1 0
Read Time:3 Minute, 11 Second

ከአማራ ህዝባዊ ኃይል /ፋኖ/ የውጪ ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ።

June 21, 2022
ሰኔ 15 2014 ዓ.ም

ከጥቂት ቀናት በፊት በፓርላማ ሆን ብሎ ጠ/ሚ አብይ አህመድ “ኦሮሞ ጠል” በማለት አማራው ላይ በተለይም ፋኖና አዲስ አበቤ ላይ ያነጣጠረ ንግግር በማድረጉ በምዕራብ ወለጋ፣ ጊምቢ ወረዳ ውስጥ እስካሁን እንደሰማነው ቁጥራቸው ከአንድ ሺ በላይ የሆኑ አማራዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል። ይህ ጠቅላይ ሚንስትሩ የቀሰቀሰው ጭፍጨፋ ሕፃናትን፣ አራስን፣ ወጣትን፣ አዛውንቶችን፣ ሴቶችን፣ ወንዶችን ሰለባ ያደረገ ነው። ሟቾቹ በአብዛሃኛው የእስልምና እምነት ተከታዮች ከመሆናቸውም በላይ ከነዚህ ውስጥ ሃምሳ የሚሆኑት የተጨፈጨፉት በመስጊድ ውስጥ ነው። እነዚህ ወገኖቻችን እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ባላቸው ተዘዋውሮ የመኖር የዜግነት መብታቸው በአካባቢው ለረዥም ጊዜ የቆዩና ከአካባቢው ወገናቸው ጋር ተጋብተው የተዋለዱ ከመሆናቸውም በላይ የማንም የግል ይዞታ ያልነበረ የሃገራቸውን ጫካ መንጥረውና አልምተው እራሳቸውን ብቻ ሳይሆን ሌላውንም ማህበረተሰብ ጭምር የሥራ ፍሬአቸው ተጠቃሚ እንዲሆን ያደረጉ ለመሆናቸው የማይታበል ሃቅ ነው።

በጣም የሚገርመው ይህንን አሰቃቂ የዘር ማጥፋት “እኔ አልፈጸምኩም፤ እሱ ነው” እየተባባሉ ኦነግ ሸኔና የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እንደተለመደው ቢካሰሱም የመገናኛ ብዙሃን በቀጥታ ከሃገሪቱ ፓርላማ እንዳሰራጩት በአብይ አህመድ ቀስቃሽነትና በሁለቱም ተባባሪነት እንደተፈጸመ ሊደብቁት የማይችሉት ሃቅ ነው። ጠ/ሚንስትሩ በፖሊሲ ደረጃ የያዘው ዘር ማጥፋት ከመቼውም ይበልጥ ተፋፍሞ እየቀጠለ ነው። ይህ የአማራን ዘር የማጥፋት ፕሮጀክት በኦሮሚያ ክልል ብቻ ሳይሆን የአማራው አውራ ጠላት በሆነው ብአዴን ተባባሪነት በራሱ በአማራ ክልልም ሕግን በማስከበር ሽፋን ስም በስፋት በመፈፀም ላይ ይገኛል።

ጀግናው የአማራ ሕዝብ ሆይ! እንዳለመታደል ሆኖ ሊጠብቅህ የሚገባው የአማራ ብልጽግና ከጠላትህ ከኦኖጋዊው የኦሮሞ ብልጽግና ጋር በማበር ሕልውናህን አደጋ ላይ ከጣለው ዋል አደር ብሏል። በቅርቡ ግን እነጀኔራል አበባውን፣ እነዶ/ር ሰማኸኝንና ይልቃል ከፍያለውን ይዞ የህልውናህን ዋስትና ፋኖን እያሳደደ በመግደል፣ በማሰርና በማንገላታት ላይ ይገኛል። እንኳን ሌላ ክልል ውስጥ የሚኖረውን አማራ ወገንህን መጠበቅና ድምፅ መሆኑ ይቅርና አንተንም በገዛ ክልልህ ውስጥ ለጥቃት አጋልጦ ሰጥቶሃል። ብአዴን “ደሜን ቢያፈሰው ወገኔ ነው፤ ሌሎቹ የሚፈልጉት ደም እንድንቃባ ነው” ብለህ በማስተንተን እጅህን ስትሰበስብ እሱ ግን አላዘነልህም፤ ሌሎቹ በሚያዩህ መነፅር እያየ ይበልጥ እንድትጠቃ እያደረገህ ነው። ለመሆኑ የአማራ ዘር እንዲጠፋ ከሚጥሩ የኦሮሙማ ነፍሰ ገዳዮች ጋር የሚተባበረውን ብአዴንን እስከመቼ ድረስ ነው የምትታገሠው? “ሙያ በልብ ነው!” እያልክ እራስህን መደለልስ የምታቆመው መቼ ነው?

ጀግናው የአማራ ሕዝብ ሆይ! በቅርቡ ፋኖን አላስነካም በማለት የወሰድከው የመከታ እርምጃ አማራጭ የለለው ተፈጥሯዊ ግዴታህ ቢሆንም የሚያስመሰግንህ ነው። ግን ይህ ብቻውን በቂ ነው ብለን አናምንም። በመጀመሪያ ብአዴንና አገልጋይ ካድሬዎቹን ከመሃልህ ክስልጣናቸው መመንጠር ግድ ይልሃል ብለን እናምናለን። አጎብዳጁንና የኦሮሙማ አገልጋይ የሆነውን ብአዴንን ከክልልህ ሳታፀዳ ሌላ ክልል ውስጥ የሚታረዱትን አማራ ወገኖችህን ልትደርስላቸው ፈጽሞ አትችልም። ቀጥሎም የእርስትህን ዳር ድንበር ለማስከበርና ከወራሪውና ተስፋፊው ኦሮሙማ ለመጠበቅ በመሃልህ ያሉትን “የአማራው አንገት አንድ መሆኑን” የማያምኑ ጎጠኞችን በመሃልህ የጠላት መግቢያ ክፍተት ስለፈጠሩብህ አደብ ማስገዛት ይኖርብሃል ብለን እናምናለን።

ጀግናው የአማራ ሕዝብ ሆይ! 1500 ሜትር እርዝመት ያለው ባንዲራ ሰፍተህ ማንነቱን ሳታይ ፍትሃዊ መስሎህ አክብረህ “የዘመናችን ሙሴ” እያልክ ባህር ዳር የተቀበልከው ጠ/ሚ አብይ አህመድ ከደመኛህ ከሕወሃት ጋር በመናበብ ሰሜን ወሎን፣ ደቡብ ውሎን፣ ሰሜን ሸዋን እና ደቡብ ጎንደርን እንዳልነበሩ ካስደረገብህ በኋላ ዛሬ ከጦርነት የተረፈውን ጎጃምን ቄሮዎችን የአማራ ክልል ልዩ ሃይል ዩኔፎርም በማልበስ በማስወደም ላይ ይገኛል። ከ5000 በላይ የሚሆኑ ልጆችህን ፋኖ ናችሁ በማለትና፣ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ አንተባበርም ያሉ የልዩ ሃይል አባሎችን አሥሯቸዋል። ይህ እጁ በደም የተነከረ ጠ/ሚንስትር ከመከላከያ ውስጥ ያሉ አማራዎችን በተለያየ ወንጀል በመክሰስ የሚያሥረውን እያሠረ፣ የሚያሳድደውን በማሳደድ ላይ ይገኛል። አዲስ አበባን በነደመቀ መኮንን፣ በኢዜማና በአብን አመራሮች ተባባሪነት በቁጥጥሩ ሥር አድርጓል። አሁን የቀረው አንተንና ልጆህን አዳክሞ አፅመ እርስትህን መንጠቅና ከሕወሃት ጋር መከፋፈል ነው። ይህ ሊሆን የሚችለው ፋሽስቱና እሥስቱ አብይ አህመድ በአንተ ላይ የጀመረውን የዘር ማጥፋት ሲያገባደድ ስለሆነ አንተን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማፅዳቱን በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ብቻ ሳይሆን የራሥህ በተባለውም ክልል ውስጥ ተያይዞታል።

በሚያሳዝን ሁኔታ ከዓለም አካባቢ እነሱን አቁሙ፣ አንተን አይዞህ፣ አጥፊዎቹን ለዓለምአቀፍ ፍርድ እናቀርብልሃለን የሚል የሚያጽናና ድምጽ እየተሰማ አይደለም። ስለሆነም ለሕልውናህ ዋስትና ከፈጣሪህ በታች አንተው እራስህና ልጅህ ፋኖ ብቻ ናችሁ። ሌሎቹ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ከጎንህ እንደሚቆሙ ጥያቄ ውስጥ የማይገባ ቢሆንም ለጊዜው ግን መተማመን ያለብህ በራስሃና በራስህ ብቻ ነው። ውድ ጀግናው አማራ ሆይ፤ የሞት መልዕክተኛ የሆነውን የዘር አጥፊ አገዛዝ ታግሎ ማሸነፍ ብቻ ነው ህልውናህን ብዘላቂ ህል። ብአዴንን ወንድሜ፣ አብይን መንግሥቴ እያልክ በሁለቱም ከምትበላ አብይ የሚባል መንግሥትና ብአዴን የሚባል ወንድም እንደለለህ አውቀህ እስከመጨረሻው ለሕልውናህ እንድትዋደቅ ጥሪያችንን እናቀርብልሃለን።

“አማራ ሆይ የሞት መልዕክተኛ የሆነውን የዘር አጥፊ አገዛዝ ታገል”
የአማራ ሕዝብ በጠላቶቹ ላይ ድል ይቀዳጃል!
የአማራ ህዝባዊ ኃይል/ፋኖ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ

PDF view

Avatar

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
100 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
Avatar

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator