የትግሬ ወራሪ ወልቃይት ጠገዴን እንደወረረ በርካቶችን ጨፍጭፏል። በጭፍጨፋው ከአንድ ቤተሰብ በርካቶች አልቀዋል። ከ34 አመት በፊት በእነ ልጃለም ታዬ ቤተሰብ የተፈፀመው ለዚህ ማሳያ ነው።
አባት ልጃለም ታየ እንዲሁም ሶስት ልጆቻቸው አዲሰይ ልጃለም፣ አለምሸት ልጃለም እና ተክሌ ልጃለም በገሃነም እስር ቤት ተሰቃይተው ተረሽነዋል። ከ34 አመታት በኋላ በቅርቡ አፅማቸው ወጥቶ በወልቃይት-ጠገዴ ደጀና ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን አፅማቸው አርፏል።
የተፈፀመው የዘር ፍጅት ከቤተሰብ አባላትም በርካቶችን የጨረሰ ነው። አራት የቤተሰብ አባላቱ ታፍነው ታስረው፣ ተረሽነው ለአመታት አፅማቸውን እንኳን አንስቶ መቅበር እንዳይችል የተደረገ ቤተሰብ በምን አይነት ሁኔታ እንደኖረ ግልፅ ነው። ይህ ቤተሰብ ለአጠቃላይ በወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አማራ ሕዝብ ላይ ለደረሰው ትልቅ ማሳያ ነው። የዘር ፍጅቱ እያንዳንዱ ቤተሰብን ያዳረሰ ነው።