞ ባላባቶች ከተሸጠበት ከደቡብ አፍሪካ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ገንዘብ ከፍለው ነጻ ያወጡት ያንዱ ሰው ትውልዶች በደርግ ዘመን ከኢትዮጵያ ወደ ካናዳ ተሰደው አሁንም ድረስ ካናዳ ውስጥ እንደሚኖሩ ጥናቱ ያሳያል።

ይህ ሁሉ የተመዘገባ ታሪክ ባለበት አገር የባሪያ አሳዳሪው የገዳ ሥዓት ናፋቂዎቹና በነውራቸው የማያፍሩቱ ኦነጋውያን ገንዘባቸውን ሳይቀር አውጥተው በኦሮሞ ባላባቶች ወደ ውጭ አገር ባርያ ተደርገው ከተሸጡበት አገር ነጻ እያወጡ ወደ አገራቸው ሲመልሱ የኖሩትን ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክን በባሪያ እኩልነትና ነጻነት ላይ ከሸፈተው ሮበርት ኢ.ሊ. ከተባለው ባሪያ አሳዳሪ ጋር ሲያመሳስሉ ትንሽ እንኳ አይሰቀጥጣቸውም።

ባጭሩ የባርነት ሥርዓትን ለመልቀቅና የባሪያን ነጻነት ለመስጠት ባለመፈለግ ሁለት ዓመታት ተዋግቶ በስተመጨረሻ ላይ የተማረከው ጀኔራል ሮበርት ኢ.ሊ. ኢትዮጵያ ውስጥ የሚመሳሰለው የባርያ ንግድ አላቆምም በማለቱ እስከመታሰር የደረሰውና ከአንድ ሚሊዮን በላይ ባሮችን የሸጠው የምስራቅ አፍሪካው ታላቅ የባሪያ ነጋዴ አባ ጅፋር እንጂ ባሪያ ነጻ አውጭውና “ደሀው እወደደው እተመቸው ቦታ ይደር” ያሉት ዳግማዊ ምኒልክማ የሚመሳሰሉት የባሪያ ነጻነትን ለማወጅ ከጀኔራል ሮበርት ኢ.ሊ. ጋር የተዋጋው አብርሐም ሊንከን ነው።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator