0 0
Read Time:2 Minute, 19 Second

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሀምሌ 9 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

ከአውሮፓ ህብረት እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ለልማት ተብሎ የሚሰጠው ድጋፍ ለመሳሪያ መግዣ እና አማራን እንደ አውሬ አድኖ ለመግደል፣ለማሳረድ እና ለማጥፋት እንደሚውል ሀምሌ 8/2014 ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ተሰበባስበው ጄኖሳይድን ለመቃወም ወደ ቤልጅዬም ብራስልስ ያቀኑ አማራዎችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ተናግረዋል።

ከአውሮፓ የተለያዩ ሀገራት ከጀርመን፣ከቤልጅዬም፣ከኔዘርላንድ፣
ከፈረንሳይ፣ከሲዊዲን፣ከኖርዌይ እና ከሌሎችም ጭምር የመጡ አማራዎች እና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በጋራ በመሰባሰብ በኢትዮጵያ የዘር ፍጅት ለሚፈጸምበት ለአማራ ህዝብ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

በአማራ ላይ ታቅዶ የሚፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ ይቁም በሚል በቤልጅዬም ብራስልስ በመገኘት ለአውሮፓ ህብረት አባላት ከፍ አድርገው ድምጻቸውን አሰምተዋል።

አማራ በመሆኑ ምልክት ተደርጎበት፣ቀድሞ ቅስቀሳ ተደርጎ ሲያበቃ፣ አጥፊው ልዩ ኃይል ተደራጅቶ፣ የሚያጠፋውን ሲያጠፋ የሚከላከል የህግ አካል በዙሪያ እንዳይኖር ተደርጎ
የሚፈጸም የተደራጀ እና የታቀደ የዘር ፍጅት ስለመሆኑ ሰልፈኞች አንስተዋል።

የመከላከያ ሰራዊትም እንዳይገባና በቅርብ ርቀት ሆኖ ውጤቱን እንዲሰማ እና ወንጀል ፈጻሚዎች እንዲሸሹ ከመንግስታዊ መዋቅሮች መመሪያ ተሰጧቸው ቦታውን ከለቀቁ በኋላ አስከሬን በአስከሬን በሆነበት ቦታ እየመጡ ምንም ንጹሃንን ለመታደግ አለመቻላቸውን ያወገዙት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ድርጊቱንም መንግስታዊ ቅንብር እና ሴራ ስለመሆኑ አመላክተዋል።

የዳቦ ስም እየተሰጣቸው የተዘጋጁ ክሱት እና ህቡዑ ኃይሎች መኖራቸውን በመግለጽ አማራው በአማራነቱ ከተገደለ እና ከተቀበረ በኋላ ግን አማራ አትበሉ ተብሎ ተጨፍጫፊውን ላለማሳወቅ እና በዓለም አቀፍ ህግ ላለመጠየቅ ዜጋ ነው እያሉ እንደሚናገሩም ገልጸዋል።

ሲኖር አማራ ተብሎ ተገድሎ ሲሞት ዜጋ ተብሎ የሚፈጸምበት ወንጀል እንዲድበሰበስ እና ግፉን የፈጸሙት ደግሞ ለህግ እንዳይቀርቡ የሚደረግ መንግስታዊ ሴራ እና ሽረባን ይፋ በማድረግ አውግዘዋል።

የዘር ፍጅቱን በተመለከተ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተባበሩት መንግስታት ጣልቃ ገብቶ በገለልተኛ አካል በግድ የመንግስት ማንቁርት ተይዞ የማጣራትና የምርመራ ስራ እንዲካሄድም ተጠይቋል።

በአጠቃላይ የምርመራ ውጤቱም ይፋ እንዲደረግ፣ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡና ወንጀሉም በዓለም አደባባይ እንዲታወቅ ጥሪ አድርገዋል።

መንግስት ለተፈናቀሉ ወገኖች መልሶ የማቋቋም ግዴታ በአስተማማኝ የደህንነት ዋስትና ዙሪያ እንዲሆን የተለያዩ ጥያቄዎችም ተነስተዋል።

ለዚህ ሁሉ ፋሺስታዊ አገዛዝ የ21ኛው መቶ ክ/ዘመን ፋሺስት አብይ አህመድ እና አገዛዙ መሆኑን፣ የዘረኞች ቁንጮ፣ በአሁኑ በ21ኛው ክ/ዘመን ሂትለር እሱ መሆኑን፣ ሞሰሎኒ እሱ መሆኑን፣ በዘረኝነት የኢትዮጵያ ጠላት መሆኑንም በሰልፈኞች ተንጸባርቋል።

አብይ አህመድ አሁኑኑ ስልጣን መልቀቅ እንዳለበትና በቦታው ፍትሃዊ የሽግግር ስርዓት እንዲመሰረት የሚሉ ጥያቄዎችንም በስፋት አንስተዋል።

በቀድሞው የስለላው መረብ ኃላፊ ሆኖ ብዙዎችን ያስገደለ እና የጌቶቹን አልጋ ሲቋምጥ እንደነበረና ተመሳሳይ አላማን እያስፈጸመ ስለመሆኑ ተገልጧል።

ሰልፈኞችም የራሳቸውን ጭሆትና ተንበርክከው ኡኡ ብለው እሪታቸውን በማሰማት ወንጀለኞች ለዓለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍ/ቤት እንዲቀርቡ በአፅንኦት አሳስበዋል።

የግፉን ይዘት የሚጠቁሙ ደብዳቤዎችም በአግባብ ወደሚመለከተው የአውሮፓ ህብረት ክፍል እንዲቀርቡ እና አስቸኳይ የሆነ እርምጃ እንዲወስዱ ተማጽነዋል።

ከአውሮፓ ህብረት እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ለልማት ድጋፍ ተብሎ በገንዘብ የሚሰጠው እገዛ ለመሳሪያ መግዣ እና አማራን እንደ አውሬ አድኖ ለመግደል፣ለማሳረድ እና ለማጥፋት እንደሚውል አስገንዝበዋል።

በመሆኑም የልማት ድጋፍ በአሁኑ ሰዓት ከአስቸኳይ እርዳታ ውጭ ለዚህ ለዘረኛው አስገዳይና የኦሮሙማ አፍራሽና ዘረኛ ጽንፍ ሀሳብ አራማጅ ሊሰጥ እንደማይገባው ገልጸዋል።

ይህንን ኦሮሙማዊ አይዶሎጅ የሚያራምደው የአብይ አህመድ አገዛዝ በህግ ፊት ለዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍ/ቤት ዘሄግ መቅረብ የሚገባው እንጅ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በስልጣን መቀመጥ የለበትም የሚል አቋማቸውንም በተቃውሞ ሰልፉ አንጸባርቀዋል።

በሰልፉ እኒህ እና መሰል በርካታ ጥያቄዎች በሚገባ ተንጸባርቀዋል ሲል
የሰልፉ ውሏቸው ምን እንደሚመስል
ከአስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆነው አፈወርቅ አግደው ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) አጋርቷል።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator