የአማራ ፋኖ አማራዊ አንድነት

የአማራ ፋኖ  አማራዊ አንድነ

በአማራ ሕዝብ ላይ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ በተዘራበት መንግስት-መር ዘር ተኮር የጥላቻ ቅስቀሳና የታቀዱ ፖሊሲወች ምክንያት ህዝባችን የኢኮኖሚ ድቀት፣ የልማትና የእምነት ተቋማት ውድመት፣ ለዘመናት የገነባቸው የአገራዊ እሴቶች ርክሰትና የዘር መሣሣትና መጥፋት እየተፈፀመበት የህልውና ስጋት ላይ ይገኛል።

ይህንን ወንጀል ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመቀልበስ እንዲሁም በደምና በአጥንቱ ያቆማትን ሀገር በቁመናው ልክ ለመረከብ እንዲችል ፋኖ ተጠራርቶ ዱር ቤቴ ብሏል። ፋኖነት ከጥንት አባቶቻችን የወረስነው የአማራዊ መገለጫ እሴታችን ነው።

አማራ የገጠመውን የህልውና አደጋ ለመሻገርና ፋኖ የጀመረውን ትግል ከግብ ለማድረስ እንዲችል አራቱም የአማራ ፋኖ መሪዎቻችን አማራዊ አንድነታችንን የሚያበስረውን አደረጃጀት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በግንቦት አንድ 2017 መመስረታቸውን ይፋ አድርገውልናል። በዚህም ከተመሠረተ ፭ኛ አመቱን በቅርቡ የሚያከብረው የአማራ ማህበር በዩኬ የተሰማውን ደስታና ድጋፍ ልንገልጥላችሁ እንወዳለን።

ይህ እንዲሳካ ላደረጉት ጀግኖች የአማራ ፋኖዎችም ጥልቅ አክብሮትና ከልብ የመነጨ ምስጋና እናቀርባለን።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) በውጭ ለሚኖሩ አማሮች ያቀረበውን ጥሪ ሙሉ በሙሉ የምንቀበለውና ለተግባራዊነቱም የበኩላችንን አስተዋፅዎ እንደምናደርግ እና አማራዊ አንድነታችን ከምንም በላይ ዋስትናችን በመሆኑ በውጭ ለሚኖሩ አማሮችም ከጎናቸው እንድንቆም ጥሪ እናቀርባለን፡፡

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፣ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ

የአማራ ማህበር በዩናይትድ ኪንግደም

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Leave a Reply

Translator