0 0
Read Time:6 Minute, 51 Second

አቻምየለህ ታምሩ

የጋሞ ብርብር ማሪያሙ መነኩሴ አባ ባሕርይ፣ ወራሪው የኦሮሞ የገዢ መደብ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ከባሌ በታች ተነስቶ በየስምንት ዓመቱ በሚያካሂደው ወረራ ሀገራችንን ሲያጠፋና የሬሳ ክምር ሲያደርግ በዐይናቸው ያዩ የታሪክ ምስክርና ሀገራችን በኦሮሞ የገዢ መደብ የጠፋችበትን ምክንያት አጥንተው መጪው ትውልድ ይማርበት ዘንድ የጥናታቸውን ውጤት ቀለም በጥብጠው፣ ብራና ፍቀው ጽፈውልን ያለፉ ታላቅ ሊቅ ናቸው።

ሰሚ ያላገኘውን የአባ ባሕርይ ምክር ከማቅረቤ በፊት ስለ ኦሮሞ የገዢ መደብ የተወሰነ ነገር ልበል። ከዚህ በፊት እንዳልኩት የገዳ ሥርዓት በየስምንት ዓመቱ ወረራ የሚካሄድበት ጽልመታዊ ወታደራዊ አደረጃጀት ነው። በዚህ ወታደራዊ የገዳ ሥርዓት መሠረት የኦሮሞ ገዢ መደብ የሚኾነው በገዳ እርከን ስድስተኛው መደብ ላይ የሚገኘው ሉባ የሚባለው የወታደር መደብ ነው። ሉባ እድሜያቸው ከ41-48 የኾኑ የተመሰከረላቸው ገዳይና ወራሪ ወታደሮች ስብስብ ነው። የሉባው መሪ አባገዳ ይባላል። ከሉባ መደብ በፊት ያለው የገዳ እርከን ራባ ዶሪ ይባላል። ራባ ዶሪ ከ33-40 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ጎረምሳ ወታደሮች መደብ ነው።

የገዳ ሥርዓት ባጠቃላይ ዐሥር መደቦች ያሉት ሲኾን ደበሌ (ከ0- 8 ዓመት )፣ ጋሜ ጥጥቆ (ከ9- 16 ዓመት)፣ ጋሜ ጉርጉዶ (ከ17- 24 ዓመት)፣ ኩሳ (ከ25- 32 ዓመት)፣ ራባ ዶሪ (ከ33- 40 ዓመት)፣ ሉባ (ከ41- 48 ዓመት)፣ ዩባ (l) (ከ49- 56 ዓመት)፣ ዮባ (II) (ከ57- 64 ዓመት)፣ ዮባ (III) (ከ65- 72 ዓመት) እና ጋዳሞጂ (ከ73- 80ዓመት) ናቸው።

በበላኤ ሰብዕ ዐቢይ አሕመድ የጠቅላይ ሚኒስቴርነት ዘመን ስለ ገዳ ባካሄደው ጥናት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ኤርትራዊው ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ እ.ኤ.አ. በ1973 ዓ.ም. «Gada: Three Approaches to the Study of African Society» በሚል ባሳተመው መጽሐፍ ገጽ 8 ላይ የራባ ዶሪ መደብ ወደ ሉባ ወይም ገዢ መደብ ለመሸጋገር ሊከውናቸው ከሚገቡ ወታደራዊ ተግራባት መካከል ዋና ዋናዎቹ ሲጠቅስ «ሥልጣን ተረካቢው መደብ ሥልጣኑን ከመረከቡ በፊት ቀደምት ትውልዶች ያልወረሩትን አካባቢ በወረራ መያዝ አለበት። ይህ ለየት ያለው ጦርነት ቡታ ይባላል። ቡታ በየስምንት ዓመቱ ሳይስተጓጎል የሚደረግ ጦርነት ነው» ብሏል።

የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰንም እ.ኤ.አ. በ1990 ባሳተመው «The Oromo of Ethiopia: A History 1570-1860» በሚለው መጽሐፉ ገጽ 14 ላይ በራባ ዶሪ እርከን ያሉ የአንድ መደብ አባላት ወደ ሉባ መደብ ተሸጋግረው የመደቡ መሪ ወይም አባ ገዳ ለመኾን ከሚጠበቅባቸው መስፈርቶች መካከል ዋናው፣ ቀደምት ትውልዶች ያልወረሩትን አካባቢ ለመውረር በሚደረገው የቡታ ጦርነት የሚያሳዩት ወታደራዊ ጀግነትና በወታደራዊ መስክ ጀግንነታቸውን በተግባር ያስመሰከሩ መኾናቸውን ግዳይ ማቅረብ መኾኑን ጠቅሰዋል።

ራባ ዶሪና ሉባ መደብ ብቻ ሳይኾን የገዳ ሥርዓት ባጠቃላይ ከእድሜ ደረጃ አወጣጥ ጀምሮ እያንዳንዱ የሥርዓቱ ደንቦች የተቃኙት ወታደራዊ የበላይነትን ለማስገኘት ነው። የራባ ዶሪ እድሜውን ጨርሶ ሉባ መደብ የሚገባ ወታደር መሪ ኾኖ የሚመረጠው ሰው ከእድሜ አቻዎቹ ብዙ የገደለው ነው። በራባ ዶሪ ዘመኑ ሰውን አድኖ ገድሎ ለመረጃነት ይዞ ያልተገኘ ሉባ ሲኾን መሪ ወይም አባ ገዳ ኾኖ አይመረጥም። በገዳ ሥርዓት አንዱ የሉባ ወታደር ከጓደኞቹ መካከል በልጦ ለመገኘት በተለይ ወንዶችን፣ በእናት ማኅጸን ውስጥ ያለ ጽንስን ጨምሮ ገድሎ እንደ ሽልማት ይዞ መቅረብ የሥርዓቱ አንድ አካል ነው።

ባጭሩ የገዳ ሥርዓት በየስምንት ዓመቱ ያልወረሩትን አካባቢ እየወረሩ ያገኙትን ሁሉ የሚያጠፉ የገዳዮች ሥርዓት ነው። በአገራችን በተለይም ኦሮምያ በሚባለው ክልል ኦሮሞ ባልሆኑና ኦሮሞ አይመስሉም በተባሉ ድኆች ላይ የኦሮሞ ብሔርተኞች ባጠቃላይ፣ ኦነግና ኦሕደድ/ የኦሮሞ ብል[ጽ]ግና እየፈጽሙት ያለው የጅምላ ፍጅት፣ ውድመትና የዘር ማጥፋት የገዳው ዘመን ቅጥያ ነው። እነ ለማ መገርሳና ዐቢይ አሕመድ የክብር ዶክትሬት የሰጡት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰም ኾነ የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን እንደነገሩን ራባ ዶሪዎች ወደሚቀጥለው የገዳ እርከን ወደ ሉባ ተሻግረው አባ ገዳ ለመኾን ከሚያቀርቧቸው ማስረጃዎች መካከል የገደሉት ሰውና የሰለቡት የወንድ ብልት ብዛት፣ የወረሩት የሌሎች መሬት ስፋት፣ በሞጋሳ ገርባ ያደረጉት የጎሳ ቁጥርና የዘረፉት ሀብት መጠን ዋና ዋናዎቹ ናቸው። የዘንድሮዎቹን እያደረጉት ያለው ይህንኑ ለአራት መቶ ዓመታት ያህል የመንፈስ አባቶቻቸው ሲያደርጉት የኖሩትን ነው።

አሁን አባ ባሕርይ ምሑር ኅሊናቸው የጫረውን፣ እስካሁን ግን ሰሚ ያላገኘውን የሽምግልና ምክራቸውን ወደማቅረቡ ልሸጋገር። አባ ባሕርይ የኦሮሞ የገዢ መደብ በገዳ ወታደራዊ ሥርዓት እየተመራ ከባሌ በታች ተነስቶ ዛሬ ደቡብ በምንለው ክፍል የነበሩበት አካባቢን ሲጨፈጨፍና ነባር የኢትዮጵያ ነገዶችን ሲጠፉ ዐናቸው እያየ «ጋ*ች ጥቂት ሆነው ሳለ ከነሱ በብዛት የሚበልጠውን ሕዝብ እንዴት መጨፍጨፍና መሬቱን መቀማት ተቻላቸው?» የሚል ተጠየቅ (inquiry) በማንሳት የሽንፈቱን መሠረታዊ መንስኤና መፍትሔዎች በዚያው ችግሩ በተፈጠረበት መዋቅር ውስጥ መፈለግ ሞክረዋል። አባ ባሕርይ ላነሱት መጠይቅ የውጭ ሰበብ ወይም ማመካኛ ከመፈለግ፣ መንፈሳዊ ወይም ሃይማኖታዊ ኃይልን ተጠያቂ ከማድረግ እንዲሁም ከስሜታዊነትና ከወገንተኝነት በመነሳት ከሚነሱ ጥያቄዎች ፈጽሞ በተለየ ምሑራዊነት የዘመናቸውን መዋቅራዊ ችግሮች በትክክል ለመረዳት ሞክረዋል።

አባ ባሕርይ በ«ዜናሁ ለጋ*» ክፍል 19 ላይ የኦሮሞ የገዢ መደብ ከባሌ በታች ተነስቶ ያገኘውን ሁሉ እያጠፋ ራሱን ከመከላከል በላይ አቅም ያለውን ኢትዮጵያዊ አሸንፎ በወረራ በያዘው የራሱ ያልኾነ የሰው መሬት ላይ እንደ ዋርካ የተንሰራፋበትን መንስኤ ሲመረመሩ በዘመኑ ይሰነዘሩ የነበሩ የተለያዩ መላ ምቶችን ሁሉ ይፈትሹና ብዙዎች ኾነን በጥቂቶቹ የተወረርንበትን ትክክለኛ መንስኤ ሲያስቀምጡ ማኅበራዊ አደረጃጀታችንን ተጠያቂ ያደርጋሉ። አባ ባሕርይ ለመወረራችን ምክንያት ነው ያሉትን ማኅበራዊ አደረጃጀታችንን እንደ ገዳው አደረጃጀት በዐሥር መደብ በመክፈል «ቁጥራችን ብዙ ይኹን እንጂ ውጊያ የሚችሉት ጥቂቶች፣ ወደ ውጊያ የማይቀርቡት ብዙዎች በመኾናቸው ተወረርን» ሲሉ በምሬት የተወረርንበትን ምክንያት ያስረዳሉ።

አባ ባሕርይ በዐሥር የከፈሉት የዘመኑ ማኅበራዊ አደረጃጀት እንደሚከተለው በመዘርዘር ከዐሥረኛው አደረጃጀት ውጭ ያሉቱ ዘጠኙ ለመወረራችን መንስኤዎች እንደኾኑ ተጠያቂ ያደርጓቸዋል፡፡ (ምንጭ፡- «ዜናሁ ለጋ*»፡ በብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ በ1959 ዓ.ም. ከግዕዝ ወደ አማርኛ ከተተረጎመው ከገጽ 47-55)፡-

  1. [ከማኅበራዊ አደረጃጀቶቻችን] መካከል አንዱ ክፍል ስፍር ቁጥር የሌላቸው የመነኮሳቱ ወገን ነው፤ እንደዚሁ ታሪክ ፀሐፊና እንደሱ ብጤዎች በልጅነቱ ሳለ መነኩሴዎቹ ደልለውት የሚመነኩስ አለ፤ ውጊያ ፈርቶ የሚመነኩስ አለ።
  2. ሁለተኛው ክፍል ደብተራ ይባላል፤ መጻሕፍቱንና የክህነቱን ሥራ ሁሉ ይሰራል፤ ምሳሌነት የአሮን ልጆች ከኾኑት ከሌዋዊያንና ከካህናት ይወስዳል።
  3. ሦስተኛው ክፍል ዣን ሐጻና ዣን መዓሠሬ ይባላል፤ ፍርድ ይጠብቃሉ ከውጊያ ግን ይርቃሉ።
  4. አራተኛው ክፍል የመኳንንት ሚስቶችና ወይዛዝሮች ደጋፊዎች ናቸው፤ ኃይለኛ ወንዶች፣ ጠንካራ ጎልማሶች ኾነው ሳለ ወደ ውጊያ አይቀርቡም፤ የሴቶች ሎሌዎች ነን ይላሉ።
  5. አምስተኛው ክፍል ሽማግሌ፣ ገዢ፣ ባለርስት ይባላሉ፤ መሬታቸውን ያሳርሳሉ፤ በፍርሀታቸው አያፍሩም።
  6. ስድስተኛው ክፍል ገበሬዎች ናቸው፤ እርሻ ላይ ይውላሉ፤ ስለ ውጊያ ሐሳብ የላቸውም።
  7. ሰባተኛው ክፍል ንግድ በመነገድ ተጠቅመው የሚኖሩና የራሳቸውን ረብ ጥቅም የሚሹ ናቸው።
  8. ስምንተኛው ክፍል የጥበብ ሰዎችን ናቸው፤ ማለት ብረት ሠራተኞች፣ ጸሐፊዎች፣ ሰፊዎችና ጠራቢዎችና እነሱን የመሳሰሉት ናቸው፤ ሁሉም ውጊያ መዋጋት አያውቁም።
  9. ዘጠነኛው ክፍል ልመናን ተግባር አድርገው የሚኖሩ አዝማሪዎች፣ ባለ መለከተኞች፣ ባለ ከበሮዎችና ባለ በገናዎች ናቸው። የሰጣቸውን ይመርቁታል። የማይረባ ምሥጋናና ከንቱ ውዳሴንም ይሰጡታል። የከለከላቸውንም ቢረግሙት ዕዳ አይኾንባቸውም፤ ወግ፣ ልማድ፣ (ሕግ) አለን ይላሉና፤ ከውጊያ በረጅሙ ይርቃሉ።
  10. ዐሥረኛው ክፍል ጦርና ጋሻ የሚይዙት፣ ለመዋጋትም የሚችሉ ናቸው፤ ወደውጊያ ለመሮጥ የንጉሡን ፈለግ ይከተላሉ፤ እነዚህ በማነሳቸው ምክንያት ሀገራችን ጠፋች።

አባ ባሕርይ የወቅቱን የኢትዮጵያ ማኅበራዊ አደረጃጀት በዚህ መልክ ካስቀመጡ በኋላ ከኦሮሞ የገዢ መደብ አደረጃጀት ጋር በማወዳደር «ጋ* ግን እነዚህ ያነሳናቸው ዘጠኝ ወገኖች የሉበትም። ሁሉም ከደቂቅ እስከ ልኂቅ ለውጊያ የሰለጠኑ ናቸው። ስለዚህ ያጠፉናል፣ ይፈጁናል።» በማለት ጥቂቶቹ ብዙውን የወረሩበትን ምክንያት ያስረዳሉ።

የአባ ባሕርይ ትንታኔ ሰፋ ተደርጎ ሲታይ፣ በዚያ ዘመን ኦሮሞ ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ከባሌ በታት በተነሳው የኦሮሞ የገዢ መደብ ወረራ ሀገራችን የጠፋችው ከአንድ እስከ ዘጠኝ ድረስ ባሉት ክፍሎች ውስጥ የምናገኘው ማኅበረሰብ ዐሥረኛው ክፍል ብቻ በሚያደርገው ተጋድሎ ሰላም አግኝቶ ለመኖር በመዘጋጀቱ ነው የሚለውን እናገኛለን። ይህ እሳቤ ዛሬም ድረስ አልተለወጠው። አብዛኛው ሰው ዛሬም እያሰበ ያለው ሌሎች ታግለው ባመጡት ነጻነት በሰላም ለመኖር ነው። የኢትዮጵያን ፖለቲካ በንቃት መታዘብ ከጀመርሁ ጊዜ ጀምሮ እንደታዘብኩት ብዙ ሰው በርስቱ ላይ ሊገድለው፣ ሊዘርፈውና ሊያፈናቅለው ከሚመጣ የገዳ ሥርዓት ናፋቂ ራሱን ተከላክሎና መብቱን አስከብሮ ከመኖር ይልቅ ሌላ አካል መስዋዕትነት ከፍሎ ታድጎት ያለ ሐሳብ፣ በሰላም በሞቀ ጎጆው ውስጥ መኖርን ምርጫው ያደረገ ይመስላል።

ከአራት መቶ ዓመታት በኋላም ሰሚ ያላገኙት አባ ባሕርይ «በዐሥረኞች ጥቂትነት ምክንያት ሀገራችን ጠፋች።» ያሉት ከሳቸው ዘመን በኋላ የሚመጣው ትውልድ በሳቸው ዘመን ከነበረው ትውልድ ማኅበረሰባዊ ስንፍና ትምህርት ወስዶ ሀገሩን ከዳግም ጥፋት እንዲታደግ ነበር። የአባ ባሕርይ ምክር ከተስተጋባ አራት መቶ ዓመታት በኋላ ዛሬም የበዛው «በእነዚህ ጥቂትነት ሀገራችን ጠፋች» የተባለው ክፍል ሳይኾን ከአንድ እስከ ዘጠኝ ክፍል ድረስ የተደረደሩት መደቦች የባሕርይ ወራሽ የኾነው ነው።

የኦሮሞ ብሔርተኞች በሚፈጽሙት የንጹሐን የጅምላ እልቂት በዚህ ዘመን ታሪክ ሲደገም በዐይናችን የምናየው ከአራት መቶ ዓመታት በፊት የወረረንን የኦሮሞ ገዢ መደብ የሚያግዝ ማኅበራዊ አደረጃጀት ወራሾች ኾነን ቆመን በመቅረታችን ነው። አባ ባሕርይ ከአንድ እስከ ዘጠኝ ክፍል የመደቡት ሀገር ስትጠፋ ዝም ብሎ ያይ የነበረው ዋልጌና ቧልተኛ ቡድን ዛሬም በዚህ ዘመን ሲኾን ራሱን በገጣሚነት፣ በሙዚቀኝነት፣ በደራሲነት፣ በተለማማጭነት፣ በአስመሳይ የጥበብ ሰውነት በአማካሪነት፣ ወ.ዘ.ተ ስም ራሱን ጀቡኖ ተቀምጦ ከአራት መቶ ዓመታት በፊት ሀገራችን በጠፋችበት ሰልቃጩ የገዳ ሥርዓት ዛሬም ደግማ እንድትጠፋ እያገዘ ይገኛል። እኔም ልክ አባ ባሕርይ ከአራት መቶ ዓመታት በፊት እንዳሉት በድሮው የሉባ የተስፋፊነት እና ሰልቃጭነት አጀንዳ የሰከሩ የሉባ ሥርዓት ናፋቂዎች ሳይሰልቡት ራሱን እየሰለበ እስከመስጠት ድረስ የፈራ ነሆለል በመብዛቱ የተነሳ ሀገራችን እየጠፋች ትገኛለች እላለሁ።

ባጭሩ የጋሞው መነኩሴ አባ ባሕርይ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከባሌ በታች የተነሱ ወራሪዎች በየስምንት ዓመቱ በሚያካሂዱት ወረራ ሀገራችን ስትጠፋ፣ ምድሩን የሬሳ ክምርና ባድማ ሲያደርጉ በዐይናቸው አይተው የመዘገቡት ታሪክ፣ ሀገራችን የጠፋችበት ምክንያትና የሰጡት ምክር ሰሚ ባለማግኘቱ እነሆ ዛሬ በ21ኛ መቶ ክፍለ ዘመን የ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመኑን ወረራና ውድመት ተምሳሌት ባደረጉ የስጋና የመንፈስ ልጆቻቸው ያንን ታሪክ ለመድገም በሚያደርጉት ወረራና ውድመት ብአዴን የሚባለው የአማራ ርግማን በተጫነበት “ሰሜን ሸዋ” በሚባለው የአማራ ክልል ተብዮ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ሲደገም በዐይናቸውን እያየነው ነው።

ከአራት መቶ ዓመታት በፊት የተፈጸመው የውድመትና ጽልመት ታሪክ በዚህ ፍጥነት ሲደገም በየቀኑ በዐይናችን እያየን ያለነው በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የወረረን ወራሪ ኃይል የስጋና የመንፈስ ልጆች የሆኑትን ወራሪዎች either by action or inaction የሚያግዝ ብአዴን የሚል አማራ መቃብሩን ፈንቅሎ እንዳይወጣ መቃብር ጠባቂ እንዲሆኑ ተደርገው የተፈጠሩ ነውረኞች ድርጅት በሕዝባችን ላይ በመጫኑ ነው።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator