በአብይ አህመድ የሚመራው የፋሽስት ኦነጋዊያን አገዛዝ አዲስ አበባን የማወረም ፕሮጀክቱን ቀጥሏል።የዋጭ ሰልቃጭነት ባህርይ የተጠናወታቸው ሁሉን የኔ ባይ ኦነጋዊያን አዲስ አበባን ብሎም መላው ኢትዮጵያን ለማወረም እንቅስቃሴ የጀመሩት ቤተ መንግስት በገቡ ማግስት ጀምሮ ነበር።

ከቡራዩ፣ከጉጂ፣ከጣፎ፣ከሱልልታ፣ከሰንዳፋ፣ከሰበታ እና በሌሎችም አካባቢዎች የተደረጉ ማፈናቀሎችና ማሳደዶች እንዲሁ የተደረጉ ሳይሆን ኦሮምያ የሚሏትን የህልም ሀገር ለመምስረት ለሚያደርጉት ጥረት መሳኪያ እንዲሆናቸው ነው። ይሄ ብቻ ሳይሆን በምንጃር በአጣዬ በመተከል እንዲሁም በproxy war የተለያዩ አካባቢዎች ላይ ሲያደርጉት የከረሙት የሽብር ተግባር ለኦሮምያ የህልም ሀገር መሳካት ታስቦበት የተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

የአዲስ አበባ ጉዳይ ግን ከቀን ወደ ቀን በጣም እየተባባሰ የመጣ ነው። በወንዞች ፕሮጀክት፡በአዲስ አበባ ልማት ፡በቤተ መንግስት እድሳትና በሌሎችም የተቀደሱ በሚመስሉ እቅዶች አዲስ አበባ ውስጥ ቅርስ እና ታሪክ ከማውደም ባለፈ ሺዎችን ቤት አልባ እያደረጉ ጎዳና እያስወጧቸው ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ ቆጥቦ ያስገነባውን ኮንደሚኔም በተለያየ ምክኒያት ለኦሮሞ ማደላቸው የሚታወቅ ነው።የአዲስ አበባ መታወቂያ እንደ ስኳርና ዘይት ከየገጠሩ ወጣት እየጠሩ ሲያድሉ እንደ ከረሙ ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው እውነታ ነው።

በኮሮና ወቅት እንኳ ዜጎች በኮሮና ተጋላጭ ሆነው እንዲያልቁ ጭምር በከፍተኛ ሁኔታ እያፈናቀሉ ነው። ባለፈው አምኒስት ኢንተርናሽናል 1000 አባወራዎች ቤት አልባ ተደርገው ለኮሮና እንደተጋለጡ በሚያሳዝን መልኩ አስንብቦናል። በሮመዳን ፆም እንኳ ወቅታዊውን ወረርሽኝ ቤታቸው ሆነው ፈጣሪያቸውን እየለመኑ እንዳያሳልፉ በግፍ እያፈናቀለ ሜዳ ይበትናቸው እንደነበር አይተን አዝነናል። ለይስሙላ ደግሞ በየቴሌቭዥኑ የፀሎት ፕሮግራም እያለ ቀጥታ ስርጭት እንዲደረግ እያዘዘ በጀርባ ሄዶ ንፁሃን ወገኖችን እያፈናቀለ ጎዳና ላይ ይጥል ነበር።

የአብይ አህመድ ፋሽስታዊ ኦነጋዊ ሥርዓት የሚከተለው ጭቆናዊ ሂደት እየተጨቆንክ እንደሆነ እንዳይገባህ በማደንዘዝ ነው። ይሄንን ደግሞ በተደጋጋሚ ያየነው ነው።ራሱ ወንጀለኛ ሆኖ ሲያበቃ የሚታዘንለት ሆኖ የሚተውን በጣም አደገኛ አውሬ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።አዲስ አበባ ዳግም እየወደመች ነው።የሚጠፋው ታሪክም ቅርስም የአማራ ነው። የሚፈናቀሉት አማራዎች እና እርሱ ወገኔ የማይላቸው ሁሉ ናቸው።
የኦነጋዊያን ናዚያዊ መንገድ ቀድሞ የገባው ታላቁ እስክንድር ነጋ የአዲስ አበባ ህዝብን መብት ለማስከበር ከሲቪክ ማህበር እስከ ፖለቲካ ፓርቲ ምስረታ ድረስ ብዙ እየደከመ ነው።የህዝብ ልጅ እስክንድር ነጋ በዛሬው ዕለት በፋሽስቶች ለተፈናቀሉት እርዳታ ለመስጠት መሞከሩ እንኳ በጠላትነት ታይቶ ተከልክሏል።
መላው አማራ አዲስ አበባን ከዳግም ውድመት የሚያድንበት የሚጠብቅበት ጊዜ አሁን ነው።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator