መንግስት በጋዜጠኞች ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ እንዲያቆም ኢሰመጉ ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ሚያዚያ 29/2014 አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስቧል።

ጋዜጠኞችን በሚመለከት ኢሰመጉ ባሰባሰበው መረጃዎች መሰረት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በቀን 22/08/2014 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ በፖሊሶች ተይዞ ማንነቱን ከጠየቁ በኋላ የተያዘው በስህተት እንደሆነ ተነሮት ተለቆ እንደነበር ገልጧል።

በማግስቱ በ23/08/2014 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ሰዓት አያት አካባቢ ካለው መኖሪያ ቤቱ መሳሪያ በታጠቁና ሲቪል በለበሱ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት ሊወሰድ መቻሉን እና እስካሁንም ያለበት እንደማይታወቅ ኢሰመጉ በሪፖርቱ አካቷል።

በተመሳሳይ ጋዜጠኛ ዓባይ ዘውዱ በሃምሌ 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ ተራ አካባቢ በስራ ላይ እንዳለ በፖሊሶች ተይዞ ከአስር ቀናት እስር በኋላ በዋስ ሊፈታ መቻሉን እና በስህተት ስለመታሰሩ የተነገረው ስለመሆኑ ተወስቷል።

ለዋስትና ካስያዘው ገንዘብ ጋር በተያያዘ ኢሰመጉ ቀደም ሲል የነበረውን ሪፖርት ተጠቅሞ የሰራው ስለሆነ እንጅ ጋዜጠኛው ባደረገው ተደጋጋሚ ጥረት የዋስትና ገንዘቡን ለማስመለስ መቻሉንና የተሳሳቱ ስለመሆናቸውም የሚገልጽ ደብዳቤ የተቀበለ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ይሁን እንጅ ከተፈታ በኋላ ከሙያዊ ስራው ጋር በተያያዘ አሁንም ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰበት ስለመሆኑ ሪፖርቱ አመላክቷል።

ይህ ጋዜጠኞችን በመንግስት የጸጥታ አካላት አስገድዶ የመሰወር ተግባር ከዚህ ቀደም የተራራ ኔትዎርክ መስራች በሆነው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ላይ ተፈጽሞ እንደነበር ይታወሳል ብሏል፤ ይህም በፕሬስ ነጻነት ላይ ከፍተኛ መሰናክል የሚፈጥር ድርጊት ነው ብሎታል።

ተያያዥ የህግ ግዴታዎችን በተመለከተም የመገናኛ ብዙሀን አዋጅ ቁጥር 1238/2021 በአቀጽ 48 ላይ የመገናኛ ብዙሃን እና የጋዜጠኞች መብቶችን ሲዘረዝር ዜና ወይም መረጃ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማራጨት፤ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ አስተያየት ወይም ትችት የማቅረብ መብት እንዳላቸው ጠቅሷል።

በመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ላይ የሚከሰት ጣልቃ ገብነት፣ ተፅዕኖ፣ ጥቃትንና የደህንነት ሥጋትን ጨምሮ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር የፕሬስ ነፃነትን የሚያደናቅፍ አሠራር ከተፈፀመበት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ወይም አቤቱታ የማቅረብ፤ መብት እንዳለው ይደነግጋል ብሏል፡፡

ኢሰመኮ የሰብዓዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ድንጋጌ፣ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳንንም በመጥቀስ የጋዜጠኞችን መብቶች በግልጽ አስፍሯል።

በመጨረሻም ኢሰመጉ በሪፖርቱ መንግስት የፕሬስ እና የሚዲያ ነጻነትን እንዲሁም የጋዜጠኞችን መብት እንዲያከብር፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ያለበትን ሁኔታ በአስቸኳይ ይፋ በማድረግ ተገቢውን የህግ ስነ-ስርዓት እንዲከተል ጥሪ አድርጓል።

መንግስት በጋዜጠኞች ላይ ኢሰብዓዊ ድርጊት ከመፈጸም እንዲቆጠብ እና ይህንን ድርጊት በሚፈጽሙ አካላት ላይ ተገቢ እና ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator