0 0
Read Time:3 Minute, 5 Second

በአ አ 6/12/2020 ላይ አንድ Nuro B Dedefo የተባለ ጽንፈኛ የኦሮሞ ብሔርተኛ
“Abraham Lincoln vs Menelik II” በሚል ርእስ ሁለቱን መሪዎች እያነጻጸረ በፌስቡክ ላይ ጽፎ አንድ የተከበረ ግለሰብ መጣጥፉን ላከልኝና አነበብሁት። ደራሲው አብርሃም ሊንኮንን የባርያ ነፃ አውጪ እያለ ሲያሞግሰው፣ አፄ ምኒልክን ደግሞ የባሮች ሻጭና ባለጸጋ ሲል ይወነጅላቸዋል። ጽሑፉን ሳነበው ቅራቅንቦና አርቲቡርቲ ስለሆነ ምንም መልስ ልሰጠው ዝግጁ አልነበርክሁም። ግን ዛሬ እድረገጹ ገብቼ ሳነበው አንዳንድ አድናቂዎች ዐየሁና ገረመኝ። እንደተረዳሁት አቶ ኑሮ ደደፎ የሕግ ባለሙያ ሲሆን፣ ለምን አለመስኩ ገብቶ ሊፈተፍት እንደፈለገ ማወቅ አስቸጋሪ ሆኖብኛል። ምናልባት በሠለጠነበት መስኩ ዕውቅና ማትረፍ ዐቅቶት፣ ሆይ ሆይ የሚልለትን የአጃቢ መንጋን ትኩረት ለመሳብ ከጅሎ ይሆናል። አለበለዚያ ፋይዳው ውርደት የሚያከናንብ ትዝብት እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም ብዬ አምናለሁ። አለሙያው ገብቶ ለሚዘባርቅ ሁሉ መልስ እንስጥ ከተባለ፣ የጊዜን ብርቅነት አለመረዳት ይመስለኛል። ግን ከዚህ በፊት ከጻፍሁት መጣጥፍ ጉዳዩን የሚመለከተውን ብቻ ቀንጭቤ በድረገጹ ገብቼ ልለጥፍ ብሞክር፣ ኮመንት የሚለውን ክፍል ዘግቶታል። በሐሰት በሚያስተጋባው መልእክቱ ሌላውንም እንዳያደናብር፣ ፍላጎት ያላቸው የመድረኩ አባላትም እንዲያውቁት በሚል መንፈስ ቅንጭቡን እዚህ ላይ ልዳቈስ ወደድሁኝ። መልካም ንባብ።

“ለመሆኑ የብሔር ብሔረሰብ ጭቆና በኢትዮጵያ ነበር ወይ?”
ከInternational Journal of Ethiopian Studies, Vol. XI,1, Special Issue 2017 ከገጽ 21-22 የተቀነጨበ።

በኀይሌ ላሬቦ
የጋዳን ሥርዐት አድናቂዎች፣ ሩቅም ሳይሄዱ በኦሞ ሸለቆ አካባቢ አቈጥቊጠው የነበሩትን የጂማ አባጅፋርን፣ የሊሙ እናርያን፣ የጐማንና የጉማን፣ እንዲሁም የለቃ-ነቀምቴንና የለቃ-ቄለምን መንግሥታት ሊያዩ ይገባል። እነዚህ መንግሥታት አካባቢውን የያዙት፣ ነባሩን ሕዝብ በመፈንቀል፣ ወይንም በመግደልና ለባርነት በመዳረግ መሆኑ መረሳት የለበትም። ኦሮሞቹ ከእረኝነት ወደግብርና የኑሮ ሥርዐት እንደተሻገሩ፣ የጉልበት ሠራተኛ የማግኘት ፍላጐታቸው እያሻቀበ ቢሄድ፣ ከብቶቻቸውን ለመዝረፍና ሰዎቹን ባርያ ለማድረግ ሲሉ አካባቢያቸውንና ጐረቤቶቻቸውን መዉረር እንደዋና ሙያቸው አድርገው ይዘውት ነበር። ለነሱ የባርያ ጥቅሙ ሁለገብ ነበር። የጋማ ከብትና የጠመንጃ መሸመቻ፣ የመድኀኒትና የክት ልብስ መግዣ፣ የስጦታም ዕቃ ከመሆኑ የተነሣ ከምንም ሀብት በላይ የሚፈለግ ባርያ ነበር። በጐጃም፣ በበጌምድር፣ በምፅዋና በቀይባሕር ዙርያና እንዲሁም በሸዋና በሐረር ከዚያም ማዶ ባሉት አገሮች የሚሸጡት ባሮች ዋናው ምንጫቸው ከነዚሁ አካባቢ መሆኑ ይታወቃል። (Mohammed Hassen, The Oromo of Ethiopia: A History, 1570-1860 (Cambridge: Cambridge University Press, 1990): 124-125.
Herbert S. Lewis, A Galla Monarchy: Jimma Abba jifar, Ethiopia, 1830-1932, (Madison & Milwaukee: University of Wisconsin Press, 1965): 66። ከታች የተቀመጠውን ለጅማ አባጅፋር በአፄ ምኒልክ የተጻፈውን ደብዳቤ እይ።)

በባርያ ፈንጋይነት መጀመርያውን ቦታ የያዘው ገዢው ክፍል ራሱ ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ የጅማውን አባ ጅፋር መንግሥት ብንወስድ ንጉሡ ብቻ ከዐሥር ሺ የሚበልጥ ባርያ እንደነበረው፣ ባለሟሎቹ ደግሞ እያንዳንዳቸው ከአንድ ሺ በላይ፣ ተራው ገበሬ በበኩሉ ቢያንስ ቢያንስ አንድ፣ አለበለዚያም ሁለት ባሮች እንደነበሯቸው በጊዜው ያዩትና፣ በኋላም በአካባቢው ጥናት ያካሄዱ ተመርማሪዎች ይናገራሉ ። በሩሲያ ትምህርታቸውን አጠናቅቀው እንደመጡ ወደአካባቢው ለአደን ሄደው በአባ ጅፋር መስተንግዶ ተደርጎላቸው የነበሩት በጅሮንድ ተክለሐዋርያት ወልደማርያም፣ ስለራሳቸው ሕይወት በጻፉት መጽሐፍ ውስጥ አፄ ምኒልክ ጅማን፣ ጠቅላላውን ደቡብና ሊባ አስገብረው ወደጥንታዊት እናት አገራቸው መልሰው ቀላቅለው ሲያበቃ፣ የባርያን ንግድ በአዋጅ እስካቆሙበት ጊዜ ድረስ፣ በአባ ጅፋር ባላባቶች እጅ ብቻ እየተሸጠ ወደዐረብ አገር የሄደ የሰው ብዛት ከአንድ ሚሊዮን እንደሚበልጥና፣ በጂማም ዙርያ የሚኖረውን ሕዝብ ሽጠው የጨረሱት እነሱ መሆናቸውን ይገልጣሉ (ፊታውራሪ ተከለሐዋርያት ተክለማርያም፣ ኦቶባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ)፣ ፪ኛ እትም (አአ፣ አዲስ አበባ ማተሚያ ቤት ፲፱፻፺፱)፣ 162)።

እነዚህ መንግሥታት አልፎ አልፎ አንዳንድ ጥሩ ገጽታ ሊኖራቸው ይችላል ቢባልም፣ ከመላጐደል የሚያማዝነው አስቀያሚ ጐናቸው እንደነበር የሚካድ አይደለም። የደሞክራሲ ሥርዐትን ያቀፈ ነው ተብሎ የሚወራውን የጋዳ አገዛዝ አፍርሰው፣ ገዢዎቹ አምባገነኖች ሁነው በዘፈቀደ ይገዙ ነበር። የእስላም ሃይማኖት በግድ ያልተቀበለ አንገቱን ለሳንጃ አሳልፈው ይሰጡ ነበር። አለበለዚያም ለስደትና ለባርነት ይዳረግ ነበር። ድንበራቸውን ለማስፋት የሚደረገው ጦርነት መቆሚያ አልነበረውም።

ይኸ አፀያፊ ሥርዐት ያከተመው እንግዴህ የኢትዮጵያን አንድነት መልሰው ባቋቋሙት በአፄ ምኒልክ ሥራ ነው። ንጉሠነገሥቱ በጦር ኀይልም ሆነ፣ “ሕዝብ በከንቱ እንዳያልቅ፣ ሀገር እንዳይጠፋ በሰላም ግበር” የሚለውን ጥሪያቸውን ተቀብለው በፍቅር በተዋሀዱት አገሮች፣ ከእነዚህ አስከፊ ገጽታ ካላቸው ያስተዳደር ሥርዐት አብዛኛውን ሽረው፣ ሕዝቡ እፎይ እንዲል አድርገዋል። በቦታቸው የዘረጉትም አስተዳደራቸው መዋቅር ሁለት የተጠማመሩ ግቦችን ያካተተ ነበር ማለት ይቻላል። አንደኛው ሕዝብን በግድ ሳይሆን በፍቅርና በዘዴ መግዛት ሲሆን፣ ለዚህም በሕዝቡ ዘንድ እሱ የለመደውና የሚያውቀው ያገሩ ባላባት ተቀባይነት ይኖረዋል ብለው ስላመኑበት፣ የተማረከዉን ገዢ መልሰው በቦታው ይሾሙ ነበር። ካልሆነም ልጁን ወይንም ሕዝቡ ተሰብስቦ የመረጠውን ያስቀምጡ ነበር። ከተቃዋሚያቸው ጋር መዋጋት ይመርጡት የነበረው ባላባቱ፣ በሰላም ግበር ብለው አስቀድመው ደጋግመው ለላኩት ጥሪ፣ አሻፈረኝ ሲላቸውና፣ ሌላ አማራጭ ሲያጡ ብቻ ነበር ።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
50 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
50 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator