የህውሃት ወራሪ ቡድን በደቡብ ወሎ ገርባ አልነጃሽ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ60 በላይ የጅምላና የተናጥል መቃብሮች በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ቀብሮ ሸሽቷል፡፡

የአማራ ክልልና የአፋር ክልልን የወረራው አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በደቡብ ወሎ የገርባ አልነጃሽ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን የጦር ካምፕና የቁስለኞች የህክምና ማእከል አድርጎት ቆይቷል፡፡

ቡድኑ በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነባውን ትምህርት ቤት የጦር ከምፕ ከማድረጉም ባሻገር በውስጡ የነበሩትን ኮምፒውተሮች ዘርፏል፣ መጽሃፍትን በሙሉ አቃጥሏል፣ የቤተ ሙከራ ክፍሎችንም አውድሟቸው ሄዷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አሸባሪው ቡድን የትምህርት ቤቱን ግቢ ከእውቀት ገበያነት ወደ መካነ መቃብርነት ቀይሮታል፤ ትምህርት ቤቱ ውስጥ የሞቱ ወታደሮቹን አስክሬን ቀብሮበታል፡፡

ከ60 በላይ የጅምላና የተናጥል መቃብሮች በትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ ቀብሮ ሸሽቷል፡፡

በዚህም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት መጥተው ለመማር የስነ ልቦና ጫና ደርሶባቸዋል፡፡

መንግስት በትምህርት ቤታቸው ያሉ ቀብሮችን አንስቶ ወደ ቀብር ቦታ ተውስደው እንዲቀበሩ ትብብር እንዲያደርግላቸው ነዋሪዎች ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ:- ትምህርት ሚንስቴር

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator