ፋኖ ምስጋን ደስዬ ከወሎ
ፋኖ ምስጋን ደስዬ በወሎ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር በተያያዘ የሰማውን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል:_
ያሣዝናል ዛሬ አንድ ወሬ ሽው አለኝ ! የመከላከያ ሠራዊት በዛሬው ስብሰባ ፋኖ የማረከውን ጥቁር መሣሪያ ይቀማ የሚል ውሳኔ አሳልፏል አሉኝ።
ይህ ጥቁር መሣሪያ ከማን ተማረከ ?
ከጠላት የማረክነውን መሣሪያ መከላከያ ልቀማ ማለቱ ኢ – ሞራላዊ ውሳኔ ሆነብኝ መሣሪያው በሶስት ነገር ሊወሰድ ይችላል:_
1/ ማርከነው፣
2/ ቀምተነው፣
3/ ጥሎት ከሸሸ ላይ አግኝተነው!
ይህ መሣሪያ በፋኖ እጅ ላይ እንጂ ኦነግ እጅ ላይ አልነበረም !!!
ግን ስለምን በምን የሞራል ልዕልና የተማረከ መሣሪያ አምጡ የሚል ነውር እንወስን አሉ።
ለእኔ በርካታ ነገር ያሣየኛል:_
1/ አማራን አንገት ለማሥደፋት
2/ የተረኛው ስጋት ፋኖን መበተን
3/ የድል ሺሚያ በመከላከያችን
ሌሎችም የሚጠረጠሩ ምክንያቶች ነበሩ ። ነገር ግን አንዱን ማንሳት ቢያሻኝ አንድ ጀኔራል እንዳሉን በጠሚሩ የፋኖን መሣሪያ እንድንቀማ ታዘናል ብለው የነገሩንን ሳስበው ውሳኔው ላይደንቅ ይችላል !!!
ታስቦ ታቅዶ እየተሠራ ያለውን አማራን የማሣደድ ስንኩል ሴራ የክልላችን ሰወች ምን ይሉ ይሆን ? እስከመቼ፣ በህዝባቸው፣ በርስታቸው፣ በክብራቸው፣ በስልጣናቸው ተጠቅመው ህልውናችን ይከበር የማይሉ ???
በጎንደር በጎጃም በሸዋ ያለ ፋኖ በወሎ የሆነው ነገ ላይ መምከር ይጠበቅብን ይሆን ?
ቀጣዩ ነገራችንስ ከፊት ለፊት ጂብ ከጀርባ ጂል እንዳይበላን ልካችን ምን ላይ ይሆን ?!
ከደሴ ወደ ራያ ቆቦ ለጓዶቻቸው ሬሽን ለማቀበል ሲጓዙ ነበሩ 15 የደቡብ ወሎ ፋኖዎች ኡርጌሳ ላይ በ21ኛ ክ/ጦር ተይዘው ታስረው ውለው መፈታታቸውና 14ቱ ትጥቅ የተገፈፉ መሆናቸውን በማውገዝ መግለጻቸው ይታወሳል።