0 0
Read Time:6 Minute, 37 Second

የአማራq ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ- የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ (ጋሻ አማራ ) በወቅታዊ የሀገራችን ጉዳይ ላይ ያወጣው መግለጫ!

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ (ጋሻ አማራ) ሀገራችን እና ሕዝባችን ዛሬ በብልጽግና መራሹ መንግስት እየደረሰባቸው ባለው መጠነ ሰፊ የጥቃት ዘመቻ፣ የሰብዓዊ መብት ገፈፋና ረገጣን ሁኔታ በጥልቀትና በቅርበት የምንከታተል መሆናችንን በቅድሚያ ለመግለጽ እንወዳለን።

በዚህ መሰረት ሀገራችን እና ሕዝባችን ዛሬ ከፍተኛ በሆነ የኑሮ ውድነት ክፉኛ ተሰቅዞ በመያዝ ኑሮው እጅግ አስቸጋሪ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ የኦህዴድ-ብአዴን መራሹ የብልጽግና ቡድን:_

በሰፊው የአማራ ሕዝብ፣ የጉራጌ ሕዝብና በአዲስ አበባ ነዋሪ ላይ እያደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ ጥቃት፣ እመቃንና ከፍተኛ የሆነን የሰብዓዊ መብት ገፈፋን ድርጅታችን በጽኑ ለማውገዝና ብሎም ይህንን ሰርዓታዊ ማን አለብኝነትን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አምርሮ እና እምቢ ብሎ እንዲታገለው እና ሊካሄድ በታቀደው የብልጽግና እና የትህነግ ድርድር ላይ እና የአማራ ጋሻ መከታ በሆነው የአማራ ፋኖ ጉዳይ ይህንን ወቅታዊ መግለጫ ለሕዝባችን ልናወጣ ችለናል።

1ኛ-ታላቁን የአማራ ሕዝብ ከአዲስ አበባ የመነጠልን ሴራዊ እርምጃን በተመለከተ፦

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል-ፋኖ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ (ጋሻ አማራ ) አህዴድ-ብአዴን መራሹ የብልጽግና ቡድን ታላቁን የአማራ ሕዝብ ወደ አያት ቅድመ አያቶች ቆርቁረው ከገነቡት አዲስ አበባ ከተማ እንዳይገባ እያደረገ ያለውን የእገዳን ተግባር የለየለት ፋሺስታዊና አፓርታይዳዊ ተግባር ነው በማለት ድርጊቱን በጽኑ ያወግዛል።

ለመላው የአማራ ሕዝብ የምናስተላልፈው መልእክትም ለፍተህ፣ ጥረህ፣ ግረህ በገነባሃት ሀገር ደምህን አፍሥሰህ፣ አጥንትህን ከስክሰህና ምትክ የለሽ ውድ ህይወትህን ገብረህ ህልውናዋን ጠብቀህ እዚህ ባደረስካት ሀገር ውስጥ በነጻነት ተንቀሳቅሰህ የመኖር የማይሻርና የማይገሰስ ተፈጥሮዊ መብት ያለህ ሕዝብ በመሆንህ ለአፓርታይዳዊው እገዳ ሳትንበረከክ በአዲስ አበባ የመግባት የመውጣትና የመኖር መብትህን እንድታስከብር ልንልህ እንወዳለን።

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል-ፋኖ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ (ጋሻ አማራ) የኦህዴድ-ብአዴን መራሹን የብልጽግናን ቡድን አማራዊያንን ከአዲስ አበባ የማገድን እርምጃ ፋሺስታዊነትና አፓርታይዳዊ ዘረኝነት ነው በማለት ድርጊቱን በጽኑ ያወግዛል።

እርምጃውንም ታላቂቷን ኦሮሚያ እንመሰርታለን ቅዥት አካል መሆኑን ለሕዝባችን እየገለጸ መላው የሀገራችን ሕዝብ በእምቢተኝነት ተጋድሎ ሴራውን እንዲያከሽፈው ብርቱ ጥሪ እናቀርባለን።

2ኛ_ የጉራጌን ሕዝብ የክልልነት ጥያቄን በተመለከተ፦

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል – ፋኖ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ (ጋሻ አማራ) ከጉራጌ ሕዝብ በኩል እየተስተጋባ ያለውን የክልልነት ጥያቄ በፍትሃዊነቱ የሚያምን መሆኑን እየገለጸ ለወገናችን የጉራጌ ሕዝብ ያለውን ጽኑ ድጋፍ ያረጋግጣል።

የጉራጌ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ ፍትሃዊ የሆነ ብቻ ሳይሆን ይህ ጎሳ ተኮር የፌዴራል አወቃቀር ሲመሰረት ጉራጌ በክልልነት ሊከለል የሚገባው የዘገየ መብት ነው ብለን እናምናለን።

ምንም እንኳን የአፓርታይድ ክልል የኢትዮጵያ አስተዳደራዊ መዋቅር ሙሉ በሙሉ የምንቃወመው ቢሆንም፤ የጉራጌ ሕዝብ በታሪኩ፣ በአሰፋፈሩ፣በምጣኔ ሀብት አቅሙ፣ በሕዝብ ብዛቱና በፋነቱ መሰረት እራሱን በራሱ ለማስተዳደር የሚያበቃ ክልል የሚገባው ሕዝብ ነው ብለን ስለምናምን ሁለንተናዊ ድጋፋችንን እንገልጻለን።

3ኛ_ በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት በብልጽግና መራሹ መንግስትና በትግራዩ ትህነግ መካከል ሊካሄድ ስለታቀደው ድርድር በተመለከተ፦

ሕዝባችንም ሆነ ሀገራችን ዛሬ በሰሜኑ የሀገራችን ግዛት ውስጥ በአማራ፣ በትግራይና በአፋር ግዛቶች ውስጥ የተከሰተውን እጅግ ሰው ጨራሽና ንብረትና ተቋማትን አውዳሚ ጦርነት አስተናግዶ ያለአንዳች መቋጫ ሰላምም ጦርነትም (No Peace, No War) በሌለበት ሁኔታ ላይ ያለ መሆኑን ድርጅታችን በቅርበትና በጥልቀት በመከታተል ያውቃል።

ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ በሚል ሽፋናዊ ሰበብ የብልጽግና መራሹ መንግስት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ – በተለይም ከአሜሪካና ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ባደረገው ምስጢራዊ ውይይትና ስምምነት መሰረት የሰሜኑን ጦርነት በሰላማዊ መንገድ እፈታለሁ ብሎ በመወሰን ከትግራዩ ትህነግ ጋር በአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪነት ለመደራደር ወስኖ ለዚህ ግብዓት የሚያገለግሉ እርምጃዎች ከሁለቱም ወገን እየተወሰደ እንዳለ ይታወቃል።

ሁለቱም ወገኖች በድርድሩ ላይ የሚገኙትን ተደራዳሪ ተወካዮቻቸውን ሰይመው ካሳወቁ በኋላ ድርድሩን የሚመራው የአፍሪካ ሕብረት ብቻ መሆኑ ቀርቶ አሜሪካ፣ ተመድ እና የአውሮፓ ሕብረትም በአደራዳሪነት እንዲካተቱ መወሰኑን በአፍሪካ ሕብረት በኩል የተገለጸ ነው።

በኢትዮጵያ በኩል ብልጽግና መራሹ መንግስት ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ መንግስት ለመደራደር ዝግጁ ነው ብሎ ሲገልጽ በትግራዩ ትህነግ በኩል ግን በድርድሩ ላይ ለመሳተፍ ከአሁን ቀደም ቡድኑ በኃይል ከአማራ በመንጠቅ «ምእራብ ትግራይ» ብሎ የሰየመውን ግዛት – ማለትም ወልቃይት ጠገዴ ሁመራና ጸለምት ወደ ትግራይ አስተዳደር ሲመለስለት ብቻ ይሆናል በማለት የቅድመ መደራደሪያ ጥያቄን ማቅረቡንም ለማወቅ ችለናል።

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል / ፋኖ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ (ጋሻ አማራ) እንደ አንድ በአማራ የህልውና ትግል ላይ ተሰልፎ ለሰፊው የአማራ ሕዝብ አንዳችም መቀናነስም ሆነ መሸራረፍ የማይነካው እማይሻርና እማይገሰስ የማንነት ተፈጥሮአዊ መብትና ጥቅም መከበር የሚታገል ድርጅትነቱ የፖለቲካ ቅራኔዎችን፣ ግጭቶችን እና ብሎም የፖለቲካ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ በንግግር፣ በድርድርና በውይይት መፍታት መቻሉን ከመርህ አንጻር የምንቀበለውና የምናበረታታው ችግር መፍቻ መንገድ ነው እንጂ በደፈናው የምናወግዘው አለመሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

ይህንን መርሃዊ አቋማችንን እና ጉዳዮችን መመልከቻዊ እይታችንን መሰረት በማድረግ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተለኮሰውን አውዳሚን የእርስ በርስ ጦርነት በድርድር መፍታት የሚለውን ፖለቲካዊ ውሳኔን በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ የማንቃወመው መሆናችንን እንገልጻለን።

ዝርዝር አፈጻጸሙ ላይ ግን ድርድሩ ሕዝባችንና ሀገራችን ለተጋፈጡበት ዘርፈብዙ አደጋ መፍትሄን የሚያፈልቅና መፍትሔን የሚያቀርብ እውነተኛ ድርድር መሆን አለበት እንጂ በመላው የአማራ ህዝብ እና ብሎም በአፋር ሕዝብ ዋጋ ከፋይነት ጥቂት ብልጣብልጦች ስልጣን ማደላደያነት መፈጸም የለበትም ብለን በጽኑ እናምናለን-ለዚህ አይነቱ አፈጻጸምም እንታገላለለን።

በሰሜን ኢትዮጵያ የተለኮሰውን የእርስ በርስ ጦርነት የጦርነቱ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሽ የሆነው የአማራ፣ የአፋርና የትግራይ ሕዝብ በተወካዮቹ በኩል የሚሳተፍበት የሰላም ድርድር ለተፈጠረው ችግር መሰረታዊ የሆነ ማለፊያ የሆነ መፍትሔን ማፍለቅ፣ መቅረጽና ብሎም ማሳለፍ የሚቻለው ይሆናል እንጂ አሁን እየተነገረን ባለው ሁኔታ የአማራን እና የአፋርን ሕዝብ የማይወክሉ ጥቂት የብልጽግና እና የትህነግ ተደራዳሪ ተወካዮች በሚያደርጉት ድርድር ሰላምም ሆነ መፍትሔ ይመጣል የሚል እምነት የለንም።

በዚህ በብልጽግና እና በትህነግ መካከል በሚደረገው ድርድር ከመደራደሪያ አጀንዳዎቻቸው ውስጥ አንዱና ዋነኛው የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሁመራና የራያ አማራዊያን ማንነትና እጣፈንታ ላይ እንደመሆኑ መጠን – በሁለተኛ ደረጃ አማራ እና አፋር በጦርነቱ ሰላሳ መታት ወደ ኋላ የመለሰ ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ፣ ቁሳዊና ሞራላዊ ውድመት የደረሰባቸው ሕዝብ እንደመሆናቸው እና ከትግራይ ጋር በጂኦግራፊ የሚዋሰኑ ከትግራይ ሕዝብም ጋር በእምነት በባሕልና በነገዳዊ ማንነትን የሚጋሩ በመሆናቸው በዚህ አይነቱ ድርድር ላይ መሳተፍና ድርድሩንም በዋና ባለቤትነት መምራት የሚገባቸው እነዚህ የጦርነቱ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሾች እንጂ በጦርነቱ ወቅት ሊፈረጥጥ ሻንጣውን የሸከፈና አዲስ አበባ ላይ ቁጭ ብሎ በለው ሲል የነበረ ካድሬ ነው ብለን በፍጹም አናምንም።

በዚህ መሰረት ድርድሩ የተሳካና ውጤታማ ይሆን ዘንድ መንግስት በአስቸኳይ፦

1ኛ- ከወልቃይት ጠገዴ ሁመራና ራያ አማራዊያን የተወከለን ተወካይ፣

2ኛ- ከመላው የአማራ ፋኖ የተወከለ ተወካይ፣

3ኛ- ከአዴፓ ውጪ ከሰፊው የአማራ ሕዝብ የሚወከል የሕግ፣ የታሪክና የኢኮኖሚ ባለሙያ ተወካዮች፣

4ኛ- የአማራ ክልላዊ መስተዳደር ምክር ቤት በአማራው የታመኑ ተወካዮችን በድርድሩ ውስጥ እንዲያካትት አጥብቀን እንጠይቃለን።

ድርድሩን በተመለከተ የመደምደሚያ አቋማችን፦

የአማራ ሕዝባዊ ኃይል-ፋኖ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ (ጋሻ አማራ) ወልቃይት ጠገዴ ሁመራና ራያ በትህነግ በኃይልና በጉልበት የተወሰዱ መሬቶቹ የአማራ ርስት ነዋሪዎቹም አማራዊያን የመሆናቸው ጉዳይ ላይ ለድርድርም ሆነ ለጥያቄ የማይቀርብ እውነታ ነው ብሎ በጽኑ ያምናል – ለተፈጻሚነቱም በጽናት ይታገላል።

በእነዚህ አጽመ ርስቶቻችን ላይ ሕገመንግስታዊ መፍትሔ ይሰጣል የሚለውን የማንኛውንም ወገን ፍላጎትና ጥያቄን በጽኑ ያወግዛል።

የወልቃይት ጠገዴ ሁመራና ራያ ወደ ትግራይ አከላለል ከዛሬው ሕገ መንግስት መፈጠር በፊት እንደሆነ ሁሉ አፈታቱም ከሕገ መንግስቱ ውጪ በሆነ መንገድ ነው የሚለውን የመላውን አማራ ሕዝብ አቌም ተፈጻሚ ለማድረግ ድርጅታችን የማያወላውል ጽኑ አቌም ሲሆን ለሁለንተናዊ ተፈጻሚነቱም በጽናት ይታገላል።

ዐማራው በትክክል ያልተወከለበት ህገመንግስት የህግ መሰረት ሆኖ የዐማራውን የማንነት ጥያቄ የሚመልስ ስላልሆነ፣ አማራው በመስዋእትነት ያገኘውን ማንነቱንና መሰረታዊ መብቱን በሕግና በድርድር ስም ለመጨፍለቅ መሞከር ትርፉ ጥፋት መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባል።

4ኛ- የመላው አማራ ሕዝብ ህልውና ወገናዊ ጋሻና መከታ ስለሆነው የአማራ ፋኖአዊ ሁኔታን የተመለከተ ይሆናል።

ጋሻ አማራ – የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ድርጅት ስለሆነ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በሰፊው የአማራ ህልውናን ጠብቆና አስጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ እይታ አኴያ አማራዊ ፋኖነት እና ፋኖዓዊ አደረጃጀት አስፈላጊነት ላይ ለጥያቄም ሆነ ለድርድር እማይቀርብ ወሳኝ ነው ብሎ በጽኑ ያምናል።

የአማራ ሕዝብ ስነ ባህላዊ እሴት የሆነውን አማራዊ ፋኖነትና ፋኖዓዊ አደረጃጀትን ድርጅታችን በአማራ የህልውና ትግል ውስጥ ወሳኙን ስፍራ የያዘ ኃይል ነው በሚል ጽኑ አቋማዊ መርህና እምነት በመመራት ሕዝባችንን ያስተባብራል ብሎም አቅጣጫም ያመላክታል።

አማራዊ ፋኖነት አደረጃጀትን በማንም ፍቃጅነትም ይሁን ከላይካይነት የምንፈጽመውና የምናቆመው ትግላዊ አደረጃጀት ሳይሆን በራሳችን ሕዝብ ማንነታዊ ህልውና ደህንነት ተጠብቆና ተረጋግጦለት መኖር መቻሉ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ስነ ማሕበራዊ ጥያቄዎቹ ሙሉ በሙሉ ተጠብቆለትና ተከብሮለት በነጻነት መኖር የመቻሉና ያለመቻሉ ሁኔታ ነው በነፍጥ የተደራጀን ፋኖዓዊ አደረጃጀት የማስፈለጉንና ያለማስፈለጉን የሚወሰነው ብለን ነው የምናምነው።

ዛሬ ጀግኖቻችን አርበኛና ፋኖ ዘመነ ካሴ መ/አ ማስረሻ ሰጤና አጠቃላይ አቻዎቻቸው ፋኖዎቻችን የአማራ ነጻነት ሳይከበር ነፍጣችንን አንሰጥም ብለው በዱር በገደሉና በጫካ ሸንተረሩ ስለአማራ ሕዝብ ነጻነትና ማንነታዊ ህልውና እየታገሉ ናቸው።

ጀግኖቻችን በጫካ ባሉበት ሁኔታ እና በሌላ በኩል ደግሞ እኛ በዚህ መግለጫችን ክፍል አንድ ላይ በገለጽነው መልኩ የአማራ ተወካይ ባልተሳተፈበት የአቢይ መራሹ ብልጽግና እና የትግራዩ ትህነግ መካከል በሚደረግ ድርድር የአማራን መብት፣ ጥቅምና ነገዳዊ ማንነቱን የሚያስጠብቅ ስምምነትና ውጤት ይወጣዋል ብለን የምንጠብቅ አለመሆናችንን ይታወቃል።

አማራ ባልተሳተፈበት ድርድር የሚጠቅመውን ማግኘት እንደማይችል ሁሉ በእጁ ያለውን የአማራን ፋኖ ግን እንዲጠቅመው አድርጎ በሁለገብ ድጋፍ ማጠናከርና ኃያል አድርጎ ማውጣት ግን ይቻለዋል ብለን እናምናለን።

እንደ አማራነታችን ከፈጣሪ በታች ለነገዳዊ ማንነታችንም ሆነ ለእርስታችን ለሀገራችን ብቸኛው የህልውናችን መሰረት አማራዊ ክንዳችን እና አማራዊ አንድነታችን ብቻ መሆኑን እናውቃለን።

አማራዊ ክንዳችን ማለት የአማራ ፋኖ – ፋኖዓዊ አደረጃጀታችን ማለታችን ነው።

ይህንን አደረጃጀታችንን በሰው ኃይል በጉልበት በእውቀት በሎጀስቲክስ በመረጃና በሁሉም መስክ በመደገፍ ዙሪያ ገባውን ከተደቀነብን የጥፋት ድግስ ሊያስወጣን በሚያስችል ድርጅታዊ ቁመና እና አቅም አደርጅተንና አጠናከረን ማውጣት ይጠበቅብናል ብለን እናምናለን።

ይህንንም እውን ለማድረግ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪው ዓለም ላለው ለአማራ ተወላጅ ለሆነ ሁሉ የምናስተላልፈው ጥሪ ኑ እና በጋራ የነገደ አማራን ህልውናን ማስጠበቂያን ፋኖን ተቀላቅለን በድጋፍ እናጠናክር የሚል ነው።

በተባበረ አማራዊ ክንድ ነገዳዊ ህልውናችንን እና ተፈጥሮአዊ መብታችንን እናስጠብቃለን!!!!

የአማራ ህልውና በልጁ በፋኖ ይከበራል!

ኢትዮጵያን ለጎጠኞች እንዳትመኝ እናደርጋታለን!

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator