0 0
Read Time:3 Minute, 30 Second

በቸልታ ታልፎ ሳያመጣ መዘዝና ድክመት፤
በጥልቁ ይመርመር ይጠናም ማነነት።

አንድ ተቋም ፤አላማው እንዲሳካ፤አነሳሱን፤ያከናወናቸውን ተግባራት(ደካማና ጠንካራ ጎኖቹ)፤የደረሰበትን ደረጃ፤ቆም ብሎ ማየትና መመርመር እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።ይህን ካልፍጸመ ግን ምስቅልቅል ያለ ሁኔታ እንደሚያጋጥመው ጥር ጥር የለውም።የወደፊትጉዞውንም መንተንበይና ሊያጋጥሙ በሚችሉ እንቅፋቶች ላይ ቅድም ዝግጅት አድርጎ የመከላከል አቅም አይኖረውም ፤መጨረሻውም ፤የህልውና አደጋን ያስከትላል።

አማሮች የህልውና አደጋ እንደተደቀነብን አውቀን፤ከመቼውም በበለጠ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምናደርገው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ፤ አበርታች ነው።፤ በልዩ ልዩ የአደሩጃጀት አይነቶች እየተመዝገብ የሚገኝውም ውጤት እንደ ህዝባችን ፍላጎት በተፈለገው ፍጥንት ባይጓዝም፤ተስፋ ሰጭ ነው።

ይሁን እንጅ በዚያው መልክ ድክመቶች መከሰታቸው፤እውቅ ነው።አንዳንዴም፤ መደናገጥን ፤የሚያሳድሩ ሁኔታውችን እናስተውላለን።ለዝህ ዋነኛው ምክንያት የአደረጃጀት ልምድ ማነስ ነው፤ እንደሌሎቹ 50 እና 60 አመታትን ያላስቆጠረ ።ቅድመ ጥናት ካለአለማድረግም ጭምር ነው።

የድክመቶች ምክንያቶች

ሀ.ባብዛኛወቹ የአማራ ድርጅቶች ውስጥ አባል ለመሆን፤ዋነኛው መስፈርት ፤”አማራ ነኝ” ወይም “አማራ ነው/፣ናት” መባል፤እንጂ፤ጥልቅ የሆነ የማንነት መመዘኛ የለም። በዝህ ሳቢያ ደጉ፤ ሁሉን አቃፊ የሆነው፤፤ፈርሀ እግዜር መለያው የሆነው አማር፤ቋንቋውን እየተናገሩ፤እያጠፋት ያሉትን ጠላቶቹን ከልጆቹና ከወዳጆቹ ለመለየት አለለምቻሉ ፤ አንደደኛው ነው።

ለ.ከላይ በተጠቀሰው መልክ ማንነታቸው፤በቅጡ ሳይጣራ አባላት የሆኑ ፤በአመራር ደረጃ ፤ጉብ እያሉ የሚጫወቱት የአፍራሽነት ሚና ሁለተኛው ምክንያት ነው።በቋንቋች ያቅራሩና ያነበነቡና ሁሉ ጀግኖችንን፤አዋቂያችንና ታማኞቻችን እየመሰሉን የሚፈጸምብን ደባ ቀላል አልሆነም።

ሐ.በሌላ በኩል በአመራር ደረጃ ላይ በየሚገኙ አማሮች መካከልም የሚፈጠረው ችግር በሶስተኛ ደረጃ የሚታይ ምክንያት ነው፤አንዳንድ አማሮች፤ለአማራ አደረጃጀት ጠንክሮ አለመውጣት ይህ ዋንኛ ምክንያት ነው ሲሉ ይስተዋላል፤የአማራን ሕዝብን አስተያየት ተከትሎ የተደረጋ ጥናት ባይኖርም፤ ያለጥርጥር በየእለቱ የምናየው ነው፤የዝህንም ምክንያቶች እንደሚከተልው ከፍሎ ማየት ይቻላል፤

ሀ.መንደረተኝነት(ጎጠኝነት፤ወንዘኝነት፣)

ይህ አይነቱ አማራን የመከፋፍልና የማዳከም ሥራ በኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች ፤የተጠነሰሰ ቢሆንም፤ወያኔ ጫካ እያለ መጀመሪያ በፕሮፓጋዳ(በተለይ በነድምጺ ወያኔ ) ስልጣን ሲጨብጥ በአዋጅ በግልጽ ያላተቀናቀኝ፤በስራ ላይ ያዋለው ነው።ወያኔ “የሸዋ አማራ” እያለ የፕሮፓጋንዳ መርዙን ሲረጭ፤ ለጎጃሜው፤ለወለዮው፤ለጎንደሬው፤ለሀረሬውና ለሌላውም ፤ አማራ አዝኖ፤ሳይሆን፤ደረጃ በደረጃ አማራን ቢችል ለማጥፋት፤ሳይቻለው ቀጥቅጦ ለመግዛት እንዲያመችው ነበር ።ይህንንም ለመተግበር እንዲረዳው ሲመቻው በግልጥ ሳይሆለት፤በረቀቀ መንገድ የራሱን ሰወች በአማራ አደረጃጀት ውስጥ አርሥርጎ ማስገባት ፤እኩይ ተግባሩን ሥራ ላይ አውሎታል፤አማራ ጠል ሀይሎች፤ ኦነጋዊያን ጨምሮ ፣፤የአማራን መደራጅት፤ከምንም በላይ የሚፈሩት ስለሆነ፤ምንግዜም ፣አይተኙም፤አማራውን እስክ መንደር ድረስ ወርዳው ይህን እኩይ ተግባራቸውን ለመፈጸም ከመሞከር ወደ ኋላ አይሉም(ሰሞኑን፤በደቡብና ሰሜን ጎንደር መሀል፤ልዩነት ለመፍጠር እንደሚያደርጉት መፍጭርጨር አንዱ ማሳያ ነው፤ የአማራው የእምቢተኝነት ማእከል የሆነውን ጎንድርን አዳክመን ፤”የአማራውን አከርካሪውን መተንዋል”ፍጻሜ የማየት ህልማቸው ማሳካት ተልእኮ ነው ፤ቅዥት ሆኖ ይቀራል እንጂ)።

ለ.በፖለቲካዊ መስመር ልዩነት በመሪወች የሚፈጠር አለመግባባት፤
ይህ በአብዛኛው ፣ ወደ 60 ወቹ ትውልድ የሚወስደን ነው(፣ኢዲዩ፤ኢሕአፓ፤ኢሰፓ ወዘት)፤የአማራው ችግር በዚያ ትውልድ ዘመን ብዙ የተጠነጠና አሁን ላለበት ችግር እንደዳረገው፤ተዋናይ የነበሩት ሁሉ የመሰከሩት፤ስለሆነ፤ብዙ ማተትም አስፈላጊ አይደለም።የዛ ዘመን ትውልድ አካል ከነበሩት አማሮች፤ መሀል ልዩነታቸውን ርህፍ አድርገው ትተው ፤በጸጸትና በቁጭት ተነስቶው ፤አማራውን፤አሁን የተጋረጠብትን የሕልውና አደጋ ለመቀልበስ፤ደፍ ቀን የሚሉና የአማራ ወጣትም አቅጣጫውን እንዳይስት፤ምክራቸውን ያለማቆረጥ በመስጠት ላይ ሲሆኑ፤የሚያሳዝነው፤ አሁንም በጥንቱ አባዜአቸው፤የመከፋፈል ሥራቸውን ያላቆሙ አሉ።የአሁኑም ትውልድ የ60ወቹ እያለ ጥርጣሬ እንዲያድርበት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ሐ.የስልጣን፤ጥመኝነት፤ታይታ ወይም ተክለ ስምንት ፈላጊወች
እነዝህ፤አንድን የአማራ ተቋም እኛ ካልመራነው ባዮች፤ሲሆኑ፤አለብላቢት ምላሳቸውን በመጠቀም ሙያ በልባቸው ሆነው በቅንንነትና በታማኝነት የሚያገለግሉ የአማራ ልጆችን ማስገለልና ማስጠላት መለያቸው ነው። ልይህንን ለማሳካት፤በአሉባልታ፤በሀሜትና ስም ማጥፋት አባላትን በመከፋፈል ፤ዘወትር የደካማ ድርጅት መሪወች መሆን የሚመኙና ተንኮላቸው ሲነቃባቸው፤ጥቂት ደጋፊወቻቸውን በመያዝ፤ተድራቢ(ተለጣፊ) ድርጅት ፈልፋዮች ናቸው፤የግል ስልጣንና ዝና እንጂ ፤የአማራ ህልውና ለነሱ ቦታ የለውም።

መ.ቅጥረኞች(ተከፋዮች)ና ሆዳሞች

እነዝህ የአማራ ድርጅት፤ጠንክሮ እንዳይወጣ ምክንያት ከሆኑት መሀል መሆናቸውን የሚክድ አይኖርም፤። በቅንነት፤በቁጭት፤ለአማራ ተቋማት መጠናከር ብሎ ወገን የሚያዋጣውን ገንዘብ በረቀቀ መንገድ ቅርጥፍ የሚያደርጉ ናቸው፤አማሮች፤አንዳንዴ በቋሚ ክፍያ፤ሌላግዜ በመዋጮ፤በጎፈንድሚና በሌሎችም መንገዶች ድጋፋችንን መስጠት ያላቆረጥን ቢሆንም፤፣”ተበላ” ፣ሊበሉት ነው” እየተባለ የሚነዛው ወሬ የተለመደ ሆኗል።በሀቅ እየሰሩ ላሉ ፤ተገቢውን ድጋፍ እንዳያገኙም እንቅፋቶች ናቸው።ሆዳሞቹን ከቀጣፊወቹ መለየት የሚያስችልና መሬት ላይም የሚሰጠውን ድጋፍ ለመቆጣጠር የሚያስችል የአሰራር ሥርአት አለመፈጠሩ ነው አስተዋጽኦ አድርጋል።፣ይህ አሰራር
ቅጥ ይዞ ቢሆን ኖር፤ የቃልኪዳን ቀለበቶቻቸንና ንብረታቸውን ሳይቀር እየሸጡ፤ድርጅቶቻቸውን ካፈረጠሙ ጠላቶቹ አማራ ባስከነዳ ነበር።፣
ከላይ በተዘረዘሩት ምክንያቶች ፤በአማራ አደረጃጀት ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች አስተዋፅኦ ካበረከቱት መካከል፤ ከልክ ያለፈ ትእግስት፤ይሉኝታና እያዩ እንዳላዩ ማለፍም የሚካተቱናቸው። አማሮች ከአሁን በኋላ ከእዝህ አይነት ጎታች ባህል ተላቀን፤ተቋሞቻችንን ልንጠብቅ ይገባል፤፣”ጠላትማ ምንግዜም ጠላት ነው…፣” የተባለው እኮ ያለምክንያት አይደለም።፣፣

አማራ ከማንም በበለጠ ከሁሉም ነገዶች ጋር የተቀላቀለ በመሆኑ ይህ ውህድነቱ፤ጠቀሜታ እንዳለው ሁሉ፤ጉዳትም አስከትሎበታል፤በማንነቱም ፈጥኖ ለመደራጅቱ፤እንቅፋት ሆኖበታል፤ይሁን እንጂ ውህድነቱ ከጥቃት አላዳነውም።ይህ በማንነቱ ላይ እየተደረገ ያለው የጥፋት ዘመቻ እስካልቆመ ድረስ ፤አማራ ፍጹም አድስ አይነት አደረጃጀት ስልት ሊከተል ይገባል።

ቸር እንሰንብት

#ከፍያለው

Avatar

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
Avatar

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator