ኩርዶች የጥንታዊውን የሞሶፖታሚያ ስልጣኔ የመሰረቱ፣ በመካከለኛው ምስራቅና ኤሲያ ማይነር በአምስት የተለያዩ አገሮች በሚገኙ ተራራማ ቦታዎች ተበትነው የሚኖሩ፣ ቁጥራቸው ከ35 እስከ 50 ሚሊዮን የሚደርስ፣ 90% በላይ የሚሆኑት የሱኒ ኢስላም ሲሆኑ በመካከለኛው ምስራቅ ከአረብና ፐርሺያ ቀጥሎ ብዙ ሕዝብ ያለው ብሔር ናቸው።

ኩርዶች ለምን አገር አልባ ተንከራታች ሕዝብ ሊሆኑ ቻሉ?
ይህን ጥያቄ ለመመለስ የታሪክ ገፆችን ወደኋላ ስንገልፅ ከጥንታዊው የሜሴፖታሚያ ስልጣኔ መፈራረስ ጋር የሚያያይዙት የታሪክ ፀሐፍት ቢኖሩም የሕዝቡ ከተራሮች ጋር ተቆራኝቶ ከዘመናዊ የመንግስት አወቃቀር ራሱን አግልሎ መኖሩን እንደ ዋና ምክንያት የሚያነሱ ፀሐፍት አሉ።


♦ከሁሉም በላይ የአንደኛው የአለም ጦርነትን ማብቃትና የኦቶማን ቱርክን ሽንፈት ተከትሎ ቅኝ ገዢዎች የወሰዱት ኢርቱዕ የድንበሮች አከላለል ዋና ምክንያት እንደሆነ የኩርድን ሕዝብ ያጠኑ የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ።
♦ ቢቢሲ የዜና ምንጭ በOctober 15, 2019 ባወጣው ሰፊ ዘገባ ላይ እንደተጠቀሰው በ1920 ዓ.ም ‘የኩርድ መንግስት’ የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸው እውቅና አግኝተው ለመሰባሰብ ሙከራ ቢያደርጉም በመንግስትነት መዝለቅ የቻሉት ለሶስት አመታት ብቻ ነበር ።
♦ ከዛ ጊዜ ጀምሮ በተለያየ ቦታ የተበጣጠሰ የነፃነት ትግል ቢያደርጉም እስከ1946ዓ.ም ተጨባጭ ነገር ማድረግ አልቻሉም ነበር። በአርሜንያና በኢራን የሚሮሩ ኩርዶች በአብዛኛው ማንነታቸውን የማጣት አደጋ ተጋርጦባቸው ወደ ቱርክና ኢራቅ ተሰደው እንዲኖሩ ከመገደዳቸውም በላይ በሁሉም አገሮች እንደ አናሳ ብሔር ከመታየት አልፎ ብዙ ግፍ ይፈፀምባቸው ነበር።
በቱርክ ሙሉ በሙሉ ከፖለቲካ ተሳትፎ እንዲገለሉ ከመደረጋቸውም በላይ ከሁሉም የቱርክ አካባቢዎች በለምነቱ የሚታወቀው ምስራቃዊ ቱርክ እጅግ ኋላቀርና የተረሳ ቦታ እስኪሆን ተሰርቷል።
በሶሪያና ኢራቅም ከቱርክ የተለየ አልነበረም። በሶሪያ ከ300ሺህ የሚበልጡ ኩርዳውያን የሶሪያ ዜግነት እንዳይሰጣቸው ከመከልከላቸውም በላይ መሬታቸው እየተቀማ ለአረቦች እንዲታደል ተደርጓል። ኢራቅ ውስጥም የባዝ ፓርቲ በነዳጅ ሀብቱ የሚታወቀውን ሰሜን ኢራቅ ከኩርዶች ላይ በመንጠቅ ለአረብና ምዕራባውያን እንደሰጣቸው ይታወቃል።

የኩርድ ሕዝብ በየአገራቱ የሚደርስበትን ስቃይና እንግልት ለመከላከል ሰላማዊ ትግል የጀመረው ሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቃትን ተከትሎ ከሰራዊት በተሰናበቱ የአርመን ኩርዶች አስተባባሪነት ኢራቅ ውስጥ KDP የተባለውን ፓርቲ በማቋቋም ነበር።
ኬዲፒ በሁሉም አገራትና በመላው አለም የተበተኑ ኩርዶችን በማስተባበር ባደረገው ትግል በአምስቱም አገራት እስከ ራስ ገዝ የሚደርስ የፖለቲካ ተሳትፎ ማግኘት ቢችሉም የጠበቁትን ያህል ተሳትፎ ባለማግኘታቸው በ1961ዓ.ም የትጥቅ ትግል ማድረግ ጀመሩ።
ኬዲፒ በሰሜን ኢራቅና ሶሪያ የጀመረውን የትጥቅ ትግል መነሻ በማድረግ የኩርድ ሰራተኞች ፓርቲ PKK በታዋቂው የነፃነት ታጋይ አብዱላህ ኦቻላንና ጓደኞቹ በ1978ዓ.ም ተመሰረተ። በፒኬኬ መቋቋም ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ስጋት የገባው የማዕከላዊው የቱርክ መንግስት ድርጅቱን እስከማፍረስና አባላቱን በአለም አቀፍ አሸባሪነት እንዲመዘገቡ አድርጎ መሪውን አብዱላህ ኦቻላንን በሲአይ ኤ ድጋፍ በኬንያ ናይሮቢ ተይዞ መጀመሪያ የሞት ቀጥሎ የእድሜ ልክ እስረኛ ሆኖ ይገኛል።

ውድ አማሮች ይህ ከላይ ከተለያዩ አውታረ መረቦች ለቃቀሜ ከፃፍኩት የኩርዶች ታሪክ ምን እንማር?
♦ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያን እየዘመርን የአማራ ርስቶችን ለጠላቶቻችን አስረክበን አገር አልባ ሕዝብ እንሁን? ወይስ አንድነታችንን አጠንክረን ሕዝባችንን ከተንከራታችነት እናድነው?
ምርጫው የራሳችን ነው፣ ወይ ነፃነትን ግብ አድርገን እንነሳ፣ ወይንም ዳግማዊ ኩረድ ሆነን በባርነት ቀንበር እንገዛ!

?? አማራ ከኩርድ ሕዝብ ስህተት ተማር!

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator